2021-02-17 11:36:19
በጋምቤላ ክልል 125ኛው የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ የካቲት 10/2013 ዓ.ም (አብመድ) በጋምቤላ ክልል 125ኛው የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዓሉ በስፖርታዊ ውድድር፣ በሥራ ጉብኝት እና በፓናል ውይይት እየተከበረ ይገኛል፡፡
የኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው እና የጋምቤላ ክልል ርእሰ መሥተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የተለያዩ የክልሉ እና የፌደራል መንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም የአካባቢዉ ነዋሪዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡
ዛሬ ጠዋት የክልሉ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ተጎብኝተዋል፤ የአድዋ መታሰቢያ ፓርክም ተሰይሟል፡፡
አዲሱ ትውልድ ከቅድመ አያቶቹ የወረሰውን የጀግንነት እና የመተባበር ባህል ዳግም በማደስ ለሀገሪቱ ሰላም እና ልማት በጋራ መረባረብ እንዳለበትም በክብረ በዓሉ ላይ ተገልጿል፡፡
የአድዋ ታሪክ በኢትዮጵያውያን የጋራ ተጋድሎ መላዉ ጥቁር ህዝቦች ድል የተጎናጸፉበት መሆኑም በመድረኩ ላይ መገለጹን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
6.6K viewsማሜ, 08:36