Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethpress — Ethiopian Press Agency/አማርኛ / E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethpress — Ethiopian Press Agency/አማርኛ /
የሰርጥ አድራሻ: @ethpress
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.66K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-22 09:48:46
ለበዓላቱ ከ255 ሺህ ኩንታል በላይ ጤፍ በሸማች ማህበራት አማካኝነት ተሰራጭቷል
****************
(ኢ ፕ ድ)

ለትንሳኤ በዓል እና ለኢድ አልፈጥር የምርት እጥረት እንዳያጋጥም ከ255 ሺህ ኩንታል በላይ ጤፍ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ሸማች ማህበራት መሰራጨቱን የኢትዮጵያ ሕብረት ሥራ ኮሚሽን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ሕብረት ሥራ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ጫልቱ ታምሩ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የትንሳኤ በዓልና የኢድ አልፈጥርን አስመልክቶ የምርት እጥረት እንዳይፈጠር በከተማዋ ከ255 ሺህ ኩንታል በላይ የጤፍ ምርት እንዲሰራጭ ተደርጓል።

እንደ ወይዘሮ ጫልቱ ከሆነ፤ በአዲስ አበባ ከተማ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=97419
653 views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 16:09:30
የትግራይ ክልልን የንግድ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት የሚያስችል ተጓዠ ባዛር ሊካሄድ ነው
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)

የትግራይ ክልልን የንግድ እንቅስቃሴን የማነቃቃት ዓላማ ያለውና "ሰላም ትግራይ ተጓዠ ባዛር ለቀጠናዊ ሰላም" በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ሥርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ተሻለ በልሁ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ ባዛሩ ባለፋት ጊዜ ተቋርጦ የነበረውን የትግራይ ክልል የንግድ ሥርዓት ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚያስችል ነው፡፡

ተጓዥ የንግድ ባዛሩ ሚያዝያ 21 ቀን 2015 ዓ.ም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት በመቀለ ከተማ እንደሚከፈትም ሚኒስትር ድኤታው ገልፀዋል፡፡

ባዛሩ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ማለትም በመቀለ፣ በውቅሮ፣ አዲግራትና በማይጨው ከተሞች ይካሄዳል ብለዋል፡፡

በባዛሩ መሰረታዊ የምግብ፣ የንጽህና መጠበቂያን ጨምሮ የተለያዩ ምርቶች ለተጠቃሚዎች የሚቀርቡ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

የንግድና ማህበራት ዘርፍ ተወካይ ዶክተር ደገላ ኤርገኖ በበኩላቸው ባዛሩ ተቋርጦ የነበረውን የንግድ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት የሚያስችልና ለአንድ ወር የሚቆይ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በማርቆስ በላይ
2.1K views13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 08:41:52
የአንድ ሺ 444ኛው ዒድ አል-ፊጥር የሶላትና የተክቢራ ስነስርአት ተጠናቀቀ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው አንድ ሺ 444ኛው የዒድ አል-ፊጥር የሶላትና የተክቢራ ስነስርአት በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም ተካሂዷል።

በዒድ ሶላት መርሃግብሩ  የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼይክ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ ኡስታዞች፣ ኢማሞችና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።

በሞገስ ተስፋ
1.8K views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 07:53:19
በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም የ"ተክቢራ" ስነ ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

የ"ተክቢራ" ስነ ስርዓት በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ አምላክን የማወደስ፣ የማስታወስና የማላቅ ሃይማኖታዊ የክንውን ስርዓት ነው።

ይህንኑ ሥነ ስትዓት ህዝበ ሙስሊሙ በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም እያከናወነ ይገኛል።

በመቀጠል የስግደት ስነ ስርዓት የሚከናወን ይሆናል።

በዓሉ የአንድነት፣ የፍቅርና የመተሳሰብ ባህልን የሚያጠናክር መሆኑንም የእስልምና እምነት ተከታዮች ተናግረዋል።

በሳሙኤል ወንድወሰን
1.5K views04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 07:29:34
"አገር ሰላም ሆና ዒድ አል- ፊጥርን በደማቅ ሁኔታ እያከበርን መሆናችን ታላቅ መንፈሳዊ ደስታን ፈጥሮልናል"
- የእስልምና እምነት ተከታዮች
******************
(ኢ.ፕ.ድ)

አገር ሰላም ሆና አንድ ሺ 444ኛውን ዒድ አል- ፊጥርን በደማቅ ሁኔታ እያከበርን መሆናችን ታላቅ መንፈሳዊ ደስታ ተሰምቶናል ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሰጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች ገለጹ።

በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም ዒድ አል-ፊጥርን እያከበሩ ያገኘናቸው አህመዲን ሁሴን እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ የነበረው የድርቅ፣ የግጭትና መሰል ችግሮች ተቀርፈው ዒድን በሰላም እያከበርን ነው። የእምነትን አስተምሮ በመከተል ዒድን ማክበር የሚቻለው አገር ሰላም ስትሆን ነው። ስለዚህ አገራችን ሰላም በመሆኗ ኢድን በማክበራችን ታላቅ መንፈሳዊ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል።

ሌላው የበዓሉ ታዳሚ አህመድ ሁሴን በበኩሉ በእስልምና ዒድ አል-ፊጥር የመከባበር፣ የመቻቻል የመደጋገፍ እሴት የሚታይበት ነው። ስለሆነም ዒድንየተቸገሩትን በመደገፍ፣ የታመሙትን በመጠየቅ የምናከብረው ነው ብሏል።

ኢትዮጵያ ሰላም ስለሆነች ኢድን በሰላም ማክበር ችለናል ነው ያሉት የበዓሉ ታዳሚዎች።

በሞገስ ተስፋ
1.4K views04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 14:35:11
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት
ሰላም የሁሉም መልካም ነገር መሠረት እንደመሆኑ፣ ያለ ሰላም ልማት የማይታሰብ ነው። ሕዝባችን ሰላሙን በማረጋገጥ ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር የማድረግ የጋራ ኃላፊነት አለብን:: በነቀምት ለነበረኝ ቆይታ እና ውይይት ሕዝቡን አመሰገናለሁ።
1.5K views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 11:27:10
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ነቀምቴ ከተማ ገቡ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት ነቀምቴ ከተማ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነቀምት ሲገቡ አባ ገዳዎች፣ ሐደ ሲንቄዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አመራሮችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዘግቧል::
1.9K views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 11:14:58
ለውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ከ163 ሺህ በላይ ዜጎች ሥልጠና እየወሰዱ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)
12ሺህ የሚጠጉ ከስደት ተመላሽ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል
በመላ አገሪቱ ከ163 ሺህ በላይ ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ወደ ውጭ አገር ሄዶ ሥራ ለመሥራት ሥልጠና በመውሰድ ላይ መሆናቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ። ከ12 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ከስደት የተመለሱ ዜጎችም የሥራ ዕድል መፈጠሩን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ አበበ ዓለሙ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከተሰጠው ዋና ዋና ተልዕኮዎች አኳያ ገበያ መር የክህሎት ልማትን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=97105
1.5K views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 10:20:50
በ201 የገጠር ከተሞች የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች ሊገነቡ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)
የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባቸው 201 የገጠር ከተሞች በ217 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች ሊገነቡ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳሉት፤ በሀገሪቱ እኤአ በ2030 መቶ በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ዕቅድ ተይዟል።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=97098

(ፎቶ ከኢንተርኔት)
1.4K views07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 09:40:48
ባንኩ በዲጂታል መተግበሪያ ከሁለት ነጥብ አንድ ትሪሊየን ብር በላይ አንቀሳቅሷል
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል መተግበሪያን በመጠቀም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በ549 ሚሊዮን ግብይቶች ከ2 ነጥብ አንድ ትሪሊየን ብር በላይ ማንቀሳቀሱን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል መተግበሪያዎችን በመጠቀም ለደንበኞቹ ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=97090
1.5K views06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ