Get Mystery Box with random crypto!

Amhara Media Corporation

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharamassmedia — Amhara Media Corporation A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharamassmedia — Amhara Media Corporation
የሰርጥ አድራሻ: @amharamassmedia
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 64.60K
የሰርጥ መግለጫ

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 699

2021-02-01 15:29:05 ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን እንዲያሳውቅ ተጠየቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን 'ቁርጥ' ያለ ቀን እንዲያሳውቅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ። ሚኒስቴሩ “ቀኑን ለመቁረጥ ለፈተናው የሚያስፈልጉት 400 ሺህ 'ታብሌቶች' ወደ አገር ውስጥ መግባት አለባቸው” ብሏል።
የምክር ቤቱ የግብርና፣ የአርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ቋሚ ኮሚቴ ሚኒስቴሩ በአርብቶ አደርና ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች ያከናወነውን የሁለተኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል። ሚኒስቴሩ ለቋሚ ኮሚቴው ያቀረበው ሪፖርት እንደሚያሳየው በአፋር፣ በሶማሌ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች አርብቶ አደር አካባቢዎች ትምህርት ለማስጀመር ሲሰራ ቆይቷል።
በእነዚህ አካባቢዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ ግብዓቶች ተሟልተው ትምህርት ተጀምሯል።
በክልሎቹ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች የተገነቡ ሲሆን የመምህራን እጥረት ችግርን ለማቃለልም በጎ ፈቃደኛ መምህራን እየተሳተፉ ነው።
ይሁን እንጂ በአካባቢዎቹ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በአማካይ 30 በመቶ ያህሉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም ነው የተባለው። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ አልማዝ መሰለ እንደሚሉት፤ በሕዝብ ንቅናቄ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ያስፈልጋል።
ከዚህ ጎን ለጎን ከክልሎችና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብር መጀመር እንዳለበት ጠቁመዋል። እንደ ወይዘሮ አልማዝ ገለጻ፤ ድጋፍ የሚሹትን ጨምሮ በሌሎችም አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን በግልጽ ሊቀመጥ ይገባል።
ይህም ተማሪዎች ራሳቸውን ለፈተና እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፤ ለወላጆችም እፎይታ ይሆናል ነው ያሉት። በሌላ በኩል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት በአፋጣኝ ተገልጾ የ9ኛ ክፍል ትምህርት መጀመር እንዳለበት አሳስበዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ በበኩላቸው "ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ለማሳወቅ ለፈተናው የሚያስፈልጉት 400 ሺህ 'ታብሌቶች' ወደ አገር ውስጥ አልገቡም" ብለዋል።
ይህ የሆነው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፈጠረው ዓለምአቀፍ ተፅዕኖ መሆኑን ገልጸው፤ "በቅርቡ የማጓጓዙ ስራ ይጀመራል" ብለዋል።
ለዚህም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር እንደሚሰራና 'ታብሌቶቹ' ወደ አገር ሲገቡ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን እንደሚወሰን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል። የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ለማቀላጠፍ በ1 ሺህ 500 የፈተና ጣቢያዎች አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት በአፋጣኝ እንዲገለፅ ክልሎች እንደሚደግፉ፤ ልዩ ድጋፍ በሚሹ አካባቢዎችም የትምህርት ቤት ምገባውን በቀጣዩ ወር አጋማሽ ለመጀመር መታቀዱን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከመግባቱ በፊት ትምህርት ሚኒስቴር 26 ሚሊዮን ያህል ተማሪዎችን ሲያስተምር ቢቆይም ዘንድሮ በርካታ ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው እንዳልተመለሱ ተገልጿል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
7.2K viewsማሜ, 12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 15:27:15
መድኃኒትነት ያላቸውን ዕጽዋት በሳይንሳዊ መንገድ በማዘጋጀት ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየሠራ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ፡፡
https://www.amharaweb.com/መድኃኒትነት-ያላቸውን-ዕጽዋት-በሳይንሳ/
መድኃኒትነት ያላቸውን ዕጽዋት በሳይንሳዊ መንገድ በማዘጋጀት ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየሠራ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ፡፡ ባሕር ዳር ፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሀገር በቀል እውቀቶችን ጠብቆ በማቆየትና ሳይንሳዊ የአሠራር ሂደትን በመከተል ፈዋሽነታቸው የተረጋገጠ መድኃኒቶችን ጥቅም ላይ ለማዋል እየሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ለመድኃኒትነት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ በርካታ ዕጽዋትን ለመጠበቅ፣ ለማላመድና በተለያየ ሥነ-ምሕዳራዊ ቀውስ ምክንያት ዝርያቸው [...]
6.1K viewsAmmaOnlineBOT, 12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 15:23:09
“ከተሞች በመሰረተ ልማትና በኢንቨስትመንት እንዲጠናከሩ የክልሉ መንግስት ከምንጊዜውም በላቀ ትኩረት እየሰራ ነው” የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር
https://www.amharaweb.com/ከተሞች-በመሰረተ-ልማትና-በኢንቨስትመ/
“ከተሞች በመሰረተ ልማትና በኢንቨስትመንት እንዲጠናከሩ የክልሉ መንግስት ከምንጊዜውም በላቀ ትኩረት እየሰራ ነው” የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ ስር የነበረችው ጋሸና ከተማ ወደ ከተማ አስተዳደርነት አድጋለች። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው፣ የስትራቴጅክ ጥናትና [...]
5.0K viewsAmmaOnlineBOT, 12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 15:18:52
በአብሮነት የደመቀው ኢትዮጵያዊነት
https://www.amharaweb.com/በአብሮነት-የደመቀው-ኢትዮጵያዊነት/
በአብሮነት የደመቀው ኢትዮጵያዊነት ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) በብቸና ከተማ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት ሰላም መስጂድ የእስልምናና የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በተገኙበት ተመርቋል፡፡ የእስልምና እና የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ቤተ እምነቶች ሲገነቡ በመተጋገዝ የቆየ አብሮ የመኖርና አንድነታቸውን ዛሬም በተግባር አሳይተዋል፡፡ በብቸና ከተማ የተገነባው ሰላም መስጂድ ሲመረቅ የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች ለመስጊዱ ምረቃ እንኳን ደስ አላችሁ [...]
4.8K viewsAmmaOnlineBOT, 12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 15:05:27
የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማህበርን በዩኒስኮ ለማስመዝገብ እየተሠራ ነው፡፡
https://www.amharaweb.com/የሰባት-ቤት-አገው-የፈረሰኞች-ማህበርን-በ/
የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማህበርን በዩኒስኮ ለማስመዝገብ እየተሠራ ነው፡፡ ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማህበር በእንጅባራ ከተማ በደምቀት ተከበሯል፣ ከክብረ በዓሉ በኃላ የበዓሉን ክንውንና በቀጣይ ሊሠሩ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ሲፖዚየም ተካሂዷል። በሲምፖዚየሙ ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎችም በሀገሪቱ የሚገኙ ብዙኀን መገናኛ ድርጀቶች የህዝብ መሆናቸውን ተረድተው ለህዝባዊ በዓላት [...]
5.3K viewsAmmaOnlineBOT, 12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 12:11:57
መንግሥት የከተሞችን የወደፊት ዕድገት ያገናዘበ መሠረተ ልማት ሊያሟላ እንደሚገባ የወገዳ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ።
https://www.amharaweb.com/መንግሥት-የከተሞችን-የወደፊት-ዕድገት-ያ/
መንግሥት የከተሞችን የወደፊት ዕድገት ያገናዘበ መሠረተ ልማት ሊያሟላ እንደሚገባ የወገዳ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ። ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) በአማራ ክልል ከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሰው ህዝብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የከተሞችን ኢንቨስትመንት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን እና የመሰረተ ልማት አቅርቦትን ለማስፋፋት የክልሉ መንግስት እየሠራ ይገኛል። በዚህ ዓመት ብቻ 30 ከተሞችን ወደ ከተማ አስተዳደርነት ማሳደጉም የዚህ [...]
6.3K viewsAmmaOnlineBOT, 09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 11:19:32
"ሀገራዊ የኢንቨስትመንት ተወዳዳሪነታችንን በማሳደግና የክልሉን ፀጋ በመጠቀም የኢንዱስትሪ ልማትን ማሳደግ ይገባል" የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ
ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የ2013 የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም በደብረማርቆስ ከተማ እየገመገመ ይገኛል፡፡
የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ ለአሠራር ምቹ የሆኑ መመሪያዎችን ማሻሻል የቢሮው ትኩረት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
"ሀገራዊ የኢንቨስትመንት ተወዳዳሪነታችንን በማሳደግና የክልሉን ፀጋ በመጠቀም የኢንዱስትሪ ልማትን ማሳደግ ይገባል" ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- የኔነህ ዓለሙ - ከደብረማርቆስ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
6.0K viewsማሜ, 08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 11:18:23
የውኃ አካል ዳርቻ ክልልን ለመወሰን በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ የባለሙያዎች ውይይት በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።
ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) በውይይቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት፣ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ፈቲያ የሱፍን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ አካላትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተሳታፊዎች ናቸው።
በረቂቅ አዋጅ ላይ የሚደረገው የባለ ድርሻ አካላት እና ምሁራን ውይይት ተጨማሪ ግብዓት ለማግኘት እና በሚሻሻሉ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃ ለመሰብሰብ ያለመ መሆኑን የተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ግዛው ተናግረዋል።
ረቂቅ አዋጁ በስድስት ክፍሎች እና በ28 አንቀጾች ተከፍሎ የቀረበ ሲሆን 23 ሙያዊ ቃላትም ትርጓሜ ተዘጋጂቶላቸዋል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
5.2K viewsማሜ, 08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 11:17:32
የጨጎማ - ጋሸና የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ተጀመረ።
ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) የመንገድ ፕሮጀክቱ መጀመር የተበሰረው የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኝ ጨምሮ የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው።
መንገዱ 44 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው ግንባታው በሀገር በቀሉ ዮቴክ ኮንስትራክሽን ይከናወናል ተብሏል።
3 ዓመት የግንባታ ጊዜ የተያዘለት የጨጎማ - ጋሸና የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ወጭ ይደረግበታል።
ዘጋቢ፡- ስማቸው እሸቴ - ኮን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
5.2K viewsማሜ, 08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 10:24:20 የሩዝ ምርትን እሴት በመጨመር ወደ ገበያ በማቅረባቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን ነጋዴዎች ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) ሩዝ በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ፣ ሊቦከምከም እና ደራ ወረዳዎች በብዛት ይመረታል፡፡ ካሁን ቀደም ሩዝ በባህላዊ መንገድ በመቀነባበሩ አርሶ አደሮችም ሆኑ ነጋዴዎች ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም እያገኙ አልነበረም፡፡
ሚዳ እምርታ በተሰኘ ፕሮጀክት በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ከሩዝ አምራች ወረዳዎች ጋር በጥምረት መሥራት በመጀመሩ አምራቾች፣ ነጋዴዎችና አቀነባባሪዎች የተሻለ ውጤት እያስመዘገቡ ነው ተብሏል፡፡
በባሕር ዳር ከተማ በዘርፉ የተሰማሩ አቀነባባሪዎች ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ አውደ ርዕይ ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ በአውደ ርዕዩ ከተገኙት መካከል ወጣት ግዛው ተሰማ አንዱ ነው፡፡ “የነጭ ወርቅ” የተባለ ሩዝ አቀነባባሪ የአክሲዮን ማኅበር አስተባባሪ ነው፡፡ በሚዳ እምርታ ፕሮጀክት ታቅፎ ስልጠናና የማቀነባበሪያ ማሽን በብድር በማግኘቱ ጥራት ያለው ምርት ለሸማቹ እንዲያቀርብ አስችሎታል፡፡ ግዛው ፕሮጀክቱ የገበያ ትስስር ስለፈጠረላቸው የተሻለ ገቢ እያገኘ እንደሆነም ነግሮናል፡፡
በዘመናዊ መንገድ የተዘጋጀው ሩዝ የተሻለ ተፈላጊነት አለው ብሏል፡፡
ወጣት ፍቅር አቻምየለህ በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ የወረታ ከተማ ነዋሪ ናት፡፡ ፍቅር በሜዳ ፕሮጀክት ያገኘችው ስልጠና ሩዝ የምግብ ይዘቱ ሳይለቅ ለተጠቃሚው እንድታቀርብ አስችሏታል፡፡
ፍቅር እንዳለችው አውደ ርዕዩ ያቀረበችውን የሩዝ ምርት ለማኅበረሰቡ እንድታስተዋውቅ ረድቷታል፡፡
አቶ በድሉ ክፍሌ በሀገር ውስጥ የማይገኙ አዳዲስ የሩዝ መፈልፈያ እና ማዘጋጃ ማሽኖችን ጥሬ እቃውን ከውጭ በማስመጣት ሀገር ውስጥ በመገጣጠም ለሩዝ አምራቾች እና አቀናባሪዎች ያስረክባሉ፡፡
እንደ አቶ በድሉ ገለጻ ሩዝ አቅራቢዎች የተቀነባበረ እና የታሸገ (ስቲም ወይም ፓርቦይልድ) የሚባለውን ሩዝ የሚያመርቱት እሳቸው በሠሩት ማሽን ነው፡፡ ሩዝ በዘልማድ ሲፈለፈል ይሰባበራል፤ የምግብ ይዘቱም ይቀንሳል ነው ያሉት አቶ በድሉ፡፡ ዘመናዊ መፈልፈያ እና ማቀነባበሪያ ማሽን በመጠቀም የሩዝ ምርትን በተሻለ መልኩ ማስተዋወቅ ይቻላል ብለዋል፡፡
በሚዳ እምርታ ፕሮጀክት የፕሮጀክት ትግበራ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ዓለም ፀሐይ እጅጉ ፕሮጀክቱ በደቡብ ጎንደር ዞን በሦስት ወረዳዎች በፎገራ፣ ሊቦከምከም እና ደራ ወረዳዎች የሩዝንና የአትክልት ምርቶችን መሰረት አድርጎ እየሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ወይዘሮ ዓለምፀሐይ እንዳሉት ፕሮጀክቱ የተሻሻሉ የሩዝ ዝርያዎችን በማስተዋወቅ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋም በምርቱ ላይ እሴት ጨምረው ለገበያ እንዲያቀርቡ እያደረገ በመሆኑ አምራቾች፣ ነጋዴዎችና አቀነባባሪዎች የተሻለ ገቢ እያገኙ እንደሆነም ነግረውናል፡፡
ሚዳ እምርታ ፕሮጀክት ለአቀነባባሪዎችና ለነጋዴዎች የብድር አገልግሎት በማመቻቸት ምርቱ በብዛት የሚቀርብበትን መንገድ እያመቻቸ እንደሆነም ሥራ አስኪያጇ ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
6.1K viewsማሜ, 07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ