Get Mystery Box with random crypto!

ምናልባት ትንፋሽ የሚሠበስቡበት አንፃራዊ ሰፊ ጊዜ ካገኙ ፦ ህወሓት በፖለቲካ ውሳኔ ወደ ምርጫ | ዘሪሁን ገሠሠ

ምናልባት ትንፋሽ የሚሠበስቡበት አንፃራዊ ሰፊ ጊዜ ካገኙ ፦

ህወሓት በፖለቲካ ውሳኔ ወደ ምርጫ ፖለቲካው በአጭር ጊዜ ይመለሳል። ምናልባትም እንደነሬድዋን ሁሴን አይነት ጥርብ አገልጋይ ተፈልጎ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆኖ ይሾምና ቦርዱ ከስውር ወደ ግልፅ የብልፅግና ፓርቲ ቁጥር-2 ፅ/ቤትነት ደረጃ ያድጋል።

በርካታ አጋር የጎጥ ፓርቲዎች ይፈለፈላሉ። ያሉት ዘንግ አቀባይና እጅ አስታጣቢ አጋር ፓርቲዎችም የሰርተፍኬት እድሳት ይደረግላቸዋል። ''ህዝበ-ውሳኔ'' በሚሉት ተምሳሌታዊ ድራማ በርካታ ፖለቲካዊ መሻቶች ይፈፀማሉ።

ህወሓት ጥርስም መሬትም ይነክሳል።  የራያ ጉዳይ በፖለቲካዊ ውሳኔ (የተወሰነም ስለሆነ) ይቋጫል። የምዕራብ ጎንደር ''ህዝበ-ውሳኔ'' የሚባለው ድራማ ይተወንበታል። ተጨማሪ በዛ ያሉ ክልሎች ይወለዳሉ። አማራ አራት ትንንሽ ጎጣዊ ክልሎች ይሰፋለታል። አማራዊ መጠሪያ ሳይሆን ጎጣዊ ማንነት ጎልቶ ይወጣና ''አማራ ነኝ'' የሚለው በመላው ሀገሪቱና በአለም ላይ እንደኩርዶች የተበተነው ብቻ እንዲሆን በትጋት ይሰራል። ላለፉት አመታት ያየናቸው ዘግናኝ ግፍና መከራዎች ''ብሔራዊ ምክክርና ውይይት'' በሚባለው ድራማ በጊዜያዊ ማደንዘዣ ታልፈው ፣ የማደንዘዣው ሰአት ሲያልቅ በደረጃ ከፍ ብለው ይቀጥላሉ። 

ኦህዴድና ህወሓት በግልፅ በሚያስማማቸው ''ፀረ-አማራ ፕሮጀክት'' ዙሪያ ትብብራቸውን ሲቀጥሉ ፣ ህወሓት የሀገረ-መንግስቱን ፖለቲካ ለመቆጣጠርና ኦህዴድን ወደቀድሞው ስፍራው ለመመለስ የውስጥ ትግሏን አጧጡፋ ትቀጥላለች ፣ የሴራ መረቧን ሠፋ አድርጋ ትዘረጋለች!

ይኸው ነው!

ህዝባዊ አመፅና እምቢተኝነት ያማልዳል!