Get Mystery Box with random crypto!

የጨጎማ - ጋሸና የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ተጀመረ። ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብ | Amhara Media Corporation

የጨጎማ - ጋሸና የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ተጀመረ።
ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) የመንገድ ፕሮጀክቱ መጀመር የተበሰረው የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኝ ጨምሮ የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው።
መንገዱ 44 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው ግንባታው በሀገር በቀሉ ዮቴክ ኮንስትራክሽን ይከናወናል ተብሏል።
3 ዓመት የግንባታ ጊዜ የተያዘለት የጨጎማ - ጋሸና የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ወጭ ይደረግበታል።
ዘጋቢ፡- ስማቸው እሸቴ - ኮን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m