2022-07-16 10:59:31
"ተመራቂዎች ያገኙትን እውቀት ወደ ስራ በመለወጥ የገጠመንን ችግር በአንድነት መመከት ይገባል"
- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
ተመራቂዎች ያገኙትን እውቀት ወደ ስራ በመለወጥ የገጠመንን ችግር በአንድነት መመከት እንዳለባቸው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አሳስቡ።
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 58 ተማሪዎችን አስመርቋል።
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምረቃ ሥነ- ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር መማር ማለት የባህሪ ለውጥ ማምጣት ነው፤ ተመራቂዎች በዘር፣ በሀይማኖት ከመከፋፈል ወጥተው ለአገር የሚጠቅም ስራ እንዲሰሩና የገጠመንን ችግር በአንድነት መመከት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ኢትዮጵያን ባላችሁበት ሆናችሁ ልክ እንደ ቀደሞ አባቶችና እናቶቻችሁ ውደዷት፣ ያገናችሁትን እውቀት ወደ ስራ በመለወጥ ሀገሪቱ የገጠማትን ችግር እንድታቃልሉና በሙያችሁ ህዝባችሁን በፍፁም እኩልነት እንድታገለግሉ አደራ እላለሁ ብለዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ላለፉት 72 አመታት በማስተማርና ምርምር በማድረግ ኢትዮጵያ ሲያገለግል ቆይቷል። በግብርናው፣ ኢንዱስትሪዎችና ሌሎች ዘርፎች የሚፈልጉትን የተማረ የሰው ሃይል በጥራት ሲያቀር ቆይቷል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በርካታ ችግር እያስተናገደች ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፣ አገር ለማሳደግ መረባረ ሲገባ የበርካታ ንጹሃን ደም እየፈሰሰ ነው። ህዝባችን የሚፈልገው በሰላም ሰርቶ በሰላም መግባት ነው፣ መሰረት ልማቶች እንዲሟሉለት ነው።
አገራቱ ከጦርነት፣ ከስጋት፣ ከመፈናቀል ወጥታ ወደ ተሻለ ደረጃ እድትደርስ መንግስት የተለያዩ እቅዶችን ቀርጾ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰውየተማረ ሰው ችግር ውስጥ ያለን ህዝብ ከችግር ማውጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
አዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና፣ ዩኒቨርስቲ በአሁኑ ወቅት 11 የምርምር ተቋማትና ሁለት የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አሉት። ከ40 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያሰተማረ ነው። 40 በመቶ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ሲሆኑ 33 በመቶው ደግሞ ሴቶች ናቸው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከውስጥና ከውጭ ጠላት በበዛባት ወቅት እናንተን ተንከባክባ ለዛሬው ቀን አብቀታኋለች፣ በዘርና በጎሳ ከመከፋፈል ወጥታችሁ ሀገሪቱን በጥናትና ምርምር መርዳት አለባችሁ ብለዋል።
በሞገስ ፀጋዬ
1.4K views07:59