Get Mystery Box with random crypto!

የውኃ አካል ዳርቻ ክልልን ለመወሰን በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ የባለሙያዎች ውይይት በባሕር ዳር እየ | Amhara Media Corporation

የውኃ አካል ዳርቻ ክልልን ለመወሰን በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ የባለሙያዎች ውይይት በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።
ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) በውይይቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት፣ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ፈቲያ የሱፍን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ አካላትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተሳታፊዎች ናቸው።
በረቂቅ አዋጅ ላይ የሚደረገው የባለ ድርሻ አካላት እና ምሁራን ውይይት ተጨማሪ ግብዓት ለማግኘት እና በሚሻሻሉ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃ ለመሰብሰብ ያለመ መሆኑን የተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ግዛው ተናግረዋል።
ረቂቅ አዋጁ በስድስት ክፍሎች እና በ28 አንቀጾች ተከፍሎ የቀረበ ሲሆን 23 ሙያዊ ቃላትም ትርጓሜ ተዘጋጂቶላቸዋል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m