Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethpress — Ethiopian Press Agency/አማርኛ / E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethpress — Ethiopian Press Agency/አማርኛ /
የሰርጥ አድራሻ: @ethpress
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.66K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-17 09:17:07
“ወዳጅ እንዲኮራ፣ ጠላት እንዲፈራ መስራት ብቻ ሳይሆን የሰራነውን ማሳየት አለብን"
- አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
************************
(ኢ ፕ ድ)
ወዳጅ እንዲኮራ፣ ጠላት እንዲፈራ፤ ወዳጅ እንዲተማመን፣ ጠላት እንዲመነምን መስራት ብቻ ሳይሆን የሰራነውን ማሳየት አለብን ሲሉ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡
በብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ባለቤትነት በእውነተኛ ታሪክ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99679
1.8K views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 09:15:37
ለሱዳን ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ የፌዴራል መንግስት ግብረ ኃይል አቋቁሞ እየሰራ ነው
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የሱዳን ጦርነትን ተከትሎ ወደኢትዮጵያ ለሚመጡ ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ በፌዴራል መንግስት ደረጃ ግብረኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሱዳን የተከሰተውን የእርስ በርስ ግጭት ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99673
1.9K views06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 16:10:19
አቶ ደመቀ መኮንን በቤላሩስ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ከሆኑት ሚስተር ዲሚትሪ ሉካሼንኮ ጋር ተወያዩ
******************
(ኢ ፕ ድ)
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቤላሩስ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል የሆኑትን ሚስተር ዲሚትሪ ሉካሼንኮን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የክብር ቆንስሉ በምስራቅ አውሮፓዊቷ ሀገር ኢትዮጵያንና ህዝቧን በመወከል እያበረከቱት ስላለው አስተዋጽኦ አቶ ደመቀ ምስጋና አቅርበዋል።
ኢትዮያ እና ቤላሩስ በተለይ በኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም፣ ግብርና ሜካናይዜሽን እና ማዕድን ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ይበልጥ ማጠናከር ይገባቸዋል ብለዋል። "ይህን ለማሳካት በእኛ በኩል የምንችለውን እናደርጋለን" ብለዋል።
ሚስተር ዲሚትሪ ሉካሼንኮ በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቲዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
2.6K views13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 14:41:32
መልካም ዕ ድል
2.4K views11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 18:41:37
ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት መጀመር የሚያስችለውን ፈቃድ አገኘ
****************
(ኢ ፕ ድ)

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት መጀመር የሚያስችለውን ፈቃድ መስጠቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሰታወቀ።

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የውጭ ሀገር ኩባንያ ያደርገዋል ተብሏል።

ባንኩ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ለሳፋሪ ኮም መስጠቱን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ አስታውቀዋል፡፡

ባንኩ በጥሬ ገንዘብ የሚደረግን ግብይት በዲጂታል ክፍያ ስርዓት ለመተካት የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍና የሳፍሪኮም ፈቃድም የዚሁ አንዱ አካል ተደርጎ ይወሰዳል።
1.5K views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 18:31:54
የኢጋድ አባል ሃገራት የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን በጋራ ለመሥራት ተስማሙ
******************
(ኢ ፕ ድ)

ከስድስት የኢጋድ አባል ሃገራት የተውጣጡ የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን መረጃን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ስምምነት በጅቡቲ ተፈራርመዋል።

የሰምምነቱ ፈራሚዎች የጋዜጠኝነት ሙያዊ ግዴታዎችን በጠበቀ መልኩ በየሃገራቸው የሚሠሩ ሥራዎችን በተመለከተ መረጃ የሚያጋሩበትና ወሰደው የሚጠቀሙበት ነው። የመግባቢያ ስምምነቱ 14 አንቀጾችን የያዘ ነው ተብሏል።

የጋራ ስምምነቱን ለማጽደቅ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የኢጋድ ሊቀመንበር ወርቅነህ ገበየሁ በቋንቋ፣ በባህልና በታሪክ በተሳሰሩት የኢጋድ አባል ሃገራት የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን በጋራ አብረው መሥራታቸው ልማትን ለማፋጠን፤ ሕዝቦቹን ለማቀራረብ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የኢጋድ አባል ሃገራት እንቅስቃሴ በዋናነት መዘገብ ያለበት በራሳቸዉ በአባል ሃገራቱ መገናኛ ብዙሃን መሆኑ ጥቅሙ የጎላ ነው ሲሉ የኢጋድ ሊቀመንበር ገልጸዋል።

የጋራ ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ፣ የጅቡቲ፣ የኬንያ፣ ዑጋንዳ፣ ሶማሊያና ደቡብ ሱዳን የሕዝብ መገናኛ ብዙኃን ናቸው።
1.4K views15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 16:51:26
#ከአፕድ_ማህደር
ፋንቱ ያለሰፈሯ ሌሊት ስትዞር ተይዛ ታሰረች
ወይዘሮ ፋንቱ ወልደማሪያም የተባለች በንፋስ ስልክ አካባቢ የምትኖር ሴት ያለሰፈሯ ከምሽቱ በ10 ሰዓት በየካቲት 12 አደባባይ ስትዘዋወር በመገኘቷ ተይዛ የሶስተኛ ወረዳ ፍርድ ቤት የአንድ ወር እስራት የቀጣት መሆኑን አስታውቋል፡፡
ወይዘሮ ፋንቱ ስትዘዋወር መገኘቷንና ተላላፊ መኪናዎችንም አድርሱኝ በማለት ማስቸገሯን ፖሊሶች መመስከራቸው ታውቋል፡፡
ተከሳሿም ፍርድ ቤት ቀርባ በተጠየቀች ጊዜ በአድራጎቷ ጥፋተኛ መሆኗን ስላመነች፤ ፍርዱ ተሸሽሎላት በ30 ብር መቀጫ ወይም በአንድ ወር እስራት እንድትቀጣ ተደርጎ መቀጫውን መክፈል ስላልቻለች አንድ ወር እንድትታሰር ወደ ወህኒ ወርዳለች ሲል ከአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ከሶስተኛ ወረዳ ፍርድ ቤት የተገኘ ዜና ያስረዳል፡፡
ጥቅምት 7 ቀን 1963 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመ
በኃይማኖት ከበደ
1.6K views13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 16:06:01
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።
1.8K views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 10:21:33
በመስኖ መልማት ከሚችለው 10 ሚሊዮን ሄክታር ውስጥ የለማው 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብቻ ነው
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በመስኖ መልማት ከሚገባው 10 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ እስካሁን የለማው አንድ ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ሄክታር ብቻ መሆኑን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ 110 ሚሊዮን ሄክታር መሬት አላት።ከዚህ ሀብት ውስጥ ግማሽ የሚሆነው ለእርሻና ሌሎች ልማቶች ሊውል የሚችል መሬት ነው።ከዚህ ውስጥ ግን ጥቅም ላይ የዋለው ከ30 ከመቶ በታች ነው፡፡

ሙልውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99153
2.3K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 10:21:11
በዲጂታል የነዳጅ ክፍያ አጠቃቀም የነበሩ ችግሮች መፈታታቸውን አሽከርካሪዎች ተናገሩ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
በመዲናዋ በተጀመረው የኤሌክትሮኒክስ ነዳጅ ክፍያ ስርዓት የነበረው መስተጓጎል መሻሻል እያሳየ መሆኑን በአዲስ አበባ የሚገኙ አሽከርካሪዎችና የነዳጅ ቀጂዎች ገለጹ።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በበኩሉ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ በተደረገው የነዳጅ ክፍያ ስርዓት የነበረውን ክፍተት ለማስተካከል የተቀናጀ ግብረኃይል ተቋቁሞ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አስታውቋል፡፡
በመዲናዋ አራት ኪሎ አካባቢ ነዳጅ በመቅዳት ላይ እያሉ ….
ሙልውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99153
2.1K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ