2021-02-14 10:16:00
ማህበረሰቡ ጤንነቱን እንዲጠብቅ ዓላማ ያደረገው የጎንደር ከተማ የጋራ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ዛሬ ተጀምሯል።
ባሕር ዳር፡ የካቲት 07/2013 ዓ.ም (አብመድ) የጋራ ስፖርታዊ እንቅስቃሴውን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ያስጀመሩት ሲሆን ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ከንቲባው ሞላ መልካሙ ማህበራዊ የስፖርት እንቅስቃሴው በአስተሳሰብ የተሻለ፣ በአካል ብቃት የዳበረ ማህበረሰብ ለመፍጠር እንደሚያስችል አስረድተው የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ቀጣይነት እንዲኖረው ትኩረት ተሰጥቶ የሚሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
የማያቋርጥ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ከተለያዩ በሽታዎች እራሳቸውን ለመከላከል በጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉም አስተያየታቸውን ለአብመድ የሰጡ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
በጎንደር ከተማ የተዘጋጀውን ህዝባዊ የስፖርት እንቅስቃሴ ያዘጋጀው የከተማ አስተዳደሩ ባህል ቱሪዝም ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ነው።
ዘጋቢ:- ሀይሉ ማሞ- ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
6.5K viewsማሜ, 07:16