Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 46

2022-08-10 20:13:53 ክልልኛው ዘፈን ለምን?

በኢትዮጵያ ደረጃ ብያኔ እንስጠው ካልን ክልል ማለት የሴራ ፖለቲከኞች የህዝቡን ሳይሆን የራሳቸውን ጥቅምና ፍላጎት አስልተው የሚያሰምሩት ግለሰባዊ መስመር ነው፡፡

የወሎ ሰሞንኛው አጀንዳ ሁለት ክንፍ አለው፡፡ አንደኛው ምድብ ፖለቲካዊ ግብ ያለው ከ1983 ዓ.ም በፊት ቀደም ብሎም የሚንቀሳቀሰው በጥላቻ ትርክት የናወዙት ፦ የኦነግ ፣ የህወሓትና ሌሎች በመንግሥት ስርአት ውስጥ ያሉ ፅንፈኛ ሀይሎች የሚገኙበት ሲሆን በሁለተኛው ምድብ ደግሞ እዚሁ በአማራ ክልል አጥር ውስጥ ያለ ከላይ የተጠቀሱት ሀይሎች አላማ ተሸካሚና የጥቅም ፍላጎት ያለው ፣ የስልጣን ጥሙን ለማርካት ተቅበዝባዥ ብአዴናዊ ክንፍ ፣ ሀይማኖትን በሽፋንነት የሚጠቀም ቡድን ፣ ጥቅምና ጉዳቱን ብሎም ፖለቲካዊ አንድምታውን ሳያውቅ በሌሎቹ ፕሮፓጋንዳ ተመርቶ እንደበቀቀን የሚያስተጋባ ሀይል ፥ ..ወዘተ የተካተቱበት ነው፡፡ የተፅዕኖ ደረጃቸው ግን ተያያዥነት አለው፡፡

እንደው ስለሁለተኛው የስልጣን ጥመኞች ቡድን የሚያውቁና የታዘቡ እንዲረዱት ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ህወሓት አካባቢውን ከመውረሩ ቀደም ብሎ ወሎ ውስጥ በተለይ ደቡብ ወሎ ውስጥ ባደራጁት ቡድን አማካኝነት የወሎን የክልልነት ጉዳይ በተመለከተ ፕሮፖዛል ነድፈው ፣ በአምስት ዞኖች የተከፈለ የክልላዊ መዋቅር ንድፈ ሀሳብ አዘጋጅተው ፕሬዝደንትና ምክትል ፕሬዝደንት ራሳቸውን ሹመው ፤ ለየዞኖቹ ሁሉ አመራርና ተሿሚ ደልድለው በግልፅ ሲንቀሳቀሱበት ነበር፡፡

የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደርና ከጀርባ ያለው የኦሮሚያ ክልል ኦነጋዊ ክንፍ ፥ ይህን አላማ በመሪነት ደረጃ ለሚመሩትና ለሚያስተባብሩት በርካቶች እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ አዲስአበባ ላይ የመኖሪያ ቤትና አክሲዮኖችን በመግዛት ረብጣ ገንዘብ በአካውንታቸው በመቆለል ለአጀንዳ ፈፃሚነታቸው ወሮታውን መክፈሉን በወቅቱ ውስጥ ለውስጥ ሲነገር ሰምተናል፡፡ የመረጃውን ተአማኒነት የማጣራቱን ስራ "ለፀረ-ሙስና ኮሚሽን" ትቸዋለሁ!

ከዚያ ባለፈ ግን የወሎ አማራ አዎ አማራ ተብሎ ታርዷል ፥ በብአዴናዊው አስተዳደር የመልማት ፀጋው ተገፎ ኖሯል ፣ እንደአማራ የደረሰውን ግፍ ሁሉ እየተቀበለ ይገኛል፡፡ ነገርግን ህዝቡ ተከፋፍሎና በትንሽ ክልል ተሸብቦ ፥ " አንዳቸውም ጥቅምና ፍላጎቶቹ ይከበሩለታል" ብሎ ማሰብ ሞኝነት ወይም አላዋቂነት ነው፡፡

ከስያሜ ለውጥና ከስልጣን ጥመኞቹ ሹመት ብሎም በሀሰተኛ የጥላቻ ትርክት ከናወዙት የሴራ ፖለቲካ ነጋዴዎቹ አትራፊነት ውጭ ፥ ህዝቡ የተለየ ፀጋ ሊፈስለት ነውን? የተለየ የተወካዮች ምክር ቤት ተወካይ ሊኖረው ነውን? ስርአት ሰራሽና መዋቅራዊ ግፉን ለማስቀረት የተለየ ህገ-መንግስት ማርቀቅ ይችላልን? ሀገሪቱ አሁን ካላት ወይም ከምትበጅተው የበጀት ቀመር ውጪ ክልል በመሆን የሚዘንብ ነገርስ ያገኝ ይሆንን? በፍፁም !

እንደውም ቅዠታቸው እውን ቢሆን ኦነጋዊው ቡድን በዚህ ህዝብ ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ነገር ሳስብ ይሰቀጥጠኛል!

እናማ እያንዳንድህ የተወረወረልህን አጀንዳ ሳታላምጥ ከመዋጥ ይልቅ "ለምን እንዴት?" ብለህ መመርመርን ልመድ!
8.2K viewsedited  17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 22:14:07
ስታደምጡት "ውርርር... ንዝርርር... እርርርር...!" የሚያደርግ ድብልቅልቅ ስሜት አልተሰማችሁም?

#ሼር
7.0K views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 20:03:47
5.9K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ