Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethpress — Ethiopian Press Agency/አማርኛ / E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethpress — Ethiopian Press Agency/አማርኛ /
የሰርጥ አድራሻ: @ethpress
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.66K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 142

2022-08-31 11:14:20
1.4K views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:46:47 23 የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ተቋማት ዛሬ የሥራ ፈቃድ ያገኛሉ
****
(ኢ.ፕ.ድ)

በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ 46 የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ተቋማት መካከል 23ቱ ዛሬ የሥራ ፈቃድ እንደሚወስዱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አስታወቀ።

የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሀገራዊ የምክክር መድረክ "የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ለአብሮነት እሴቶች መጠናከር" በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ፤ ኢትዮጵያ በወጡ ፖሊሲና አዋጆቿ በብዙ ሀገራት ባልተለመደ መልኩ ዕውቅና መስጠቷን ገልፀው በዚህ መሰረት የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ለተደረገው የምዝገባ ጥሪ ፈጣን ምላሽ ተሰጥተዋል ብለዋል።

በሃገሪቱ ካሉ 46 የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን መካከልም አሥፈላጊውን መረጃ ያሟሉት 23 ያህሉ ዛሬ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ፈቃድ እንደሚቀበሉ ገልፀዋል።

የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ትኩረት የተሰጠው ሃይማኖቶች በሀገር ግንባታ የተጫወቱት ሚና የማይዘነጋ በመሆኑ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የመንግስት ዋናው ፍላጎት የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሕግና ሥርዓት አክብረው በሰላምና አንድነት ዕሴት ግንባታ ላይ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ነው ሲሉ አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው፤ 93 በመቶ ያህል አማኝ ባለባት ሀገር የሚታየው የሰላም እጦትና የተለያየ ችግር ሃይማኖቶች ተገቢውን አሥተምህሮ ያለመስጠታቸው ምልክት መሆኑን ገልፀዋል።

ሆኖም አሁን በተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎች ሃይማኖቶች በሚዲያዎቻቸው የግብረ ገብነት ትምህር ላይ በትኩረት በመሥራትና ትውልዱን በመቅረፅ ወደመከባበር መመለስ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በውብሸት ሰንደቁ
1.5K views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:46:03
1.4K views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:34:06 የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ
******
(ኢ.ፕ.ድ)

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ እንዳሉት አሸባሪው ህወሓት በተደጋጋሚ ጊዜ የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በመተው ለሦስተኛ ጊዜ በሀገራችን ላይ ጦርነት ከፍቷል።

መንግስት የሠላም አማራጭ የተከተለው የትግራይን ህዝብ ዘላቂ ጥቅም በማሰብ እንደሆነ ጠቁመው፣ ቡድኑ ግን ለሶስተኛ ጊዜ ወረራ መፈጸሙን ተናግረዋል።

አሻባሪው ህወሃት ለሠላም የተዘረጋውን የኢትዮጵያ እጅ ነክሶ የጀመረውን የጥፋት ጉዞ ለሠላማችን ዘብ በመቆም እንገታዋለን ብለዋል።

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ብለዋል።

መላው የክልሉ ህዝብ ባለፋት ጊዜያት በአገር ህልውና ላይ ከውስጥና ከውጭ የተቃጣብንን አደጋ ለመመልከት በተደረገው ጥረት ምልአተ ህዝቡን በማነቃነቅ ግንባር ቀደም የድጋፍ ተሳትፊ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደተቻለም ገልጸዋል።

ሰርቶ መለወጥ የሚቻለው ሀገር ሰላም ስትሆን መሆኑን የገለጹት ኃላፊው አሸባሪው ህወሓት የሀገርን አንድነት ለመናድ የሚያደርገውን ሙከራ ለመመከት የክልሉ መንግስትና ህዝብ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ፣ ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልሀኪም ኡመርን ጨምሮ የፓርቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች መሳተፋቸውን የክልሉ የመንግሥት ኮምንኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
1.5K views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:34:01
1.4K views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:09:24 “አሸባሪው ሕወሓት ሶስተኛ ዙር ጦርነት የከፈተው የትግራይ ሕዝብ እንደሚያጠፋው ስለተገነዘበ ነው”
– አቶ ከበደ ዴሲሳ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ
*****
(ኢ ፕ ድ)
አሸባሪው ሕወሓት ጦርነት የከፈተበት ምክንያት የማሸነፍ ዓላማ ይዞ ሳይሆን ከትግራይ ሕዝብ ጥያቄ ለመደበቅና ሕዝቡ እንደሚያጠፋው ስለተገነዘበ ነው ሲል የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን ትናንት በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ አሸባሪው ሕወሓት ሶስተኛ ዙር ጦርነት የከፈተው ለማሸነፍ ዓላማ ይዞ ሳይሆን የትግራይ ሕዝብ እንደማያኖረውና እንደሚያጠፋው ስለተገነዘበ በጦርነት ውስጥ ተደብቆ ለማለፍ አስቦ ነው፡፡

የሽብር ቡድኑ በስሜን ዕዝ ጥቃት በሰነዘረበት ወቅት እንኳ ሁሉንም ነገር በተቆጣጠረበት ጊዜ ማሸነፍ ያልቻለ፤ ብዙ ሞክሮ ውርደትን ተከናንቦ እንደተሸነፈ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ መንግሥት ከጦርነት ይልቅ በንግግር ለመፍታት ተመራጭ ነው ብሎ ያቀረበውን የሰላም አማራጭ አሻፈረኝ ብሎ ጦርነት የከፈተው የማሸነፍ ዓላማ ይዞ ሳይሆን ከትግራይ ሕዝብ ጥያቄ ለመደበቅና ሕዝቡ እንደሚያጠፋው ስለተገነዘበ ነው ብለዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ ለጀመረው ይፋዊ ወረራ መንግሥት እስካሁን ድረስ ከመመከት ያለፈ የማጥቃት እርምጃ አልወሰደም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ አሁንም ቡድኑ ወደ ሰላም እንዲመላስ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በቡድኑ ላይ ጫና ማድረግ እንደሚኖርበት
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=80364
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
1.5K views07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:33:54
ጳጉሜን 5 - "የአንድነት ቀን" በመላ አገሪቷና የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በሚገኙበት ሁሉ እንደሚከብር የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ገለፀ
****************
(ኢ ፕ ድ)
"የአንድነት ቀን" በሚል የተሰየመው ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም በመላው ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በሚገኙበት በታላቅ ድምቀት እንደሚከብር የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ገለፀ።
የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የመከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር ኮ/ል ጌትነት አዳነ ፤ በዓሉ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበርና አስታውቀዋል።
"ተፈጥሯዊ የሆነውን ልዩነቶቻችን እንደ ችግር ለመጠቀም የሚፈልጉ የውጭና የውስጥ የሀገራችንን ጠላቶች በተለመደው ኢትዮጵያዊ አንድነታችን በመቆም ለአለም የምናሳይበት በዓል ይሆናል" ብለዋል።
በዓሉ ከግለሰብ ጀምሮ በተለያዩ ተቋማት ደረጃ በታላቅ ድምቀት እንደሚከበርና አዲሱን አመት በአዲስ ተስፋ ለመቀበል የምንነሳሰበትና የአንድነት መገለጫ የሆነው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችንን የምናከብርበት ዕለት ይህናል ሲሉ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ገልፀዋል።
የመንግስት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፤ በዓሉ ከሀገር ውጭ በሀምሳ ሁለት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንሲላ ፅ/ቤቶች በድምቀት እንደሚከበር ገልፀዋል።
በዕለቱ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎሉ የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚደረጉና አምስት ሰዓት ላይ "እኔ ለሀገሬ አንድነት" የሚል ልዩ ፕሮግራምም መሰናዳቱን የሀገር መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ገጹ አስታውቋል።
2.1K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:19:25 በጤና መድህን ስርዓት ወስጥ ያለውን የገንዘብ አሰባሰብ ስልት ዘመናዊ ለማድረግ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ገለጸ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ለጤና መድህን አገልግሎት መሳለጥ ሲባል ከማህበረሰቡ የሚሰበሰቡ መዋጮዎች በባንክ ስርዓትና በሌሎች አማራጭ የፋይናንስ አገልግሎት ተቋማት ውስጥ እንዲያልፉ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት የፋይናንስ ተቋማት በተለይም ባንኮች በጤና መድህን ስርዓት ወስጥ ያለውን የገንዘብ አሰባሰብ ስልት ዘመናዊ ለማድረግ ሚናቸው የጎላ በመሆኑ በዘርፉ የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲወጡ ለባንክ አመራሮች የግንዛቤ መፍጠርና ያሉ እድሎችን የማስተዋወቅ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ በዚህ ወቅት እንዳስታወቁት ከአባላት የሚሰበሰቡ መዋጮዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉ በበምጣታቸው ምክንያት ከዚህ በፊት በእጅ የሚሰበሰቡ መዋጮዎች በባንክ ስርዓት ውስጥ እንዲያልፉ ማድረግ አስፈላጊ ብለዋል፡፡
መዋጮዎች በሚሰበሰቡበት ወቅት በባንክ ስርዓት እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲሁም ዜጎች በአንድ ጊዜ የሚከፍሉትን መዋጮ ረዘም ባለ ጊዜ በባንኮች በመቆጠብ በአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ስርዓት ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ከዘጠኝ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ እማዋራ/አባወራዎች የጤና መድህን ስርዓት አባል መሆናቸውን የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉቀን አርጋው ለተሳታፊዎች ባቀረቡት ፅሁፍ ገልፀዋል፡፡
በአጠቃላይ የተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ አርባ አምስት ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን ሶስት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር መዋጮ የተሰበሰበ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
በፍቃዱ ዴሬሳ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
1.7K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:19:22
1.5K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:48:32 ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታን በተመለከተ ከድሬዳዋ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ!!
አሸባሪው የህውሓት ቡድን ለ27 ዓመታት የአገሪቱን ማእከላዊ ስልጣን ተቆጣጥሮ በነበረበት ጊዜ ከፈጸማቸው ኢሰብአዊ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዋነኛ የችግሩ ገፈት ቀማሽ የድሬደዋ አስተዳደር ህዝብ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።
ቡድኑ የአገሪቱ ፈላጭ ቆራጭ ገዢ በነበረበት ዘመን የፍቅር ፣ የመቻቻል እና የብሄር ብሔረሰቦትች የአብሮነት መኖሪያ ትንሿ ኢትዮጵያ የሆነውን የድሬደዋ አስተዳደር ህዝብን እርስ በእርስ እንዲጠራጠር እና እንዲጋጭ በማድረግ በማህበረሰቡ መካከል አለመተማመን እንዲፈጠር አርጓል፡፡
አሸባሪው ህውሀት በፍቅር መሀል ጥላቻን በመተማመን መሀል መጠራጠርን በአንድነት መሀል መከፋፈልን በበጎነት መሀል ክፋትን በሰላም መሀል ጦርነትን የሚዘራ ባጠቃላይ ከሰው ልጆች መሰረታዊ እና ሰዋዊ ባህሪ ያፈነገጠ ፀረ -ሰው ድርጊት የሚፈፅም መሰሪ ስብስብ ነው ።
ከዚህም አልፎ ለርካሽ ፖለቲካና ለስልጣኑ ቀጣይነት ሲል ሴራ በመጎንጎን የስልጣኔ በር የፍቅር እና አብሮ መኖር ተምሳሌት የሆነችውን ድሬደዋን ስምና ዝናዋን በማይመጥን ደረጃ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ማሽቆልቆል እዲፈጠርና አስተዳደሩ በልማት ወደ ኋላ እንዲቀር አድርጓል፡፡
አሸባሪው ህውሓት ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እየተጋለበ በከፈተው ጦርነት በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚኖሩ በርካታ ንፁሃን ዜጎችን ህይወት አጥፍቷል፤ በእድሜ ልክ ድካም የተከማቸ የሚሊዮኖችን ሀብትና ንብረትም በከንቱ አውድሟል።
የዚህ ባንዳ ቡድን ዋነኛ ሀሳብ ኢትዮጵያን እኔ ወይም የኔ ተላላኪ የሆነ ሀይል ካልመራት አፈርሳታለሁ የሚል ሲሆን ይህን በጤነኛ አእምሮ ሊታሰብ የማይችል ከክፋት ሁሉ የከፋ ሀሳቡን ለማስፈፀምም ለሶስተኛ ጊዜ ጦርነት በመክፈት ምስኪን የደሀ ልጆችን በአደንዛዥ እፅ እያደነዘዘ ወደ እሳት እየማገደ ይገኛል።
ቡድኑ የያዘው እኩይ አላማ ለአገራችን ሁለንተናዊ ሰላም እና ልማት ፀር መሆኑን የሚገነዘበው የድሬደዋ አስተዳደር መንግስት እና ህዝብ በምስራቅ በኩል የህወሃት አጋሮች በሆኑት እንደ አልሸባብ እና ሸኔ ባሉ የሽብር ቡድኖች የሚሞከሩ ሙከራዎችን በማክሸፍ እና በህወሃት ላይ በሚወሰደው እርምጃ እንደሁልጊዜው ያልተቆጠበ ድጋፉን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በአፅንኦት እየገለፀ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር አስፈላጊውን መሰዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑንም ያረጋግጣል፡፡
በመጨረሻም ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ቡድኑ የጀመረውን ጦርነት አቁሞ በኢትዮጵያ መንግስት የቀረበውን የሰላም አማራጭ እንዲቀበል ተገቢውን ጫና እንዲያሳድር የድሬደዋ አስተዳደት ጥሪውን ያቀርባል።
የድሬደዋ አስተዳደር
ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም
ድሬዳዋ
1.6K views12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ