Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethpress — Ethiopian Press Agency/አማርኛ / E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethpress — Ethiopian Press Agency/አማርኛ /
የሰርጥ አድራሻ: @ethpress
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.66K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-04 14:43:26
የአርበኞችን የድል ተምሳሌትነትና አንድነትበልማት ሥራዎች መድገም ይገባል
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የአርበኞችን የድል ተምሳሌትነት አንድነትን በማጽናትና በልማት ሥራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ መድገም ይገባል ሲሉ የጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ተናገሩ።

ጀግኖች አርበኞች ፋሽስት ጣልያንን ያሸነፉበት የድል በዓል ሚያዝያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም የበዓሉን ክብር በሚመጥን መልኩ በአራት ኪሎ የድል ሐውልት እንደሚከበር ተገልጿል።

ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ትውልዱ የአርበኞችን የድል ታሪክ በኢኮኖሚው፣ በትምህርት፣ በሥራና በሌሎች ዘርፎች ውጤት በማስመዝገብ እንዲሁም የሀገርን አንድነትና ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ሊደግመው ይገባል።

https://www.press.et/?p=98559
1.8K views11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 11:01:49
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት

ዛሬ ጠዋት በማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴው በኩል አሁናዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ ገምግመናል። የወደፊት ተግባራትንም ለይተናል።
2.0K views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 10:16:17
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የኤዲተርስ ፎረም ዛሬ በመካሄድ ላይ ነው

በመድረኩ ከዚህ በፊት የተሰሩ ጥናቶች ተጠናቅረው የቀረቡበት መጽሀፍ ይመረቃል።

በዚሁ መጽሀፍ የተካተቱና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮምንኬሽን መምህራን እንዲሁም በኢፕድ ከፍተኛ አርታኢያን የተሰሩ አዳዲስ ጥናቶች ይቀርባሉ፤ ሙያዊ ውይይትም ይደረግባቸዋል።

ጥናቶቹ የተካተቱበትን መጽሀፍ ለመመልከት ከስር ያለውን ሊንከ ይጫኑ
https://www.press.et/?p=98548
2.0K views07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 10:21:18
ከቡና የውጭ ንግድ ከ896 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል
***************
(ኢ ፕ ድ)
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከቡና የውጭ ንግድ ከ896 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ። ከሻይ ቅጠል ምርት አንድ ነጥብ 83 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደተገኘም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ገለታ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ባለሥልጣኑ በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 243 ሺ 659 ቶን ቡና በመላክ አንድ ነጥብ 19 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 163 ሺ 666 ቶን የቡና ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ 896 ነጥብ 7 ሚሊዮን ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=98526
2.9K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 10:04:48
የፌስቲቫሉ መዘጋጀት የኢትዮጵያን የሰርከስዕድገትና አቅም ለማሳየት ይረዳል
****************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ የሚካሄደው አገር አቀፍ የሰርከስ ፌስቲቫል የስፖርቱን ዕድገትና አቅም ለዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ለማሳየት እንደሚረዳ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የኪነ ጥበብና ሥነጥበብ ፈጠራ ልማት ማስፋፊያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተፈሪ ተክሉ እንደተናገሩት፤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን አገር አቀፍ የሰርከስ ፌስቲቫል ከሚያዝያ 27 እስከ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ባህል ማዕከል ይካሄዳል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=98523
2.1K views07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 09:58:29
«በአዲስ አበባ የተገነቡ ፕሮጀክቶች በቀጥታየሕዝብን ችግር ፈቺ ናቸው»የተለያዩ ከተማ ከንቲባዎች
******************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ የተሠሩት ፕሮጀክቶች በቀጥታ ከሕዝብ ጋር የሚገናኙና ችግር ፈቺ መሆናቸውን የተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ከንቲባዎች ገለጹ።
የጂግጂጋ ከተማ ከንቲባ አቶ ዚያድ አብዲ፤ አዲስ አበባ ከተማ የተሠሩና በመሠራት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን መጎብኘታቸውን ገልጸው፤ ፕሮጀክቶቹ የሕዝብን ችግር ለመፍታት ታስበው የተገነቡና አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን መረዳታቸውን ተናግረዋል።
በቀጣይ ሌሎች ከተሞች ላይ ተመሳሳይ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያነሳሱ ፕሮጀክቶች በመዲናዋ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን አቶ ዚያድ ጠቁመዋል።
በተቀመጠላቸው ጊዜና ጥራት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=98495
1.8K views06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 12:11:15 ጠ/ሚ ዐቢይ የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው ከፈቱ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው ከፈቱ።
በምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር በጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ዳርቻ የሚገኘው የሀላላ ካብ በ'ገበታ ለሀገር' ኮይሻ ኮሪደር ፕሮጀክት አካል በሆነው ሃላላ ኬላ ሪዞርት ውስጥ ተካቶ የለማ ድንቅ የቱሪስት መስህብ ስፍራ መሆኑን ተናግረዋል።
ሀላላ ኬላ ሪዞርት ከመዝናኛ ስፍራነቱ በተጨማሪ ታሪካዊና ባህላዊ ሙዚየሞችና የምርምር ማዕከላትን ያካተተ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የዳውሮ ዞን ለአይን የሚማርኩ መልከዓ ምድር፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦች ባለቤት ስለመሆኑም አንስተዋል።
ኢትዮጵያውያን ለብዙ ስራዎች አእምሯችሁ እንዲከፈት የህዝብና አካባቢ ሰላም በእጅጉ በሚገኝበት የዳውሮ ዞን በመምጣት አዳዲስ ሀሳቦችን ለማፍለቅና ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት እንዲጎበኙም ጥሪ አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሸትን በማለባበስ እውነት ማድረግ እንደማይቻልና ውሸትን ቀባብቶ እውነት ለማስመሰል መሞከር እንደ ሐላላ ኬላ ያሉ ፕሮጀክቶችን ለመፍጠር አያስችልም ሲሉም አክለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊት የብዙ ባህልና ቋንቋዎች መገኛ ሀገር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንን ብዘኃነት እንደራስ መቀበልን መለማመድ ያስፈልጋል ብለዋል።
እንደ ዋልታ ዘገባ፤ ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊ ሀገር ናት የምንለው በባህልና ቋንቋ ብቻ ሳይሆን በተፈጥሮም እጅግ ማራኪ ሕብረ ብሔራዊ ቀለማትን በውስጧ የያዘች ሀገር መሆኗን መረዳት ያስፈልጋል፤ በዚህም አንዱ አካባቢ ከሌላው የተለየ የራሱ ተፈጥሯዊ ገፀ በረከቶችን የያዘ በመሆኑ በአግባቡ በማልማት መጠቀም እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
በመጨረሻም የዳውሮ ማህበረሰብ የሐላላ ኬላ ሪዞርት እንደቀደሙ አባቶች ቅርስ በመጠበቅ ለትውልድ እንዲያሸጋግርና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን እንዲያረጋግጥ አሳስበዋል።
1.6K views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 12:11:13
1.4K views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 11:29:01
የመደመር ትውልድ መፅሀፍ የትውውቅ መድረክ በድሬዳዋ
***************
(ኢ ፕ ድ)
የመደመር ትውልድ መፅሀፍ የትውውቅ መድረክ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ነው።
የትውውቅ መድረኩ በአስተዳደሩ ከሚገኙ ባለሀብቶች ጋር የሚካሄድ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
1.4K views08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 10:50:07
ከአምስት ሺህ በላይ መምህራን የተሳተፉበት ውይይት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል:: በውይይቱ ላይ መምህራን ጥያቄዎቻቸውን እና አስተያየቶቻቸውን በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
1.3K views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ