Get Mystery Box with random crypto!

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ተፃፈ። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ለጠቅላይ ሚኒስ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ተፃፈ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ ፃፈ።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ፤በደብዳቤው በሸገር ከተማ እያፈረሱ ስላሉ መስጂዶች አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቋል።

" በቅርቡ በአዲስ መልኩ' ሸገር ከተማ ተብሎ ' በተመሠረተው ከተማ ህገወጥ በሚል በርካታ መስጂዶች በከተማ አስተዳደሩ አማካኝነት እየፈረሱብን ይገኛል " ያለው ምክር ቤቱ በመስጅዶች ፈረሳ ጉዳይ ላይ ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጋር በስልክ በመነጋገር መፍትሄ ላይ እንደደረስን ብናምንም የከተማ አስተዳደሩ ግን በረመዳን ወር ለጊዜው የመስጂዶች ፈረሳውን እንዲቆም በማድረግ ከረመዳን በኋላ የመስጂዶች ፈረሳ በአዲስ መልክ በብዛት ቀጥሏል "ሲል ለጠ/ሚኒስትሩ በፃፈው ደብዳቤ አመልክቷል።

በመሆኑም የመስጂዶች ፈረሳ ጉዳይ በከተማ አስተዳደሩ" ህገ-ወጥ "ስለተባለ ብቻ በቀላሉ የሚታይ ሳይሆን የህዝበ ሙስሊሙ የኃይማኖት ዋነኛ ህልውና በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ደብዳቤ ብንፅፍም እስካሁን ምላሽ አላገኘም ብሏል።

" በስልክም በጉዳዩ ላይ ለመነጋጋር ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም "ሲል አክሏል።

"ተጨማሪ መስጅዶች የማፍረስ ተግበሩ ለክልሉ ፕሬዜዳንት ደብዳቤ ከፃፍንና በጉዳዩ ላይ በአካል በመገናኘት ለመነጋገር ቀጠሮ እየጠየቅን ባለንበት ወቅት መስጅዶች እየፈረሱ መሆኑ የጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችን እንዲሁም ሕዝበ ሙስሊሙም በእጅጉ አሳዝኗል"ብሏል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በደብዳቤው ፥ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፤እንደ ጠቅላይ ሚኒስተርና እንደ የብልጽግና ፓርቲ መሪ ለመስጂዶች ፈረሳ ጉዳይ አስቸኳይ መፍትሄ የመስጠት ሙሉ ስልጣኑ እንዳላቸው በማመን ለችግሩ የማያዳግም መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቋል።

@ethio_mereja_news