Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-24 16:18:55 ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ነጥብ ነው!

መቼም ፈቅደንም ሆነ ተገደን "በአማራ ፖለቲካ ውስጥ አለንበት!" እስካልን ድረስ ፤ ቃላቶቻችን ጥይት ሆነው የመግደልም ሆነ መድሀኒት ሆነው የመፈወስ ኃይል እንዳላቸው መገንዘብ በእጅጉ ያስፈልገናል፡፡

ፖለቲካዊ ተግባቦት/Political Communication ከስሜት በዘለለ ፥ ፖለቲካዊ አላማንና ግብን ከማሳካት አኳያ ካልተቀነበበ የሚወልደው አደጋና ኪሳራም የትየለሌ ነው፡፡

በተለይ ደግሞ በሳይበሩና በሚዲያዎች አካባቢ ፖለቲካዊ ሀሳቦቻችንን የምናቀርብና ለተግባቦታዊ ስርአቱ ቅርብ የሆንን ሰዎች  ፥ በዚህ ረገድ የመጣንበትን ገምግመን ራሳችንን ልናርም ፣ ልናበቃና ልንነቃ ይገባል ባይ ነኝ፡፡

አንዳንድ ወገኖቻችን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ፥  ሁኔታና ጊዜው ስለፈቀደላቸው ብቻ  ፥ በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በፅሁፍ ፣ በድምፅና  በተንቀሳቃሽ ምስል የሚያሰራጯቸው አደገኛ ንግግሮች ፥  ተፅዕኗቸው እነሱ ጋር ባይደርስ እንኳ ሌላ ቦታ ገጀራ ፥ ጥይት ፣ እሳት ፣ መከራና ግፍ ሆነው ፥ "እንታገልለታለን" በምንለው ህዝብ ላይ እንደበረዶ ይዘንባሉ፡፡

የምንታገላቸው ፅንፈኛ የፖለቲካ ሀይሎች (ቡድኖች) እነዚያን ሀላፊነት የጎደላቸውና የአማራ ህዝብ መሠረታዊ የትግል ግብና አላማ ያልሆኑ የግለሰቦች  ሀሳብና ንግግሮች እያስተጋቡም " እነሱኮ አላማቸው ይኸ ነው!" ሲሉ እንደህዝብ አቋም ወስደው  ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ያደርጋሉ ፥ ይቀሰቅሳሉ ፥ ለህዝባችን ተጨማሪ ጠላት ለመፍጠር ይተጋሉ፡፡

በተለይ ደግሞ የምንታገለው "የጥላቻ ጡጦ ጠብተው ያደጉና በህዝብ ስልጣን ላይ ያሉ የፖለቲካ ሀይሎችን" እንጂ ህዝብን እንደህዝብ ፈርጀን አለመሆኑን ማጤንና ማስረዳት ያሻል፡፡ ሹምምንቱንና ፖለቲከኛውን እንዳሻን መተቸት ፥ መዝለፍ መቃወም መብታችን ነው፡፡ ሆኖም እነሱ ሴራ ደርተው ለስንፍናቸውና ለወንጀላቸው መደበቂያ የሚያደርጉትን የወጡበት  ፥ ማህበረሰብ ወይም ግለሰባዊ አምልኮዎች (ሀይማኖቶች ) በተመለከተ በጅምላ ለሴራ የሚመነዘር ፖለቲካዊ ንግግር ማድረግ ፥ ፈፅሞ ጎጂና በገዛ ወገኖቻችን ላይ ተጨማሪ መከራ የሚያዘንብ መሆኑን በሚገባ በመረዳት ተጠንቅቀን መጓዝ ይኖርብናል፡፡

ይኸው ነው!
5.0K viewsedited  13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 15:45:15 ልድገመው ፦

በግሌ ስለፋኖም ሆነ ልዩ ሀይሉ የሚሠማኝ ይኸው ነው!

በትግል ላይ የሰነበተውና አሁንም በግንባር ላይ ታጥቆ የሚገኘው ፋኖ ፥ እንደህዝብ ያለንበትን አሳሳቢ የህልውና አደጋ ከተረዳና ለመታገል ቁርጠኝነቱ ካለው ፥ ግራም ነፈሰ ቀኝ ያለው አማራጭ አንድና አንድ ነው!



የታጠቁ ሀይሎቹን ይዞ በቋሚነት ወደሚንቀሳቀስበት የትግል  መሬት መጓዝና መስፈር!  ደጋፊና አባላቶቹም መስመሩ በተለየ ግልፅ መንገድ ይደግፉት ፥ ይቀላቀሉት!

ከተማና መሀል አገር ሆኖ ግን ሁልጊዜ "ተከበበ" እያልን መኖራችን ይቀጥላል እንጂ ፥ መክበባቸውም ሆነ ትጥቅ ለማስፈታት መንቀሳቀሳቸው ፈፅሞ አይቀሬ ነው!

ያ ካልሆነ ግን የሁልጊዜ   አጀንዳችን ፥ "ህዝብን ከከበባ ይታደጋል" ተብሎ የታመነበትን ፋኖ "  ...ተከበበ ፥ ታሰረ ፥ ትጥቅ ተቀማ ፥  ...! " የሚል ብቻ ሆኖ ፥ ራሳችንን እያደከምን  መጓዛችን ይቀጥላል!

ይህ ከሚሆን ደግሞ በየቤቱ ሆኖ እንደህዝብ  የሚደረገው ትግል አካል ሆኖ የሚጠበቅበትን ቢወጣ የተሻለ ይሆናል!

ልዩ ሀይሉም መወሰን ያለበት ፥ ከዚህ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ውሳኔ ነው ብዬ አምናለሁ!

ትጥቁን እንደያዘ ሚሊተሪውን አውልቆ ወደህዝቡና ቤተሰቡ ተቀላቅሎ ይታገል!  ዙሮ ዙሮ የተፈራውና የገመትነው ሁሉ እየተፈፀመ መሆኑ የተረጋገጠ ነውና በየአካባቢው ሆኖ ለቀጣይ የተቀናጀ ህዝባዊ ትግል ራሱን ያዘጋጅ!

ያ ካልሆነ ደግሞ የራሱን እዝና የአደረጃጀት ሰንሰለት ዘርግቶ ገዢ ቦታ ይዞ የሚታገልበትን አማራጭ ማበጀት አለበት!

አለበለዚያ ግን በሴራ የፖለቲካ አመራሮች ግራ እንደተጋባ ዩኒፎርም ለብሶ ከወዲያ ወዲህ   እንገፍ እንገፍ ማለቱን ከቀጠለ ፥  እጣፋንታው ተለቅሞ ማለቅና በጠላት እጅ መውደቅ ይሆናል!

አሁን ባለው መንገድና ነባራዊ ሁኔታ ፥ ሁለቱም ሀይሎች ለህዝቡ ተጨማሪ ጫና ከመፍጠር ውጪ ጫናውን ወደሚያቀል የትግል ስርአትም ሆነ ተደራዳሪ ኃይል ወደመፍጠር  ሊገቡ አይችሉም!

ሳጠቃልል ፦ እኩልነት ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ የሰፈነባት ፥ አሳዳጅና ተሳዳጅ የሌለባት ብሎም አንዱን ልጅ ሌላውን የእንጀራ ልጅ የማታደርግ ሀገርና ስርአትን ለመፍጠር ፤ አንድም በሰላማዊ የሀሳብ ትግል ያለበለዚያ ደግሞ "በአፈሙዝ እታገላለሁ" የሚለው ሀይል ፥ በራሱ ላይ መቀለዱን ትቶ ወቅቱን ወደሚመጥን "መረር" ወዳለ ትግል መግባት ካልቻለ ፥ በተያዘው አካሄድ በራስ ላይ መከራን ከማክፋት የዘለለ ስንዝር መራመድ አይቻልም !

ይኸው ነው!
4.8K views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 22:55:57 ፍዝ ተመልካች ስትሆን ተመሳሳይ አክተሮች ይተውኑብሃል!

ደበበ እሸቱ የሰላምም የጦርነትም ሌክቸር እንዲሰጥህ ያደረከው ፥ ከመቶ ሚሊየን በላይ ሆነህ ፥ ሀገሪቱን መቶ የማይሞሉ ካንሰሮች በተመሳሳይ አዙሪት ውስጥ እየተሽከረከሩ እንዲፈነጩባት ምቹ ሁኔታ ፈጥረክ በመስጠትህ ነው!

በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የእያንዳንዳችን አስተዋጽኦ አለበት!

ብሮ ፦ አልሰማኸውም እንዴ ዛሬ << ስንዋጋም ከልብ ነው ፤ ስንታረቅም ከልብ ነው! >> ብሎ ሲሳለቅብህ?

አንተኑ አዋግቶ ፥ አጫርሶና አፋጅቶ በሀዘንና በሰቆቃህ ላይ " ከልብ ተራረቅን ይሉሃል!

እኛ ደግሞ ተላልቀን ፥ ተራርቀንና ተሸማቀን ፥ ዛሬም በብስቁልናና በመከራችን ላይ ፥ የመከራ ምንጮቻችንን እያፀደቅን ስንናከስ ቀጥለናል ...!

ህዝብ ለህዝብማ ከልብ እንዲተራረቅ ፥ እንዲቀራረብና እነሱ የዘሩትን የጥላቻ ትርክት ነቅሎ አብሮነቱን እንዲያስቀጥል ፈፅሞ አይፈልጉም !

ምክንያቱም መደበቂያ ዋሻቸው ነዋ!

"አብይ አህመድ አለምአቀፍ ወንጀለኛ ነው!" ስትል " ይህ የኦሮሞ ጥላቻ ነው!" ብሎ የሚደበቀው በምስኪኑ የኦሮሞ ህዝብ ነው፡፡

"ጌታቸው ረዳ የትግራይ ወጣቶችን አስፈጅቶ የህዝብ ስልጣን ላይ ያለ ወንጀለኛ ነው!" ብለህ ብትታገለው ፤ " ይህ የትግራዋይ ጥላቻ ያሰከራቸው የአሀዳውያን ዘመቻ ነው!" ብሎ ከለላ የሚያገኘው በዚሁ በሚያናክሰው መከረኛ ህዝብ ነዋ!

የሴራ ፖለቲከኞቹ በህዝብ ፍቅር የሚከስሩና የሚከስሙ ሲሆኑ የሚለመልሙት ደግሞ በሚዘሩት የጥላቻ ፍሬ ህዝብ ለህዝብ ተናክሶ ፥ የሴራ ወጥመዳቸው ሰለባ ሲሆን ብቻ ነው!

ሌላ ሌላውን ተወው "ድራማ" ነው!

ስር-ነቀል የአስተሳሰብ ለውጥና የትግል ጅማሮ ውስጥ መግባት ካልቻልን ፥ የኢትዮጵያና የህዝቦቿ እጣፋንታ ከዛሬው የነገው እጅግ ይከፋል!

ሠላም!
4.9K viewsedited  19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 22:12:48 የተሻለ ሀሳብ ዋጋ በማያወጣበት ሀገር ውስጥ ሁሉን ነገር ለማድረግ የሚያስችልህ ስልጣንና ገንዘብ ብቻ ነው!

ስልጣንና ገንዘብ ካለህ ፥ " ምሁር ፥ አዋቂና የሁሉ ነገር አድራጊ ፈጣሪ" ተደርገህ ትቆጠራለህ፡፡ የሚያስቅ ሳትናገር ይሳቅልሀል ፤ ለማይረባ ሀሳብህ ይጨበጨብልሀል ፥ አጀብህና ተከታይህ ብዙ ይሆናል፡፡

የተሻለ ሀሳብ ማራመድና ወደተሻለ ከፍታ መውጣት አይታሰብም፡፡ "ባለህበት እርገጥ ብቻ! በአንድ ክብ ዙሪያ መሽከርከር....!

በአስመሳይነት ፥ በአላዋቂነት ፥ በክፋትና በሴራ የተካኑት የትውልዱን ነገ ከጫማቸው ስር እየተረገጡ ሲጫወቱበት መመልከት ብቻ!

በዚህ አይነቱ አውድ "ብዬ ነበር...!" ማለት እጣፋንታህ ይሆናል!

ከዚህ አውድ ለመመንጠቅ ያለው ብቸኛ መንገድ ፤ ከተናጠል ለቅሶና ቁዘማ ወጥቶ ፤ በተደራጀ ሀሳብና አላማ ፤ በህብረትና በአንድነት መራራ ትግል ማድረግ ብቻ ነው!
4.5K views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 22:10:25 ...የዛሬው የሠላም ድስኩር ፤ ለነገው ጦርነት የመክፈቻ ምዕራፍ ነው!

በተለይ በተለይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ "አክተር" የሚባሉት ሀይሎች የተወከሉባቸው የኦሮሞ ፣ የአማራና የትግራይ ህዝቦች ፤ ወደራሳቸው በመመልከት ፤ የሴራ ፖለቲከኞችን መደበቂያ ዋሻ ለማሳጣትና የተሻሉ መሪዎችን ከአብራካቸው ለማውጣት ብሎም የሀገሪቱን ነገ ለመወሰን ፥ ከዚህ ካለንበት ወቅት የበለጠ የመማሪያ እድል የለም!

..አስከሬን በቅጡ አልተሰበሰበም ፤ ሌላው ቀርቶ መርዶ እንኳ በቅጡ በክብር አልተረዳም ፥ እልፍ የትግራይ ፣ የአማራ ፣ የኦሮሞ ፣ የአፋር ፥ ... እናቶች ልጆቻቸውን ዛሬም "በር በር" እያዩ እየጠበቁ ነው ፤ ....!

ህዝብ ያልቃል ፤ የሴራ ፖለቲከኛው ጥቅሙን ተደራድሮ ይታረቃል! ዞሮ ደግሞ "ክተት ፣ አንክት" ባለበት አንደበቱ ስለሰላም አስፈላጊነት እየሰበከህ ልብህን ያደርቃል!

ህዝብ ፍዝ ተመልካች በሆነበት ሀገር የፖለቲካ ጨዋታው ህግ ይህ ነው!

አብረሀቸው እንደቤተሰብ ከኖርካቸው የአማራ ፥ የትግሬ ፥ ...ወዘተ ጎረቤቶችህ ጋር ሁሉ ሆድና ጀርባ አድርጎህ ፤ " ጁንታና የቀን ጅብ ብለህ ጥራቸው!" ብሎ የቀሰቀሰህና ያዘመተህ የሴራ ፖለቲካ ሊቅ ፥ ዛሬ ስለሰላም ሲዘምር ፥ ዛሬ ስለጦርነት አስከፊነት ሲሰብክህ ፤ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሰው ቀርቶ ችግኝ ያስጨፈጨፈ አይመስልም!

ህዝብ "ለምን? ከዚያስ?" ብሎ መጠየቅ ካልጀመረ ፤ ለሴራና ለጥላቻ ፖለቲከኞች መደበቂያ ዋሻ ከመሆን ካልተቆጠበ ብሎም "በቃ!" ብሎ የትውልዱን የተሻለ ነገና ሀገር ለመፈለግ ካልተነሳ ፤ የዛሬው የሰላምና ፌሽታ ድግስ የነገው ሌላ የእልቂት ድግስ አቀባበል መሆኑን አስረግጨ እነግርሃለሁ!
4.7K views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 18:57:55 "መሪ" መፍጠር ስለምን አልቻልንም?

ምክንያት - 1-

አብዛኛው "ኤሊት" ተብዬ መሪ ለመሆንና ዘውዱን በጉያው ይዞ ራሱን ለማንገስ ስለሚሻኮት ፥ መሪዎችን የመፍጠር ቢፈጠሩም ደግሞ የማክበር ባህላችን እየተሟጠጠ "መሪ አልባነትን" እጣፋንታችን ወደማድረግ እየተጓዝን ነው!

መሪውን የሚያከብርና በስራው ብቻ የሚመዝን ተመሪ (የፖለቲካ ማህበረሰብ) ካልተፈጠረ ሁሉም ነገር "ውሃ ቢወቅጡት ...!" ነው!

ምክንያት -2-

ውስጣዊ የፖለቲካ ትምምን የተፈጠረበትና በጋራ ኮዙ ላይ የጋራ አመለካከት ያለው የፖለቲካ ማህበረሰብ መገንባት ያለመቻሉ!

ምክንያት -3-

አውራጃዊ (የጎጥ) አስተሳሰብ ከጋራ ጉዳያችን ከፍ ብሎ መስተጋባትና ይህን ውጥረት ለማርገብ መሪዎች በኮታ ድልድል እንጂ በብቃትና በእውቀት ተመስርተው መመረጥ አለመቻላቸው!

ምክንያት - 4-

መሪዎችን በቡድናዊ የጥቅም ሰንሰለትና በፖለቲካ ታማኝነት ላይ ብቻ ተመስርቶ የመሠየም የላሸቀ የፖለቲካ ልማድ ተጠናክሮ መቀጠሉ!

ምክንያት -5- የመካድ ስነልቦናዊ ተፅእኖ

ከዚህ ቀደም በተለያዩ መሪዎቻችን ያስተናገድናቸው ክህደቶችና እኩይ ተግባራት ሳቢያ ሁሉንም በአንድ ቅርጫት የመክተትና በጅምላ ተጠራጣሪ የመሆን ስነ-ልቦና እየገነገነ መምጣቱ!
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
ግዙፉን አዕምሯዊ ፀጋ የተጎናፀፉ ምሁራን ይዘን ጠንካራና ብቁ የሆኑ መሪዎችን መፍጠር ላለመቻላችን ብዙ ብዙ ነጥቦች ማንሳት ቢቻልም ፥ እስኪ የእናንተንም ሀሳብና ምክንያቶች አክሉበትና እንወያይበት! የየድርሻችንንም እንውሰድ!

ለሁለንተናዊ ውድቀቱም ሆነ ለስኬቱ እያንዳንዳችን በልካችን አበርክቶት አለን!
2.5K views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 17:21:22 ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ የወለጋ ንግግር የተቀነጨበ ፦

"እናንተ ወደኛ ኑ እንጂ ለሌላው በጭራሽ አታስቡ።ሌላው ያወራሉ ፤እኛ ግን ለኦሮሞ ነው የምንሰራው።እየሰራን ነው።ይሔ ብልጽግና የኦሮሞ መንግስት ነው።በዚህ ወቅት ስልጣኑ ከእጃችን ከወጣ በመቶ አመት ውስጥ አናገኘውም።"

"በሰሜን በኩል ያሉት እያንገራገሩ ነው። እኛ ተደራጅተን እነሱን ማንበርከክ ካልቻልን እኛ ስልጣን ላይ ያለነው ብቻ ሳይሆን የምንጎዳው ኦሮሞ የሆነው ሁሉ ነው።..."

"በወለጋ በርካታ የተፈናቀሉ አሉ። እነዛ የተፈናቀሉት ለኛ የሚተኙልን ይመስላችኋል!?"

"ስለዚህ የብልጽግና መንግስት አትጠራጠሩ።የኦሮሞ ነው።የምን ሰራውም ለኦሮሞ ነው። እናም እናንተ ወደኛ ኑ እንጂ ለሌላው በጭራሽ አታስቡ! ይስተካከል"

"ወደኛ መምጣት፣ እኛን ማዳመጥና መደማመጥ ካልቻልን፤ ስልጣናችንን ካጣን እኛ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ኦሮሞ የሆነ ሁሉ ለከፉ ችግር ይዳርጋል"

// አብይ አህመድ አሊ - ከሰሞኑ በወለጋ ያደረገው ንግግር//
4.7K views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 17:38:11 ኢትዮጵያ ልትኖር የምትችለው ኢትዮጵያውያንን መምሰል ስትችል ብቻ ነው!

በኦሪት ዘመን አስተሳሰብ ላይ የሚገኙት አብዛኛዎቹ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ዘወትር በየመድረኩ << ... ምስራቅ አፍሪካን ማካለል ባንችል ፥ ኢትዮጵያን ኦሮሞን እንድትመስል አድርገን ጠፍጥፈን እንሰራታለን! >> የሚል ቅዠት ከአፋቸው አይጠፋም፡፡

እንዲህ አይነቱ የቅዠት ፖለቲካስ ወደፊት የሚያስጉዝ ይመስላችኃል? ይህ አይነቱ በህዝብ ጉያ ተወሽቆ በቅዠት አለም እያስጨበጨቡ ቡድናዊ ፍላጎትን ለማሳካት የመሮጥ አባዜ ለትልቁ የኦሮሞ ህዝብ ጠላት ከማብዛትና ጥቁር የሀፍረት ታሪክ ከማሸከም ውጪ የሚጠቅመው ነገር አለ ወይ ?

ጠዋት ማታ የትርክት ጡጦ ጠብቶ በጎለመሰው ስብእናችሁ "ነፍጠኛ ፥ ወራሪ ፥ አሀዳዊ ፣ ደፍጣጭ ፣ ..!" እያላችሁ የምታብጠለጥሉት የአማራ ህዝብኮ " እኩልነትና ፍትህ ይስፈን! ለሁላችንም እኩል የሆነች እናት ሀገር ትኑረን!" እንጂ " አማራን የምትመስል ኢትዮጵያ ትገንባ!" አላለም!

ለማንኛውም ፦ ኢትዮጵያ መምሰል ያለባት ኢትዮጵያውያንን ብቻ ነው፡፡ ሊሰፍንባት የሚገባውም ፍትህና ርትዕ ብቻ ነው፡፡ " ማንም የበላይ ማንም የበታች ያልሆነባትን ፍትሀዊና ዴሞክራሲያዊት ሀገር እንገነባለን!" በሚል አስተሳሰብ እስክትታነፅና እኩልነትን እስትቀበል ድረስ መዶሻው አያባራልህም!

ጠማማ ብረት እኩል ሆኖ የሚስተካከለው ፤ በእሳት አግለህ በመዶሻ ስትቀጠቅጠው ብቻ ነው!

ያ ካልሆነ ግን ፦ ለሁላችንም እኩል መሆን ያልቻለች ሀገር ደግሞ የማንኛችንም እንዳትሆን መደረጓ ሳይታለም የተፈታ ነው!
1.1K viewsedited  14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 16:42:09
ለአማራ ሕዝብ ድምጽ በመሆናቸው ብቻ ፤ የፋሺስቱ አገዛዝ በግፍ ያሠራቸው ጋዜጠኞች!

ጋዜጠኛ(መምህርት) መስከረም አበራ
ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው
ጋዜጠኛ ገነት አስማማው
ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ
ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው
ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ
ጋዜጠኛ በየነ ወልዴ
ጋዜጠኛ ሰናይት አያሌው
ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ
ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ
ጋዜጠኛ ኤሊያስ ደባስ (ዛሬ የታሰረ)

ፍትህ ለህሊና እስረኞቹ!
1.7K views13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 16:04:57
የአሻራ ሚዲያ ስራ አስኪያጅ እና ጋዜጠኛ ኤልያስ ደባስ ታፈኑ!
         
የአሻራ ሚዲያ ስራ አስኪያጅ እና ጋዜጠኛ ኤልያስ ደባስ በዛሬው ዕለት በባህርዳር ከተማ በመንግሥት አፋኝ ኃይሎች ተይዘው መታሰራቸውና በአሁኑ ሰአት በባህርዳር 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ታውቋል።

ሳምንት ባልሞላ ዜ የዛሬውን ጨምሮ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ  ከ10 ያላነሱ በማንነት አማራ የሆኑ ጋዜጠኞች በመንግሥት አፋኞች ተይዘው ታስረዋል።

መረጃውን ያደረሰን ኃይላችን አወቀ ነው፡፡
2.0K views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ