Get Mystery Box with random crypto!

የሱዳን ጦር መሪ አል ቡርሃን ተቀናቃኛቸዉንና ምክትላቸው ዳጋሎን ከስልጣን አነሱ የሱዳን ጦር አዛ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

የሱዳን ጦር መሪ አል ቡርሃን ተቀናቃኛቸዉንና ምክትላቸው ዳጋሎን ከስልጣን አነሱ

የሱዳን ጦር አዛዥ ሌተናል ጀነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ምክትላቸውን እና የፈጣን ደጋፊ ሃይሎች (RSF) አዛዥ መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሄሜቱ በመባል የሚታወቁትን ከስልጣናቸው አሰናብተዋል፡፡

ጄኔራል ቡርሃን እና ሄሜቲ ከጥቅምት 2021 ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ጀምሮ የገዢው ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር እና ምክትል ሆነው አገልግለዋል።ጀነራል ቡርሃን በዛሬዉ እለት በተለቀቀው አዋጅ የቀድሞ የአማፂ ቡድን መሪ የነበሩትን ማሊክ አጋርን ምክትል አድርገው ሾመዋል።

ማሊክ አጋር የሱዳም ሉዓላዊው ምክር ቤት አባል ናቸው።የሉዓላዊው ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አዋጁ በአስቸኳይ እንዲተገበር መመሪያ ሰጥቷል።የጦር አዛዡ አል ቡርሃን ባለፈው ወር የአርኤስኤፍን ቡድን እንዲበተን በማድረግ ተዋጊዎቹን በአማጺነት ከፈረጀ በኃላ በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል የስልጣን ሽኩቻ ተፈጥሯል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news