Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 120.68K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-06-15 19:52:54
አትሌት ቢኒያም መሐሪ ከ 20 ዓመት በታች የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ሪከርድ በመስበር አሸነፈ

አትሌት ቢኒያም መሐሪ ከ20 ዓመት በታች የ10 ሺህ ሜትር ውድድር 26 ደቂቃ 37 ሰከንድ ከ93 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ሪከርድ በመስበር አሸንፏል። 

አትሌቱ ይህን ውጤት ያስመዘገበው በስፔን ነርጃ ከተማ በተካሄደ የኢትዮጵያ ለፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ የመምረጫ እና የሰዓት ማሟያ ውድድር ላይ ነው።

ሪከርዱ ሒደቱን ጠብቆ መፅደቅ ብቻ እንደሚቀረው የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል።

Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
7.4K viewsedited  16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 14:05:18 የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ በነገው ዕለት የሚከበረው የ1445ኛው የኢድል አል አድሃ (አረፋ) በዓል ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አድርጓል፡

በዚህም:-

• ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ

• ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው አጎና ሲኒማ ላይ

• ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ

• ከብሔራዊ ቤ/መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ

• ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

• ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ 22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ

• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል አጠገብ

• ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ አቧሬ ሴቶች አደባባይ ላይ

•ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

• ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መገንጠያ ላይ

• ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ

• ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ አጠገብ

• ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ

• ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ

• ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ
ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ነገ ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ/ም ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ብሏል ፖሊስ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
9.5K views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 11:20:50
መንግስት የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የባንክ አካዉንት እንዲታገድ አደረገ!

ተቋሙ በምን ምንክንያት እንደሆነ በማናዉቅበት ምክንያት በአንድ ዓመት ዉስጥ ለ 3ኛ ጊዜ የባንክ አካዉንቱ ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ መደረጉን አስታዉቋል።ፐርፐዝ ብላክ ባለፉት ሳምንታት ተቋሙን ህልዉና ዉስጥ የሚከተዉ ችግሮች እንደገጠመው አስታዉቋል።

ላለፉት ሶስት ሳምንታት የተቋሙ አካዉንት ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ከመደረጉ በተጨማሪ የዋና ስራ አስፈጻሚዉ ፍስሃ እሸቱ ( ዶ/ር) አካዉንት ጨምር ተመሳሳይ እጣ ፈንታ መድረሱ ተገልጿል።

ደመወዝ መክፈል የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው የቢሮ ኪራይን ጨምሮ የፕሮጀክቶች ስራዎች እንዲቆሙ መደረጉ ስራ አስፈፃሚው በሰጠዉ መግለጫ ገልጿል።ከ20 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች እንዳሉት እና ከ 1 ሺህ በላይ ቋሚ ሰራተኞች ያሉት ተቋሙ አሁን ላይ ካፒታሉ 2.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታዉቋል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
10.0K views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 09:06:05
ፑቲን ጦርነቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ቅደመ ሁኔታውን አስቀመጡ

የዩክሬን ጦር ራሽያ ወደ ግዛትዋ ''በህዝበ ውሳኔ'' ከጠቀለለቻቸው አራት ግዛቶች ጠቅልሎ የሚወጣ ከሆነ ጦርነቱን ወድያው እንደሚያቆሙ ተናገሩ።

አያይዘውም የምዕራባውያን የአለሁልሽ ማሟሟቅ ዩክሬንን ከመጉዳት ባሻገር ጥቅም የለውም።

ይህን ሀሰብ የማትቀበል ከሆነ ግን ከአሁኑ የባሰ ጥቃት ዩክሬን ታስተናግዳለች ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
10.5K viewsedited  06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 09:04:14
ከ 0 አመት ጀምሮ
በ የ ቀኑ የሚወጡ አዳዲስ  የ ሰራ ማስታወቂያዎች ይለቀቃሉ
ከጋዜጦች
ከኤጀንሲዎች
ከድርጅቶች በተጨማሪም
በስልክ እና በኮምፒውተር የሚሰሩ ፓርት ታይም
ስራዎች ስንለቅ  በፍጥነት እንዲደርሶ የቤተሰባችን አባል ይሁኑ


https://t.me/plusjobs
https://t.me/plusjobs
10.2K views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 22:13:06
ዛሬ ለፓርላማ የተመራው፤ የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የሚፈቅደው የአዋጅ ማሻሻያ ምን ይዟል? 

Via @EthiopiaInsiderNews

የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እንዲገቡ የሚፈቅደው የባንክ ስራ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ። የአዋጅ ማሻሻያው፤ የባንክ አገልግሎት ዘርፍን “ለመምራት፣ የፈቃድ አሰጣጥን ለመወሰን እና ለማስተዳደር” የሚያስችል ሆኖ እንደተዘጋጀ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ሰኔ 7፤ 2016 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው፤ የባንክ ስራ አዋጅ ማሻሻያን ጨምሮ አምስት የአዋጅ ረቂቆች ለፓርላማ እንዲቀርቡ ውሳኔ አሳልፏል።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው አዲሱ የአዋጅ ማሻሻያ፤ የባንክ ዘርፉን “በጥንቃቄ በተዘጋጀ የሕግ እና የቁጥጥር ማዕቀፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት መክፈት የዘርፉን ተወዳዳሪነት እና ቅልጥፍና” ያሻሽላል ተብሎ እንደሚታመን ያስረዳል። 

በአዋጅ ማሻሻያ ረቂቁ መሰረት፤ የውጭ ባንኮች “በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት” ተቀጥላ ባንክ ወይም የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ ወይም የውክልና ጽህፈት ቤት በኢትዮጵያ እንዲከፍቱ ይፈቀድላቸዋል። 

የአዋጅ ማሻሻያው፤ የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ባንኮች ውስጥ የድርሻ ባለቤት እንዲሆኑ ጭምር ይፈቅዳል። የውጭ ሀገር ዜጎች እና የውጭ ንብረት የሆኑ የኢትዮጵያ ድርጅቶች፤ በአንድ ባንክ የሚኖራቸው የአክሲዮኖች ድርሻ 40 በመቶ ብቻ ሆኖ በአዋጅ ማሻሻያ ረቂቁ ተገድቧል። 

ለዝርዝሩ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/13326/

@YeneTube @FikerAssefa
11.5K views19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 18:18:20 በኢትዮጵያ የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች ያለ ሀኪም ትዕዛዝ በመውሰድ በጀርሞች መላመድ የተነሳ ከፍተኛ የጤና ስጋት መደቀኑ ተገለፀ

መድኃኒቶችን ያለ ሀኪም ትእዛዝ መሸጥና መጠቀም ሁኔታውን ካባባሱት ጉዳዮች መካከል ተጠቃሽ ነው ተብሏል።

በኢትየጵያ የፀረ ተህዋሲያን መድሀኒቶች በጀርሞች መላመድ ትልቁ የጤና ስጋት በመሆኑ ችግሩን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት አስፋላጊ መሆኑን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል።በባለስልጣኑ  የመድሃኒት መረጃና አግባባዊ አጠቃቀም ዴስክ ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም እሸቴ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ የመድኃኒት ባለሙያዎች ማህበር ጋር  በመተባበር የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን ተናግረዋል።

የስልጠናው ዓላማ  አቅምን በማሳደግ የተሻለ የጤና ግብዓት ማቅረብ እንደሆነ ገልፀው ተቋሙ ከሌሎች ባለድርሻ  አካላት ጋር በመተባበር ብሄራዊ የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ስትራቴጂ ነድፎ በተግባር ላይ እያዋለ ይገኛል፡፡የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሀኪሞች ተገቢውን መድኃኒት ማዘዝ እና  የፋርማሲ ባለሙያዎችም  በሀኪም የታዘዘውን መድኃኒት በአግባቡ በማደል የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ይቀንሳል  ተብሏል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ትልቁ የጤና ሰጋት እና ክስተት የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ እንደሆነ አቶ ኃይለማርያም  ጠቁመው ይህንን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር  በመሆን መስራት እንደሚኖርባቸው አስረድተዋል።በስልጠናው የተመረጡ የግል የመድኃኒት ችርቻሮ ድርጅቶች ፣ የመድኃኒት ባለሙያዎችና የእንስሳት መድኃኒት ችርቻሮ ድርጅቶች የመድኃኒት ባለሙያዎች በስልጠናው እንዲሳተፋ ተደርጓል፡፡

አሥራ ሁለተኛው የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ቀን በዛሬው እለት  የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር  የመንግስት እና የግል  ዘርፍ አጋርነት ማጠናከር  በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል።


Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
11.2K viewsedited  15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 16:51:07
https://t.me/plusjobs
ከ 0 አመት ጀምሮ
በ የ ቀኑ የሚወጡ አዳዲስ የ ሰራ ማስታወቂያዎች ይለቀቃሉ
ከጋዜጦች
ከኤጀንሲዎች
ከድርጅቶች በተጨማሪም
በስልክ እና በኮምፒውተር የሚሰሩ ፓርት ታይም
ስራዎች ስንለቅ በፍጥነት እንዲደርሶ የቤተሰባችን አባል ይሁኑ
https://t.me/plusjobs
https://t.me/plusjobs
https://t.me/plusjobs
https://t.me/plusjobs
https://t.me/plusjobs
https://t.me/plusjobs
https://t.me/plusjobs
https://t.me/plusjobs

@plusjobs
11.4K views13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 11:39:25
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ ሀብቱ 672 ቢሊየን ብር ቢደርስም 367 ቢሊየን ብሩ በዕዳ የተመዘገበ ነው ተባለ!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቅርቡ በሚያካሂደው የኃይል ሽያጭ ታሪፍ ማሻሻያ ዙሪያ ከተቋማት እና ከተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እየመከረ መሆኑን አስታውቋል።የታቀደው የታሪፍ ክለሳ የኢነርጂ ዘርፉን ለማሳደግ እና አገልግሎቱን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ ሀብቱ 672 ቢሊየን ብር ቢደርስም 367 ቢሊየን ብሩ በዕዳ የተመዘገበ ነው ሲሉ የተቋሙ የኮርፖሬት ፕላኒንግ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ ከሚዲያ ሃላፊዎች ጋር ባካሄዱት ምክክር ገልጸዋል።በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከውሃ 4 ሺህ 820 ሜጋ ዋት፣ ከንፋስ 404 ሜጋ ዋት እና ከእንፋሎት 32 ሜጋ ዋት ኃይል እያመነጨች ትገኛለች ብለዋል።

Via Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa
12.1K views08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 10:36:09
ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

በመጪው ዓመት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር አፈፃፀም በስፋት ውይይት የተደረገበት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልጸዋል።

በ2016 በጀት ዓመት ከማኅበረሰቡ በተገኘ ድጋፍ በትምህርት ለትውልድ መርሐ ግብር 22 ሺህ የሚደርሱ የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ጥገና መከናወኑን አስታውቀዋል።በተለይም ለተማሪዎች የሚሰጠው የሪሚዲያል ፈተና መጀመሩን በማስታወቅ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል።ሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር የገለጹት ሚኒስትሩ÷ ፈተናውን የተሳለጠ ለማድረግ ለፈታኝ መምህራን በቂ ሥልጠና እየሰተጠ መሆኑንም ገልጸዋል።

ዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑን ተከትሎ ለዚህ የሚረዳ በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።በክረምት ወራት 62 ሺህ መምህራንን በሚያስተምሩት ትምህርትና የማስተማር ሥነ ዘዴ ዙሪያ ሥልጠና ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።ሚኒስቴሩ በክረምት ከያዛቸው ሥራዎች መካከል የዩኒቨርሲቲዎች ዕድሳት ሥራ አንዱ በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
12.3K views07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ