Get Mystery Box with random crypto!

በተሽከርካሪ ታግዘው የሞባይል ስልክ ስርቆት ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠሩ 25 ግለሰቦችን በቁጥጥር | ኢትዮ መረጃ - NEWS

በተሽከርካሪ ታግዘው የሞባይል ስልክ ስርቆት ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠሩ 25 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ከተጠርጣሪዎቹ 6ቱ ሴቶች ሲሆኑ ግለሰቦቹ “ሿሿ” ብለው በሚጠሩት ወንጀል ከሚያገኙት ገንዘብ በቀን እስከ 35 ሺህ ብር እንደሚቆጥቡ በምርምራ ደርሼበታለሁ ብሏል የአዲስ አበባ ፖሊስ።

ከተጠርጣሪዎቹ እጅ ሁለት ሚኒባስ ታክሲዎች እንዲሁም ለወንጀል ሥራቸው የሚጠቀሙባቸውን 4 ተጨማሪ ተሽከርካሪዎችን መያዙን ፖሊስ ገልጿል።

በተጨማሪም 14 ዘመናዊ ሞባይል ስልኮች እና ገንዘብ ስለመገኘቱም የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያስረዳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news