Get Mystery Box with random crypto!

ቱጃሩ አላሙህዲንን ደብዛቸውን አጥፍቶ ሀብታቸውን እየቀረጠፈ ያለው ጅብ ማን ነው? ታዋቂው ቢሊየነ | ዘሪሁን ገሠሠ

ቱጃሩ አላሙህዲንን ደብዛቸውን አጥፍቶ ሀብታቸውን እየቀረጠፈ ያለው ጅብ ማን ነው?

ታዋቂው ቢሊየነር ፣ በአንድ ወቅት በፎርብስ መፅሄት ከአፍሪካውያን ቢሊየነሮች ከቁንጮዎቹ ተርታ ተቀምጠው የነበሩት ፣ በአለም ላይ ከ80 በላይ ኩባንያ በኢትዮጵያ ደግሞ ከ40 በላይ ኩባንያዎች የነበሯቸው ፣ በአደባባይ ''ኢህአዲግ ነኝ!'' ብለው የፖለቲካ አቋማቸውንና የስርአቱ አጋርነታቸውን በመግለፅ የሚታወቁት ብሎም በበጎ አድራጎታቸውም የሚወሱት ፤ ሼህ ሙሐመድ አላሙዲን በሳኡዲ አረቢያ ለእስር ከተዳረጉ ጀምሮ ደብዛቸው መጥፋቱ ይታወቃል።

''ለውጡ'' እያሉ ከሚጠሩት የክፉ ዘመን ጅማሮ ላይ ጠ/ሚ አብይ ወደሳዑዲ ተጉዞ በመመለስ << ...ከሳዑዲ ንጉስ ጋር ተነጋግሬ እንደሚፈቱ ተስማምተናል። እኚህ ሰው በሰው ሀገር በባእዳን እጅ መታሰራቸው ኢትዮጵያን ከማሰር እኩል ነው። አሁን ከእኔ ጋር ያልመጡት በቤተሰቦቻቸው ጫና ነው። ስለዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደሀገራቸው እንደሚመለሱ ግን መቶ ፐርሰንት ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ! >> ብሎ በብሔራዊ ሚዲያ ተናግሮም ነበር።

ቱጃሩ ግን ጠሚው ይህን ቃል ከተናገሩ በኃላ እንኳ ጭራሽ ከሳኡዲ ንቅንቅ እንዳይሉ ካቴናው ጠብቆባቸው በቁም እስር ላይ ይገኛሉ። ከሀብት ማማ ተፈጥፍጠው ፣ ስማቸው የማይነሳ ፣ ታሪካቸው የማይወሳ ሆኖ ፣ ድርጅቶቻቸው ሁሉ ተዘርፈውና ተመናምነው ባለቤቱ እንደሞተበት ማሳ የአልፎ ሂያጁ ሁሉ መጫወቻ ሆነው ቀርተዋል።

ታዲያ! ከዚህ ''ለምንና እንዴት ?'' ብለን ጠይቀን ከማናውቀው የቱጃሩ መሰወርና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያለውን እውነታ ፥ ኢትዮ-360ዎች ትናንት << የሸህ አላሙዲንን ንብረት ዘርፎ እልቂት እየፈፀመ ያለው ቡድን >> በሚል ርዕስ ባሰናዱት ፕሮግራም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አቅርበውታል።

ይህን አስገራሚው የቂቤው ክህደት የተተነተነበት ፕሮግራም ፣ ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው ይከታተሉት!

https://www.youtube.com/live/PdzLIGMJbog?feature=share

ዘንዶው ፍፁም አይራራም!