Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethpress — Ethiopian Press Agency/አማርኛ / E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethpress — Ethiopian Press Agency/አማርኛ /
የሰርጥ አድራሻ: @ethpress
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.66K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-14 12:07:40
የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም በስደተኞች ጉዳይ ላይ በተዘጋጀው የኢጋድ-ኢኤሲ የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዩጋንዳ ገቡ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ተቋም(ኢኤሲ) በስደተኞች ጉዳይ ባዘጋጁት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ዩጋንዳ ገብተዋል።

ሚኒስትር ብናልፍ ኢንቴቤ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በዩጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር እፀገነት በዛብህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በስደተኞች ጉዳይ ላይ በተዘጋጀው የኢጋድ-ኢሲኤ የሚኒስትሮች ጉባኤ በባለሙያዎች ደረጃ ትናንት በዩጋንዳ መጀመሩ ይታወቃል።

ባለሙያዎቹ የመከሩባቸውን አጀንዳዎችም ለሚኒስትሮች ስብስባ ያቀርባሉ ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
558 views09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 11:11:44 በኢፕድ ስልጠና ማዕከል ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ
በዛሬው እለት ለሚኒስቴሩ ሰራተኞች የሚሰጠው ስልጠና ተጀምሯል
****
(ኢ.ፕ.ድ)

ላለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የስልጠና ማዕከል ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል።

የማዕከሉ ስልጠና በዛሬ እለት ቀጥሎ ለሚኒስቴሩ ፈጻሚ ሰራተኞች እየተሰጠ ይገኛል።

በኢፕድ የስልጠና ማዕከል “ትጋት፣ ዕውቀት፣ ፈጠራና ትብብር ለውጤት” በሚል መሪ ሀሳብ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች የተሰጠው ስልጠና ለሶስት ቀናት በተለያዩ እውቅ አሰልጣኞች የተፈጸመ ነው።

ዶክተር ምህረት ደበበ፣ ዶክተር ወዳጄነህ መሀረነ፣ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ፣ የአሻጋሪ ኮንሰልቲንግ መስራች ወይዘሮ መቅደስ ገብረወልድ ስልጠናውን ለአመራሮች ሰጥተዋል።

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር አንተነህ ተስፋዬ እንደተናገሩት፤ ሚኒስቴሩ የተሻለ አቅምና ገጽታ እንዲኖረው ለማድረግ በኢፕድ ያገኙት ስልጠና በአይነቱ ለየት ያለና ለተሻለ የሥራ አፈጻጸም ወሳኝ ነው።

ከአመራር እስከ ባለሙያ ድረስ በስልጠናው መሳተፉ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት ውጤታማ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ሌሎች አመራሮች በበኩላቸው፤ በኢፕድ ስልጠና ማዕከል ያገኘት ስልጠና ተቋማቸውን ለመገንባት ትልቅ አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

ኢፕድ በስልጠና ማዕከሉ ከዚህ በፊት በተለያዩ የስልጠና ርዕሶች ዙሪያ ከ70 በላይ ለሚሆኑ ለፌዴራልና ለክልል ተቋማትና የግል ድርጅቶች በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ ተመሳሳይ ስልጠናዎችን በመስጠት አስመርቋል።

በአሁኑ ወቅትም የልማት ባንክ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ የሚኒሊክ ሆስፒታል፣ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን እና ቡናና ሻይ ባለስልጣን አመራሮች እና ሠራተኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አጫጭር ስልጠናዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ።

በሳሙኤል ወንድወሰን
785 views08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 11:11:41
634 views08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 10:45:12
ለሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና እየተዘጋጁ መሆኑን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ገለጹ
ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በበይነ መረብ ተመዝግበዋል
******************
(ኢ ፕ ድ)

ለሁለተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች የሚካሄደው የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና በትምህርት ይዘት እና በስነልቦናም ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ኢፕድ ያነጋገራቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች አስታወቁ።

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ በበኩሉ፤ በቅድመ ዝግጅት ስራው ከ869 ሺህ በላይ 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈታኞች በበይነመረብ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=102437
747 views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 10:44:07
በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች በመጪው ዓመት ስራ ይጀምራሉ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ስራ አቁመው የነበሩ አራት ዩኒቨርሲቲዎች በመጪው መስከረም ወር 2016 ዓ.ም ስራ እንደሚጀምሩ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሀ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በመጪው ዓመት በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=102438
635 views07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 10:43:30
ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች የመሬት መንሸራተት ሊገጥማቸው እንደሚችል ኢንስቲትዩቱ አሳሰበ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

ሰሞኑን በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚጠበቀው ከባድ ዝናብ በተለይም ባሳለፍናቸው ቀናት በተከታታይ ዝናብ በማግኘት ላይ በሚገኙ ቦታዎች የአፈር ውስጥ እርጥበት መብዛት፣ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች አፈር መሸርሸርና የመሬት መንሸራተት ችግሮችን ሊያስከትል ስለሚችል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

እየቀጠለ ባለው ዝናብ በሚቀጥሉት ሰባት ቀናት በክረምት ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ .....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=102408
578 views07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 10:34:26
14 የጁስ ማምረቻ ፋብሪካዎች በጊዜያዊነት ስራ እንዲያቆሙ ተደረገ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የምርት ሂደታቸው ላይ የተለያየ ችግር የተገኘባቸው 14 የጁስ ፋብሪካዎች በጊዜያዊነት መታገዳቸውን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ።

የምግብ ደህንነት ቀን በኢትዮጵያ ለአራተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት አማካኝነት ሲከበር የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ስሜ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የምርት ሂደታቸው ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=102401
730 views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 09:52:17
የሰኔ 7 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ
858 views06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 18:36:36 "የአማራና የትግራይ ክልል ህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንሰራለን"
-የሁለቱ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች
******
(ኢ ፕ ድ)

የአማራና የትግራይ ክልል ህዝቦችን የእርስ በእርስ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከርና ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንደሚሰሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልዑክ በባህርዳር ከተማ በመገኘት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት ከአማራ ክልል አመራሮችና የህዝብ ተወካዮች ጋር አካሂደዋል።

በዚሁ ጊዜ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት በሁለቱ ህዝቦች መካከል የወንድማማችነት ስሜት ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።

“የህዝባችን ፍላጎት ሰላም ነው፣ የህዝባችን ፍላጎት ተከባብሮ መኖር ነው፣ አብሮ መነገድ ነው” ያሉት አቶ ጌታቸው፤ የህዝቦች የቀደመ ግንኙነት እንዲመለስ የመሪዎች ቁርጠኝነት ያስፈልጋል ብለዋል።

“ባህር ዳር መገኘታችን የተከፈተውን በር አስፍተን፣ ሁሉም አይነት ሰላማዊ እንቅስቃሴ በሁለቱም ወገን የሚካሄድበት ሁኔታ ለመፍጠር ነው“ ብለዋል።

የመገናኛ ብዙሃንም ጥላቻን ሳይሆን ሰብዓዊነትን መሰረት አድርገው መስራት እንዳለባቸው ያሳሰቡት አቶ ጌታቸው የአማራ ክልል አመራሮችም የሁለቱ ክልል ህዝቦች ወደ ቀደመ ግንኙነታቸው እንዲመለሱ እያደረጉ ላለው እንቅስቃሴ ምስጋና አቅርበዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸው ህዝብ ሰላምን አጥብቆ እንደሚፈልግ ገልጸው ለሁሉም ነገር መሰረቱ ሰላም መሆኑን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል አመራር ከህዝቡ ጋር በመሆን የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ሰላምና በጋራ አብሮ ማደግ በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል።

በሁለቱ ክልሎች መካከል ትራንስፖርት ተጀምሮ ህዝብ ለህዝብ መገናኘትና አስፈላጊው የንግድ ልውውጥ መካሄድ እንደሚገባው አስረድተዋል።

ይህ እንዲፋጠን ደግሞ አሁን ላይ ህዝብን እየመሩ ያሉ የሁለቱ ክልል አመራሮች ከፍተኛ ሃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ዛሬ የተደረገው ግንኙነት የመጨረሻ ሳይሆን በየደረጀው መውረድ የሚገባውና ለዘመናት በጋራ የኖሩትን የሁለቱን ክልል ህዝቦች ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ ያለመ ነው ብለዋል።

በአማራ ክልል በኩል የህዝቦች ግንኙነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ አስፈላጊው ስራ ሁሉ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች የሁለቱ ክልል ህዝቦች ግንኙነት ወደነበረበት እንዲመለስና የተጀመረው የሰላም ግንኙነት የፀና ለማድረግ ባህር ዳር መጥተው ውይይት በማድረጋቸው ምስጋና አቅርበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የክልሎቹ አመራሮች የተጀመረውን ሰላም ማጽናትና ለህዝቦች አንድነት መትጋት አለባቸው ብለዋል።

ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ወይዘሮ የህዝቡ ጥላካሳ ለህዝቦች በጋራና በሰላም አብሮ መኖር በክልል መሪዎች የተጀመረው ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከልብ በመነጨ መንገድ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የአማራና የትግራይ ህዝብ በዘርፈ ብዙ መስተጋብሮች ለዘመናት ተሳስሮ የነበረና ወደ ፊትም አብሮ የመኖር እጣ ፈንታ ያለው እንደሆነ የገለጹት አቶ ስማቸው ንጋቱ ናቸው።

''ለዘመናት ተሳስሮ የኖረን ህዝብ መበጠስ አይቻልም'' ያሉት አቶ ስማቸው መሪዎች የህዝቡን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ስራ መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
1.4K views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 18:36:33
1.2K views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ