Get Mystery Box with random crypto!

መቐለ አምባሳደር ማይክ ሀመር ትግራይ ክልል፣ መቐለ ይገኛሉ። በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

መቐለ

አምባሳደር ማይክ ሀመር ትግራይ ክልል፣ መቐለ ይገኛሉ።

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ለመነጋገር ዛሬ መቐለ ገብተዋል።

አምባሳደር ማይክ ሀመር መቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደረሱ በትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳና በአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በትግራይ ቆይታቸውም በፕሪቶሪያ ስምምነት አፈፃፀም፣በሽግግር ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲሁም ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከክልሉ ቴሌቪዥን በተገኘው መረጃ ፤ አምባሳደር ማይክ ሀመር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ጋር ​​ተወያይተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news