Get Mystery Box with random crypto!

የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም በስደተኞች ጉዳይ ላይ በተዘጋጀው የኢጋድ-ኢኤሲ የሚኒስትሮች | Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም በስደተኞች ጉዳይ ላይ በተዘጋጀው የኢጋድ-ኢኤሲ የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዩጋንዳ ገቡ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ተቋም(ኢኤሲ) በስደተኞች ጉዳይ ባዘጋጁት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ዩጋንዳ ገብተዋል።

ሚኒስትር ብናልፍ ኢንቴቤ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በዩጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር እፀገነት በዛብህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በስደተኞች ጉዳይ ላይ በተዘጋጀው የኢጋድ-ኢሲኤ የሚኒስትሮች ጉባኤ በባለሙያዎች ደረጃ ትናንት በዩጋንዳ መጀመሩ ይታወቃል።

ባለሙያዎቹ የመከሩባቸውን አጀንዳዎችም ለሚኒስትሮች ስብስባ ያቀርባሉ ሲል ኢዜአ ዘግቧል።