Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን | ዘሪሁን ገሠሠ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል !

ሰብሳቢዋ ላለፉት አመታት ተቋሙን የመሩ ሲሆን ፣ ለመልቀቃቸው በምክንያትነት ያነሱት ከጤና ጋር በተያያዘ ረፍት እንደሚያስፈልጋቸው በመግለፅ ቢሆንም በገዢው መንግስት ፍፁም አንባገነናዊነት ተማረው እና ከሚቋቋሙት በላይ በመሆኑ መሆኑን ምንጮች እየገለፁ ይገኛሉ።

ከሳምንት በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀውና ከሰላማዊ ፓርቲነት የተሰረዘው ህወሓት ዳግም በዚሁ መጠሪያ በፓርቲነት ተመዝግቦ ለመንቀሳቀስ ያቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ የህግ መሠረት የሌለው መሆኑን ጠቅሶ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።

ይህን በማስመልከት ሪፖርተር ትናንት ሰኔ 18/2015 ዓ.ም ይዞት የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ህወሓት ዳግም ወደምርጫ ፖለቲካው ለመግባትና በተፈረጀበት ስም ለመመዝገብ ከገዢው መንግስት (ቦርዱ?) ጋር ፖለቲካዊ ድርድር መጀመሩን አስታውቋል።

ይህ ዜናና የሰብሳቢዋ በፈቃዳቸው ከሀላፊነት መነሳት በግልፅ የመንግስትን ጣልቃገብነትና ቦርዱ ገለልተኛ ሆኖ ተቋሙን መምራት አለመቻሉን አመላካች ነው። ሌሎች በቦርዱ ህግ እስካሁን መሰረዝ ያለባቸው የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰርተፍኬታቸውን ብቻ ይዘው በፖለቲካ ምህዳሩ ውስጥ መቆየታቸውም ሌላው የቦርዱን ነፃ ሆኖ የመወሰን ስልጣን ጥያቄ ምልክት ውስጥ የከተተው መሆኑ አይዘነጋም። ገዢው ፓርቲም ለቦርዱ ህግ የማይተዳደርና ህግ የማይከተል መሆኑንም በተደጋጋሚ በአደባባይ ያሳየው እውነታ ሆኖ እናገኘዋለን ።