Get Mystery Box with random crypto!

NewsAlert ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በአማራ ክልል የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት | ኢትዮ መረጃ - NEWS

NewsAlert

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በአማራ ክልል የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የኾኑት ግርማ የሺጥላ ዛሬ "በነውጠኛ ጽንፈኞች" መገደላቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ዐቢይ በዚኹ መልዕክታቸው፣ "በሐሳብ የተለየን ኹሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሳት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው" ብለዋል።

ግድያው "አስነዋሪና አሰቃቂ" መኾኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ካልተወገደ "ወደመጨራረስ እንደሚወስደን ጉልህ ማሳያ ነው" በማለትም ድርጊቱን አውግዘዋል።

ግርማ ዛሬ የተገደሉት በተወለዱበት አካባቢ መኾኑንም ዐቢይ ጨምረው ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news