Get Mystery Box with random crypto!

በኢፕድ ስልጠና ማዕከል ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ | Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

በኢፕድ ስልጠና ማዕከል ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ
በዛሬው እለት ለሚኒስቴሩ ሰራተኞች የሚሰጠው ስልጠና ተጀምሯል
****
(ኢ.ፕ.ድ)

ላለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የስልጠና ማዕከል ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል።

የማዕከሉ ስልጠና በዛሬ እለት ቀጥሎ ለሚኒስቴሩ ፈጻሚ ሰራተኞች እየተሰጠ ይገኛል።

በኢፕድ የስልጠና ማዕከል “ትጋት፣ ዕውቀት፣ ፈጠራና ትብብር ለውጤት” በሚል መሪ ሀሳብ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች የተሰጠው ስልጠና ለሶስት ቀናት በተለያዩ እውቅ አሰልጣኞች የተፈጸመ ነው።

ዶክተር ምህረት ደበበ፣ ዶክተር ወዳጄነህ መሀረነ፣ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ፣ የአሻጋሪ ኮንሰልቲንግ መስራች ወይዘሮ መቅደስ ገብረወልድ ስልጠናውን ለአመራሮች ሰጥተዋል።

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር አንተነህ ተስፋዬ እንደተናገሩት፤ ሚኒስቴሩ የተሻለ አቅምና ገጽታ እንዲኖረው ለማድረግ በኢፕድ ያገኙት ስልጠና በአይነቱ ለየት ያለና ለተሻለ የሥራ አፈጻጸም ወሳኝ ነው።

ከአመራር እስከ ባለሙያ ድረስ በስልጠናው መሳተፉ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት ውጤታማ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ሌሎች አመራሮች በበኩላቸው፤ በኢፕድ ስልጠና ማዕከል ያገኘት ስልጠና ተቋማቸውን ለመገንባት ትልቅ አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

ኢፕድ በስልጠና ማዕከሉ ከዚህ በፊት በተለያዩ የስልጠና ርዕሶች ዙሪያ ከ70 በላይ ለሚሆኑ ለፌዴራልና ለክልል ተቋማትና የግል ድርጅቶች በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ ተመሳሳይ ስልጠናዎችን በመስጠት አስመርቋል።

በአሁኑ ወቅትም የልማት ባንክ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ የሚኒሊክ ሆስፒታል፣ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን እና ቡናና ሻይ ባለስልጣን አመራሮች እና ሠራተኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አጫጭር ስልጠናዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ።

በሳሙኤል ወንድወሰን