Get Mystery Box with random crypto!

ሩሲያ ምዕራባዊያን ለዩክሬን F-16 የጦር ጀት አውሮፕላን ከሰጡ የከፋ ጉዳት እንደሚገጥማቸው አስጠ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ሩሲያ ምዕራባዊያን ለዩክሬን F-16 የጦር ጀት አውሮፕላን ከሰጡ የከፋ ጉዳት እንደሚገጥማቸው አስጠነቀቀች።

የቡድን ሰባት ሀገራት ጉባኤ በጃፓኗ ሂሮሽማ በመካሄድ ላይ ሲሆን የዩክሬን ጉዳይ ዋነኛ መወያያ አጀንዳ ሆኗል።ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በውይይቱ ላይ የተገኙ ሲሆን የቡድን ሰባት አባል እና ሌሎች ሀገራት የሩሲያን ጥቃት ለመመከት F-16 የተሰኘውን የጦር አውሮፕላን እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል።

አሜሪካ እና ሌሎች ሀገራት ለዩክሬን F-16 የተሰኘውን ዘመናዊ የጦር አውሮፕላን ለመስጠት ከስምምነት ላይ ስለመድረሳቸው ተገንጿል።
ሀገራቱ የዩክሬንን ወታደሮች ለማሰልጠን የስልጠና ፕሮግራም ስለማውጣታቸው ሮይተርስ ዘግቧል።

ሩሲያ በበኩሏ ምዕራባዊያን ለዩክሬን የጦር አውሮፕላኑን ከሰጡ የከፋ ጉዳት እንደሚደርስባቸው አስጠንቅቃለች።የሩሲያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሌክሳንደር ግሩሽኮ እንዳሉት የኔቶ አባል ሀገራት ለዩክሬን F -16 የጦር አውሮፕላንን ከሰጡ ጦርነቱን ከማባባስ እና ከማወሳሰብ ውጪ መፍትሔ አያመጣም ብለዋል።

ዩክሬን ከወራት በፊት ጀምሮ F -16 የጦር አውሮፕላን እንዲሰጣት ስትወተውት የነበረ ቢሆንም ጥያቄው ውድቅ ሲደረግባት ቆይቷል።የኔቶ አባል ሀገራት የዩክሬንን ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት F-16 የጦር አውሮፕላንን ብንሰጥ ጦርነቱ ዩክሬንን አልፎ ወደ ሌሎች ሀገራት ይስፋፋል በሚል ነበር።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news