Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethpress — Ethiopian Press Agency/አማርኛ / E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethpress — Ethiopian Press Agency/አማርኛ /
የሰርጥ አድራሻ: @ethpress
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.66K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-05-01 10:28:46
45 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን ከወባ በሽታ መታደግ ተችሏል
*************
(ኢ ፕ ድ)
እንደሀገር በተከናወኑ የመከላከል ሥራዎች ለወባ በሽታ ተጋላጭ የሆኑ 44 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሰዎችን ከወባ በሽታ መታደግ እንደተቻለ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ ሰሞኑን እንደገለጹት፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ537 ወረዳዎች የሚውል 19 ነጥብ 7 ሚሊዮን አጎበር ተገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል። ከዚህ ውስጥ 16 ሚሊዮን 861 ሺህ በላይ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=98321
1.2K views07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 10:27:55
በመዲናዋ ሕግ በተላለፉ ከ17 ሺ በላይ አሽከርካሪዎች ላይ ርምጃ ተወሰደ
**************
(ኢ ፕ ድ)
– 211 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው አልፉል
በአዲስ አበባ ከተማ በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የፍጥነት ወሰን በጣሱ ከ17 ሺ በላይ አሽከርካሪዎች ላይ ርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድ ደህንነት ምክር ቤት አስታወቀ። 211 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉንም አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድ ደህንነት ምክር ቤት የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=98312
1.1K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 10:13:27
አዋኪ ድርጊቶችን በፈፀሙ 2 ሺህ 625 የንግድ ቤቶች ላይ ርምጃ ተወሰደ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በመዲናዋ የተለያዩ ስፍራዎች አዋኪ ድርጊቶችን በፈፀሙ 2 ሺህ 625 የንግድ ቤቶች ላይ ርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሕል፣ ኪነጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር በመተባበር የሆቴል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዓለም አቀፍ ፕሮቶኮልን ጠብቀው እንዲሠሩ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=98304
1.2K views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 09:57:59
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ዘጠኝ ሚሊዮን የሚጠጉ ቱሪስቶች ክልሉን ጎብኝተዋል
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
- 163 ሺህ ያህሉ የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ናቸው
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ዘጠኝ ሚሊዮን የሚጠጉ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ክልሉን መጎብኘታቸውን ኦሮሚያ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። 163 ሺህ ያህሉ የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች መሆናቸው ተጠቁሟል።
የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም የቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሁንዴ ከበደ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ኦሮሚያን ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=98318
1.3K views06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 19:30:03
ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በተሰጠ መግለጫ መሠረት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች

ወንድወሰን አሰፋ
ሲሳይ አውግቼው
ማዕረጉ ቢያብን
በቀለ ኃይሌ
አሰፋ ኪዳኔ
መሰረት ቀለመወርቅ
አለልኝ ምህረቱ
ታደሰ መንግሥቱ
ዮርዳኖስ አለሜ
ነዋይ ዮሃንስ
ሄኖክ ኪዳኔ
መስከረም አበራ
ትእዛዙ ታረቀኝ
ሙሉቀን ወንዴ
ሰይፈ ተስፋዬ
ማስረሻ እንዬው
ጌታቸው ወርቁ
አንደበት ተሻገር
ገነት አስማማው
ቴዎድሮስ አስፋው
ዳዊት ጋሻው
ሞላልኝ ሲሳይ
ዳዊት አባቡ
ቢሰጥ ተረፈ
አብርሃም ጌትነት
ዮሃንስ አበበ
ጌታወይ አለሙ
ሰለሞን ልመንህ
እርቁ ተስፋዬ
ሳሮን ቀባው
ሀብታሙ ዳኜ
ዘመኑ ጌታቸው
ታደሠ ወንዳይነህ
አባይ ዘውዱ
አድነው አማረ
ጆን ተሻገር
ነብያት ተገኝ
ምስጋናው ማሩ
ቴዎድሮስ ተሾመ
ቢያዝን ምህረቱ
ጌታቸው ጥዑመልሳን
ጌትነት ወንድወሰን
2.1K views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 19:20:02
ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በተሰጠ መግለጫ መሠረት በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎች

ሀብታሙ አያሌው፣
ምንአላቸው ስማቸው፣
ብሩክ ይባስ እና
እየሩሳሌም ተ/ፃዲቅ
ዘመድኩን በቀለ
ልደቱ አያሌው
መሳይ መኮንን
ጎበዜ ሲሳይ
ምህረት ወዳጆ (ምሬ ወዳጆ)
በለጠ ጋሻው እና
ሙሉጌታ አንበርብር
1.8K views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:57:20
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ከሰአት በኋላ ከመላው ኢትዮጵያ ለመጡ ከ200 በላይ የከተማ ከንቲባዎች ገለጻ አድርገዋል። የክልል ፕሬዝዳንቶች የተገኙበት ይህ መድረክ የበለፀጉ ከተሞችን ለመፍጠር ከንቲባዎች በሚጫወቱት ሚና ላይ ያተኮረ እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።
1.8K views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 11:46:29
በቦረና ዞን ሁለት ወረዳዎች በ136 ሚሊየን ብር የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአለም ባንክ በተገኘ ብድር በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል በቦረና ዞን ሁለት ወረዳዎች በ136 ሚሊየን ብር የጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ለማከናወን ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ተፈራረመ።
የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ እንደገለጹት በቦረና ዞን በተደጋጋሚ ድርቅ በሚከሰትባቸው አካባቢዎች ድርቁን ለመቋቋም ታሳቢ የተደረጉ ስራዎች ተሰርተዋል። ድርቅን የሚቋቋምና ለአየር ንብረት የማይበገር የውሃ ልማት ስራ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአልወያ ወረዳ 3 ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ በ90 ሚሊየን ብር እና በዋጨሌ ወረዳ 6 ጉድጓድ ከ46 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ እንደሚከናወንና የበጀት ምንጩ ከአለም ባንክ ዋን ዋሽ ፕሮግራም በኩል በተገኘ ብድር ይተገበራል።
ኮርፖሬሽኑ ስራውን በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ እንዲያስረክብ አሳስበዋል፡፡
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሉ ለማ በበኩላቸው የጉድጓድ ቁፋሮ ስራውን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለማስረከብ በትጋት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡
በኤልወያና በዋጨሌ ወረዳዎች የሚከናወነኑት የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራዎች በ4 ወር ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
722 views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 11:43:05
ዲያስፖራው በዘጠኝ ወራት ለሀገራዊ ጥሪዎች 19 ሚሊዮን ዶላር አበርክቷል
ለሦስት ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል
በስምንት ወራት 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ወደ ሃገር ውስጥ ልኳል
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የዲያስፖራው ማኅበረሰብ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለሀገራዊ ፕሮጀክቶችና ወቅታዊ ሀገራዊ ጥሪዎች ከ19 ሚሊዮን ዶላር በላይ አስተዋፅዖ ማበርከቱን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ ያስመዘገቡ 223 የዲያስፖራ ባለሀብቶችም ሦስት ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እንደቻሉ ተገልጿል።
የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ግርማ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ ዲያስፖራው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለሀገሩ ከፍተኛ አስተዋፅዖ በማበርከት ለሀገራዊ ፕሮጀክቶችና ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=98162
708 views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 11:42:25
በትግራይ ክልል ከዛሬ ጀምሮ የንግድ ባዛር ይካሄዳል
***************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን የንግድ እንቅስቃሴ ለማስቀጠልና የተሻለ ቀጠናዊ ትስስር ለመፍጠር በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ባዛር መዘጋጀቱን የክልሉ የንግድ ምክር ቤት ገለጸ።
የትግራይ ክልል የንግድ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አታኽልቲ ስዩም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ ትግራይ ላይ ተቋርጦ የቆየውን የንግድ እንቅስቃሴ ለማስቀጠልና የተሻለ ትስስር ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=98146
688 views08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ