2021-02-18 10:57:29
የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና የአፍሪካ ልማት ባንክ በትራንስፖርት መሪ ዕቅድ ተግባራዊነት ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡
ባሕር ዳር፡ የካቲት 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ።
ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ቼፕሮ አሞስ ኪፕሮኖህ ጋር በቀጣይ 10 ዓመታት በሚተገበረው የትራንስፖርት ዘርፍ መሪ የልማት ዕቅድ ተግባራዊነት ላይ ተወያይተዋል።
የአፍሪካ ልማት ባንክ አጋር ሆኖ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን የትራንስፖርት ሚኒስቴር ገልጿል።
በተለይም ባንኩ በኢትዮጵያ ለልማት ሥራ ከሚያዉለው 1 ነጥብ 65 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዉስጥ 31% በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ እንደሚዉል ይታወቃል።
በሌላ በኩል በልማት ባንኩ ድጋፍና ብድር በሚሰሩ የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች እና ሌሎች ፕሮጀክቶች ተግባራዊነት ላይ በሚታዩ አንዳንድ የአፈፃፀም ችግሮች ዙሪያም ተወያይተዋል።
የልማት ባንኩም የተለመደውን አጋርነት አጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ከሚኒስትሯ ጋር ተወያይተዋል።
ቀጣይ በሚኖሩ የልማት ስራዎች በተለይም ብሔራዊ የትራንስፖርት ፖሊሲን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለዉን የትራንስፖርት ዘርፍ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድን ለማሳካት ከባንኩ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል። መረጃው የትራንስፖርት ሚኒስቴር ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
2.7K viewsማሜ, 07:57