Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-27 21:26:01
ለአዝማሪው ባንጃው እንዲህ ትለዋለህ ፦

ምን አይነት ገዢ ነው ፣ የገዢ ደንባራ
ብረት ተሸክሞ ፣ ብዕር የሚፈራ!

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ ብዕርህ ገና ከወረቀት ጋር እንኳ ሳይገናኝ ገዢዎቹ በፍርሃት ይርዳሉ!
5.2K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 19:27:42 አሁንም " ሳይቃጠል በቅጠል!" እላለሁ!

ተከታዩ ፅሁፍ ከአመት በፊት በዚሁ መንደር ያጋራሁት ቢሆንም ፣ ከሰሞኑ የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ የአማርኛና የታሪክ ትምህርት ክፍሎችን መዝጋቱን ተከትሎ ለማስታወስ ያህል በድጋሜ ልለጥፈው ወደድኩ!



አሁንም " ሳይቃጠል በቅጠል!" እላለሁ!

" ..የታሪክ ሽሚያ - የራሱን ታሪክ መፃፍ የማይችል የመከነ ትውልድ መገለጫ ነው!"

ታሪክ ጥሩም ሆነ መጥፎ በታሪክነቱ ተከትቦ ትውልድ ከመልካሙ ታሪክ እንዲማርበትና እንዲያስቀጥለው ፥ እኩይ የሆነውን ታሪክ ደግሞ ዳግም እንዳይከሰት ተግቶ የሚሰራበት ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ቀዲም አሻራ ነው፡፡

የአሁኑ ትውልድ የሚጠበቅበት ከትናንት ተምሮ ፥ በጎ ታሪኮችን አስቀጥሎ ነገን የመስራትና የራሱን ታሪክ ፅፎ ፥ ለተተኪው ትውልድ አውርሶ ማለፍ ነው፡፡

ያለፈ ታሪክ ዛሬውንም ሆነ ነገውን እንዲያበላሽ የሚፈቅድና የትናንቱን የቀድምት አባቶቹን አኩሪ ታሪክ ከመድገም ይልቅ ወደሽሚያ ውስጥ የሚገባ እርሱ ታሪክ መስራት የማይችል የመከነ ትውልድ ነው፡፡

አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚንስትር ሆኖ ከመጣ ጀምሮ የታሪክ ትምህርት በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ከሀምሳ በላይ ዩኒቨርስቲዎች መሠጠት አቁሟል፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ከዚህ " ቀደምት የነበረው የኢትዮጵያ ታሪክ የእኛ ታሪክ አይደለም!" ብለው የሚያምኑና ለታሪክ ሽሚያ ያሰፈሰፉ ነውረኛ የፖለቲካ ሀይሎች ፥ የሀገረ መንግስቱን ስልጣን በመያዛቸው ነው፡፡ እነዚህ ሀይሎች የቀደምት አባቶቻችንን አኩሪ ታሪክ በብሄር ሚዛን ላይ አስቀምጠው ለቅርጫ የተቀመጡ ብሎም የተፈፀመውንም ሆነ በትርክት የወለዱትን በጎ ያልሆነ ታሪክ ፥ ህዝብን እርስበርሱ በማባላት በደም የጨቀየ አሁናዊው የፖለቲካ ስልጣን ረሀባቸውን ለማስታገስ የሚጠቀሙ ከንቱዎች መሆናቸው የሚታመን ነው፡፡

የዛሬ ሁለት አመት ገደማ የኦሮሞ የፖለቲካ ኤሊት ከሚባሉት አብዛኛዎቹ በተገኙበት መድረክ ላይ የመታደም እድሉን አግኝቼ በውይይታችን ካነሳሁት ጭብጥ መካከል ፦

<< ..ኢትዮጵያ ውስጥ ታሪክን አንሻፎ የሚተረጉም ፥ በክፉም ሆነ በበጎ የነበረውን ታሪክ ያለፈ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው ብሎ የማያምን ፥ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አባቶቻችን ስለሀገር ብለው ሰርተው ያለፉትን ታሪክ በብሔር ቅርጫ ላይ አስቀምጦ ለመከፋፈልና ለመነጣጠቅ የሚተጋ ብሎም "ኢትዮጵያ" በምትባለው ሀገር ላይ በጋራ የሚያግባባ ተመሳሳይ ሀገራዊ ብያኔ የሌለው እንዲሁም ስያሜዋን ሁሉ የማይቀበል በፅንፈኝነትና በጥላቻ የሠከረ የፖለቲካ ኤሊት ባለበት ሀገር ፥ ማንኛውን ዘላቂ ሰላምና አብሮት ለማምጣት ነው ለውይይት የተቀመጥነው? ስለየቱ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ነው የምናወራው? ግጭትና እልቂትን እየደገሰ ያሐ የፖለቲካ ኢሊት ስለሰላምና ህዝባዊ አንድነት ለመስበክ መነሳቱ አሽሙር አይሆንምን ? ….. >> የሚል ሀሳብ አንስቼ ተከራክረን ሳንግባባ መለያየታችንን አስታውሳለሁ፡፡

በነገራችን ላይ ከኢህአዴግ/ህወሓት በፊት በነገስታቶችና በህዝቦች መካከል የነበረው ጥሩም ሆነ መጥፎ ታሪክ የተሰራው በሀገራዊ (ኢትዮጵያዊነት) ስሜት እንጂ በብሔር አጥር ስር አልነበረም፡፡ የሀገርን ሉአላዊነት ኢትዮጵያውያን በጋራ ሆነው ከውጭ ወራሪዎች ጋር ካደረጓቸው ጦርነቶችና ካስመዘገቧቸው አኩሪ ድሎች ባሻገር ፥ እርስበርስ ተደረጉ የሚባሉት ግጭቶች ለስልጣን ሽኩቻ (ንግስና) ካልሆነ በስተቀርም ለብሔር የበላይነት የተደረጉ አለመሆናቸውን በቀና ልቦና የኢትዮጵያን ታሪክ ለሚገነዘብ ሁሉ ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡

እናም " ለምን?" ብሎ የማይጠይቅ አድርባይና አጎብዳጁ የፖለቲካ ሀይል ፥ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ከመጡ በኃላ በኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያ እየተሰራ ያለውን ሀገር አፍራሽና ለማንም የማይጠቅም የታሪክ ሽሚያ ማስቆምና መታገል አለመቻሉ ፥ በጥላቻ የሠከረው ፣ ፅንፈኛውና ታሪክ ለመስራት ያልተፈጠረው ይህ የፖለቲካ ቡድን ፥ ከዩኒቨርስቲ የታሪክ ዲፓርትመንት መዝጋት አልፎ ፥ መጪው ትውልድ የሚታነፅበትን ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተዘረጋ የትምህርት ስርአት ውስጥ የተንሻፈፈ ፣ የተፋለሰ ብሎም ለራስ ፖለቲካዊ ፍጆታ ማሳኪያነት ብቻ የሚውል ትርክት ተቀርፆ በማስተማሪያነት ሊመጣ ችሏል፡፡

ከዚህ በመነሳት ነገ ሀገሪቱ አሁን ካለችበት ማጥ መውጣት ቀርቶ ወደከፋ የእልቂት ጎዳና እየተንደረደረች እንደምትገኝ ፥ የተሟላ ጤንነት ያለው ሙሉ ሠው ሁሉ ፣ በቀላሉ የሚረዳው ሀቅ ነው!

ሠላም!
5.3K views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 17:34:06 ምናልባት ትንፋሽ የሚሠበስቡበት አንፃራዊ ሰፊ ጊዜ ካገኙ ፦

ህወሓት በፖለቲካ ውሳኔ ወደ ምርጫ ፖለቲካው በአጭር ጊዜ ይመለሳል። ምናልባትም እንደነሬድዋን ሁሴን አይነት ጥርብ አገልጋይ ተፈልጎ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆኖ ይሾምና ቦርዱ ከስውር ወደ ግልፅ የብልፅግና ፓርቲ ቁጥር-2 ፅ/ቤትነት ደረጃ ያድጋል።

በርካታ አጋር የጎጥ ፓርቲዎች ይፈለፈላሉ። ያሉት ዘንግ አቀባይና እጅ አስታጣቢ አጋር ፓርቲዎችም የሰርተፍኬት እድሳት ይደረግላቸዋል። ''ህዝበ-ውሳኔ'' በሚሉት ተምሳሌታዊ ድራማ በርካታ ፖለቲካዊ መሻቶች ይፈፀማሉ።

ህወሓት ጥርስም መሬትም ይነክሳል።  የራያ ጉዳይ በፖለቲካዊ ውሳኔ (የተወሰነም ስለሆነ) ይቋጫል። የምዕራብ ጎንደር ''ህዝበ-ውሳኔ'' የሚባለው ድራማ ይተወንበታል። ተጨማሪ በዛ ያሉ ክልሎች ይወለዳሉ። አማራ አራት ትንንሽ ጎጣዊ ክልሎች ይሰፋለታል። አማራዊ መጠሪያ ሳይሆን ጎጣዊ ማንነት ጎልቶ ይወጣና ''አማራ ነኝ'' የሚለው በመላው ሀገሪቱና በአለም ላይ እንደኩርዶች የተበተነው ብቻ እንዲሆን በትጋት ይሰራል። ላለፉት አመታት ያየናቸው ዘግናኝ ግፍና መከራዎች ''ብሔራዊ ምክክርና ውይይት'' በሚባለው ድራማ በጊዜያዊ ማደንዘዣ ታልፈው ፣ የማደንዘዣው ሰአት ሲያልቅ በደረጃ ከፍ ብለው ይቀጥላሉ። 

ኦህዴድና ህወሓት በግልፅ በሚያስማማቸው ''ፀረ-አማራ ፕሮጀክት'' ዙሪያ ትብብራቸውን ሲቀጥሉ ፣ ህወሓት የሀገረ-መንግስቱን ፖለቲካ ለመቆጣጠርና ኦህዴድን ወደቀድሞው ስፍራው ለመመለስ የውስጥ ትግሏን አጧጡፋ ትቀጥላለች ፣ የሴራ መረቧን ሠፋ አድርጋ ትዘረጋለች!

ይኸው ነው!

ህዝባዊ አመፅና እምቢተኝነት ያማልዳል!
5.3K viewsedited  14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 15:59:46
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል !

ሰብሳቢዋ ላለፉት አመታት ተቋሙን የመሩ ሲሆን ፣ ለመልቀቃቸው በምክንያትነት ያነሱት ከጤና ጋር በተያያዘ ረፍት እንደሚያስፈልጋቸው በመግለፅ ቢሆንም በገዢው መንግስት ፍፁም አንባገነናዊነት ተማረው እና ከሚቋቋሙት በላይ በመሆኑ መሆኑን ምንጮች እየገለፁ ይገኛሉ።

ከሳምንት በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀውና ከሰላማዊ ፓርቲነት የተሰረዘው ህወሓት ዳግም በዚሁ መጠሪያ በፓርቲነት ተመዝግቦ ለመንቀሳቀስ ያቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ የህግ መሠረት የሌለው መሆኑን ጠቅሶ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።

ይህን በማስመልከት ሪፖርተር ትናንት ሰኔ 18/2015 ዓ.ም ይዞት የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ህወሓት ዳግም ወደምርጫ ፖለቲካው ለመግባትና በተፈረጀበት ስም ለመመዝገብ ከገዢው መንግስት (ቦርዱ?) ጋር ፖለቲካዊ ድርድር መጀመሩን አስታውቋል።

ይህ ዜናና የሰብሳቢዋ በፈቃዳቸው ከሀላፊነት መነሳት በግልፅ የመንግስትን ጣልቃገብነትና ቦርዱ ገለልተኛ ሆኖ ተቋሙን መምራት አለመቻሉን አመላካች ነው። ሌሎች በቦርዱ ህግ እስካሁን መሰረዝ ያለባቸው የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰርተፍኬታቸውን ብቻ ይዘው በፖለቲካ ምህዳሩ ውስጥ መቆየታቸውም ሌላው የቦርዱን ነፃ ሆኖ የመወሰን ስልጣን ጥያቄ ምልክት ውስጥ የከተተው መሆኑ አይዘነጋም። ገዢው ፓርቲም ለቦርዱ ህግ የማይተዳደርና ህግ የማይከተል መሆኑንም በተደጋጋሚ በአደባባይ ያሳየው እውነታ ሆኖ እናገኘዋለን ።
5.2K viewsedited  12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 20:00:27
5.5K views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 20:00:13 ቱጃሩ አላሙህዲንን ደብዛቸውን አጥፍቶ ሀብታቸውን እየቀረጠፈ ያለው ጅብ ማን ነው?

ታዋቂው ቢሊየነር ፣ በአንድ ወቅት በፎርብስ መፅሄት ከአፍሪካውያን ቢሊየነሮች ከቁንጮዎቹ ተርታ ተቀምጠው የነበሩት ፣ በአለም ላይ ከ80 በላይ ኩባንያ በኢትዮጵያ ደግሞ ከ40 በላይ ኩባንያዎች የነበሯቸው ፣ በአደባባይ ''ኢህአዲግ ነኝ!'' ብለው የፖለቲካ አቋማቸውንና የስርአቱ አጋርነታቸውን በመግለፅ የሚታወቁት ብሎም በበጎ አድራጎታቸውም የሚወሱት ፤ ሼህ ሙሐመድ አላሙዲን በሳኡዲ አረቢያ ለእስር ከተዳረጉ ጀምሮ ደብዛቸው መጥፋቱ ይታወቃል።

''ለውጡ'' እያሉ ከሚጠሩት የክፉ ዘመን ጅማሮ ላይ ጠ/ሚ አብይ ወደሳዑዲ ተጉዞ በመመለስ << ...ከሳዑዲ ንጉስ ጋር ተነጋግሬ እንደሚፈቱ ተስማምተናል። እኚህ ሰው በሰው ሀገር በባእዳን እጅ መታሰራቸው ኢትዮጵያን ከማሰር እኩል ነው። አሁን ከእኔ ጋር ያልመጡት በቤተሰቦቻቸው ጫና ነው። ስለዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደሀገራቸው እንደሚመለሱ ግን መቶ ፐርሰንት ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ! >> ብሎ በብሔራዊ ሚዲያ ተናግሮም ነበር።

ቱጃሩ ግን ጠሚው ይህን ቃል ከተናገሩ በኃላ እንኳ ጭራሽ ከሳኡዲ ንቅንቅ እንዳይሉ ካቴናው ጠብቆባቸው በቁም እስር ላይ ይገኛሉ። ከሀብት ማማ ተፈጥፍጠው ፣ ስማቸው የማይነሳ ፣ ታሪካቸው የማይወሳ ሆኖ ፣ ድርጅቶቻቸው ሁሉ ተዘርፈውና ተመናምነው ባለቤቱ እንደሞተበት ማሳ የአልፎ ሂያጁ ሁሉ መጫወቻ ሆነው ቀርተዋል።

ታዲያ! ከዚህ ''ለምንና እንዴት ?'' ብለን ጠይቀን ከማናውቀው የቱጃሩ መሰወርና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያለውን እውነታ ፥ ኢትዮ-360ዎች ትናንት << የሸህ አላሙዲንን ንብረት ዘርፎ እልቂት እየፈፀመ ያለው ቡድን >> በሚል ርዕስ ባሰናዱት ፕሮግራም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አቅርበውታል።

ይህን አስገራሚው የቂቤው ክህደት የተተነተነበት ፕሮግራም ፣ ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው ይከታተሉት!

https://www.youtube.com/live/PdzLIGMJbog?feature=share

ዘንዶው ፍፁም አይራራም!
5.4K views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 18:46:58
ጉርባዮ! ቁጡሪ ሂንቤክቱይ?

<< .... 50 ቢሊየን ችግኝ እየተከልን ነው! በቀላሉ እያንዳንዱን በ1 ዶላር እንኳ ብናሰላው 50 ቢሊየን ዶላር ነው! >> ጠሚ

- አጠቃላይ የኢትዮጵያ የቆዳ ስፋት 1,104,300 km² ነው።

የአለምን የደን ሽፋን 50 በመቶ የሚሸፍነው የአማዞን ጥቅጥቅ ዝናባማ ደን ፣ ስፋቱ ከ6 ሚሊየን km² በላይ ነው። ያ ማለት ይህ ደን ብቻውን ኢትዮጵያን 6 ጊዜ ደምረን ማለት ነው። ከትንሽ ወደትልቅ ቆጥረን የአሜሪካን 48 ስቴቶች ያክላል። ወይም ደግሞ እንግሊዝና አየርላንድን በአንድ ላይ ጨፍልቀን እንኳ በ17 ጊዜ ይበልጣቸዋል። በሌላ ስሌት በአፍሪካ ትልቁ ደን የኮንጎ ባሲን ፣ የኢንዶኔዥያ ደን ተደምሮ እንኳ ከአጠገቡ አይደርሱበትም።

ታዲያ በዚህ የአማዞን ደን የሚገኙት 390 - 400 ቢሊየን የሚገመቱ ዛፎች ሲሆኑ ፣ ወደ16 ሺህ አይነት የዛፍ ዝርያዎችም አሉ!

ታዲያ! ይህን ሁሉ ችግኝ ድፍን ኢትዮጵያ ላይ ተክለን ፣ ህዝቡን ያለቤት ጫካ ውስጥና በዋሻ እንዲኖር ከምንፈርድበት ፣ በ50 ቢሊየን ዶላሩ ከአማዞን ጥቅጥቅ ጫካ ትንሽ ገመስ አድርገን ለምን አንገዛም?

ባሻዬ! አለም ባንክ ግን << 2 ቢሊየን ዶላር አላበድርም! >> ብሎ ገግሞ ቀረ አይደል?

ሠፊው ህዝብ እሱው ይሁንህ!
4.9K views15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 20:21:42 ''በኦነግ ሸኔ ታግተው ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ለተጠየቁ ሹፌሮች ገንዘብ እየተሰበሰበ ነው'' ተባለ!

ከአምስት ቀን በፊት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ገርበ ጉራቻ ከተማ አካባቢ ለታገቱ ከ50 በላይ ሹፌሮች ፣ እገታውን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የጠየቁትን ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ህዝቡ እየሰበሰበ መሆኑን አዲስ ማለዳ ከምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የሥራ ኃላፊዎች ሰምታለች።

በዚህም በደብረ ማርቆስ እና ደንበጫ መካከል አማኑኤል ከተማ ላይ የታገቱ ሹፌሮች ይለቀቁልን በሚል ለሦስት ቀናት ያህል መንገድ ተዘግቶ እንደነበር የተጠቀሰ ሲሆን ፤ መፍትሔ ባለመገኘቱ የታጋቾቹ ቤተሰቦች በየቦታው ጨርቅ አንጠፈው የተጠየቁትን ገንዘብ በመለመን ላይ ናቸው ተብሏል።

"እኛም ግራ ገብቶናል" ያሉ አንድ የሥራ ኃላፊ ፤ "አብዛኛው ሹፌሮች የታገቱት ከዚህ አካባቢ ስለሆነ ሕዝቡ ልጆቻችን ይፈቱልን በማለት መንገድ ተዘግቶ ነበር።" ካሉ በኋላ ፣ "ሕግ እና መንግሥት ባለበት አገር ሰው ታግቶ በሚሊየን ክፈሉ እየተባለ ነው፣ አጣርታችሁ ለመንግሥት ይፋ አድርጉ የሚሰማ ካለ።" ሲሉ ተደምጠዋል።

አክለውም፤ "ከታገቱት ውስጥ ዕድል ቀንቶት ለአንድ ሰው አንድ ሚሊየን ከፍሎ የሚለቀቅ አለ። አልፎ አልፎ እየከፈሉ እየተለቀቁ ነው፣ ክፍሎ ያልተለቀቀም አለ" ብለዋል።

የሥራ ኃላፊው "ገርበ ጉራቻ አሊዶሮ አካባቢ ያለው የመንግሥት አካል በዚህ ጉዳይ ለምንድነው ማብራሪያ የማይሰጠው?" ሲሉ ጠይቀው፤ "የፀጥታ ኃይል፣ መንግሥትና ህግ ባለበት አገር በተደጋጋሚ ድርጊቱ መፈፀሙ ያሳዝናል።" ብለዋል።

ከ50 በላይ ሹፌሮች ታግተው ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ነው የተጠየቀው ያሉት የሥራ ኃላፊው፤ "በዚህ ኑሮ ውድነት ምንም የሌለው ድሃ ልጆቹን ለማትረፍ በየቦታው ጨርቅ አንጥፎ እየለመነ ነው። የሚመለከተው አመራር ማብራሪያ ይስጥ።" ሲሉ አሳስበዋል።

ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው እና በመንግሥት ኦነግ ሸኔ ተብሎ በአሸባሪነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡድን በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሰዎችን ከመግደልና ከማፈናቀል ባለፈ ንጹሃን ዜጎችን በማገት ከፍተኛ ገንዘብ እየጠየቀ ይገኛል።

አዲስ ማለዳ ባለፈው ሰኔ 10/2015 በሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ አቅራቢያ ከ50 በላይ የከባድ መኪና እና የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ተሽከርካሪዎች ሹፌሮች ፣ እረዳቶችና ተሳፍሪዎች መታገታቸውን መዘገቧ የሚታወስ ሲሆን፤ ድርጊቱ ሲፈጸም በቅርብ እርቀት የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ አካላት "ከበላይ አካል ትዕዛዝ አልተሰጠንም" በማለት የታገቱ ዜጎችን ሊታደጉ አለመቻላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች መግለጻቸው አይዘነጋም።

//ዘገባው ፦ የአዲስ ማለዳ ነው//
5.3K views17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 18:26:49
አቤት ውርደት…!

"…የእኛው ጉድ ወሬ አማረለኝ ብሎ እንዲህ ይለዋል። እዚ በእነ አገኘሁ ተሻገር ላይ መንበጫበጭ በጌታቸው ረዳ ላይ ማላገጥ ለምዶ እኮ ነው። አዲሱ የዓለም ባንክ መሪ ዕድለኛ ነህ፣ የሚታይ ሥራ ለውጥ ሳታመጣ ቱ ምን አለ በለኝ፣ ጌታ ምስክሬ ነው 2 ዓመት በቦታው ላይ አትቆይም ዓይነት ነገር ያለው መሰለኝ ። እኔ ራሴ እኮ እንግሊዝኛ ያለመማሬ እንደጎዳኝ አሁን አሁን ነው በደንብ የገባኝ። 

"…የዓለም ባንኩም መሪ ሲመል ምን ቢለው ጥሩ ነው። "የፈጣሪ ያለህ እኔ እኮ የተመረጥኩት ለ 5 ዓመታት ነው። አባቴ ምን እንዳወራህ አልገባኝም። ነገር ግን አንድ የገባኝ ቁም ነገር ይህ ንግግርህ ስላንተ ማንነት ብዙ ነገር ይነግረኛል ወይም (በሾርኔ ኢትዮጵያውያኖች በየቀኑ በአንተ የተነሣ ዋይ ዋይ የሚሉት በምን ዓይነት መሪ እየተመሩ እንደሆነ ነው አሁን የገባኝ) በልቡም ሐበሾች ሆይ ጭንቀታችሁን አሁን ገና ነው ተረዳሁት፣ ያ በጀርመን ስደተኛው ሰውዬ ዘመድኩን ዘመዴ የምትሉት "ይሄ የ7ተኛ ጨ ሰው ነው፣ ዱፍትርናውም የቁጩ ነው ዓይነት መልስ ነው የሰጠው)

"…ይሄን አረመኔ ሰው መሳይ በሸንጎ፣ በየሄደበት፣ በየደረሰበት፣ አፉን በከፈተበት ሁሉ የንፁሐኑ ደም እየተከተለው ያዋርደው ብለን የረገምነው እርግማን አሁን በግልጽ እየሠራ መጥቷል። አሳማ ሊፒስቲክ ብትቀባ አሳማነቷ እኮ አይቀየርም። አይለወጥም። መሃይምነትን ሱፍ መልበስ ሊቅ አያደርገውም።

"…You is my president ገና ከዚህ በላይ ትዋረዳታለህ። መሳቂያ መሳለቂያም ትሆናታለህ። ኢትዮጵያ ግን አንተ መቃብር ላይ ሰንደቋን ተክላ ትነሣለች። አይ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ምን ብለው ቢረግሙን ይሆን እንዲህ ዓይነት ሼምለስ ልቡሰ ሥጋ ጋኔል ላይ የጣለን…?

"…ምንአለ ዝም ቢል…?

@ዘመድኩን በቀለ
5.1K views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 23:20:10
የጉድ ሀገር ገንፎ እያደር ይፋጃል!

<< ሌባ ሁላ ፣ ሌባ ሁላ ...! >>

USAID በሚሊዮን ለሚቆጠሩ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለሚሹ ኢትዮጵያውያን የሚያደርገውን የምግብ እርዳታ ፣ በመንግስት ከፍተኛ ሌብነትና የዘረፋ እቅድ ምክንያት ለጊዜው ሙሉ በሙሉ ማቋረጡን ገልጿል!

የዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት (USAID) ዛሬ ይፋ ባደረገው መግለጫው ፣ ከመንግሥት ሾልከው በወጡ ሰነዶች ፣ ከአለምአቀፍ ለጋሶች ለተራቡ ኢትዮጵያውያን የሚሰጠውን እርዳታ የኢትዮጵያ መንግስት ከክልል መንግስታት ጋር በመቀናጀት በከፍተኛ ሁኔታ ለመዝረፍ መዘጋጀቱን አረጋግጫለሁ ብሏል።

መረጃውን ሮይተርስና ዋሽንግተን ፖስትን የመሳሰሉት አለምአቀፍ ሚዲያዎች እየተቀባበሉት ይገኛሉ !

ከዚህ ቀደም የአለም የምግብ ፕሮግራም <<በኢትዮጵያ አሳሳቢ የረሀብ አደጋ ላይ ለሚገኙት ቀሚሊየኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እርዳታ ላድርግ!>> ሲል ፥ የገዛ ዜጎቹ ዳቦ አጥተው እየተራቡና እያለቁ << ስንዴውን ከእኔ ግዙኝ! >> ብሎ በዶላር የቸበቸበው የሚለውን ዜና ሰምተን ስንገረም ፥ ጉደኛው መንግስታችን ዛሬ ደግሞ ፦

<< የሚላስ የሚቀመስ አጥተው በጠኔ እየረገፉ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለመመገብ ከአለም መንግስታት የተደረገ እርዳታን የገዛ መንግስታቸው እየዘረፈ በማስቸገሩ ተቋረጠ! >> የሚለውን ዜና በአለምአቀፍ ሚዲዲያዎች ሲነገርለት መስማት በራሱ የህሊና ሰላም ያሳጣል! ምን አይነት አረመኔነት ነው ግን ? ምን አይነት ሞራለ ቢስነትስ ነው?

ኧረ የእናንተስ ከፋ!
4.0K views20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ