Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Fm 107.8

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofm107dot8
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.12K
የሰርጥ መግለጫ

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-24 13:54:54
የተከበራችሁ የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አድማጮች ሬድዮ ጣቢያችን ፋሪ ከሚገኘው ዋናው ማሰራጫ የቴክኒክ እክል ስለገጠመዉ በቅርቡ በሞገዳችን እንደምንመለስ ማሳወቅ እንወዳለን ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
"የኢትዮጵያውያን"
2.3K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 11:50:25
በጎረቤት ሀገር ሱዳን አዉሮፕላን ተከሰከሰ፡፡

በፖርት ሱዳን አንቶኖቭ አዉሮፕላን ተከስክሶ 9 ሰዎች መሞታቸዉ ተሰምቷል፡፡

በአደጋዉ ህይዎታቸዉን ካጡት መካከል አራቱ ወታደሮች መሆናቸዉ ታዉቋል፡፡
በፖርት ሱዳን ዛሬ ጠዋት ለደረሰዉ የአዉሮፕላን መከስከስ አደጋ መንስኤዉ የቴክኒክ ብልሽት መሆኑን የዘገበዉ አልጄዚራ ነዉ፡፡

አንድ ህፃን ከአደጋዉ መትረፉንም የሀገሪቱ ጦር አስታዉቋል፡፡

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube

https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.8K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 11:48:51
ዩክሬን ተተኳሽ ጥይቶችንና የጦር መሳሪያ ቅሪቶችን ከግዛቷ ለማስወገድ ከ7መቶ ዓመት በላይ ይፈጅባታል ተባለ::

ሀገረ ዩክሬን በጦርነቱ ምክንያት አብዛኛዉ ግዛቷ በጦር መሳሪያ ቅሪቶችና በተተኳሽ ጥይቶች በመሸፈኑ ይህንን ለቅሞ ለማስወገድ 7 መቶ 57 ዓመት እንደሚወስድባት አንድ ጥናት አመልክቷል፡፡

ጦርነቱ ዩክሬንን በአለማችን በማዕድን የተሸፈነች ሀገር እንዳደረጋትም ሪፖርቱ አስታዉቋል፡፡
አንድ ሶስተኛ የሚሆነዉ የዩክሬን ግዛት የጦርነቱ ሰለባ መሆኑን የገለጸዉ ጥናቱ ፤ ይህም ብዙ በተቀጣጣይና መርዛማ የጦር መሳሪያ ቅሪቶች የተሸፈነ ነዉ ተብሏል፡፡

በቁጥር ሲገለፅም 1 መቶ 73 ሺህ 5መቶ 29 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፤ ይህም ከዩራጓይ የቆዳ ስፋት እኩል እንደማለት ነዉ፡፡
እነዚህ ተቀጣጣይና ያልፈነዱ የጦር መሳሪያ ቅሪቶች ከ 3 መቶ በላይ ንጹሃንን እንደገደሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ያመላክታል፡፡

ዩክሬን በእነዚህ አደገኛ የጦር መሳሪያ ቅሪቶች እንደትወረር የእነ አሜሪካ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋዕፅኦ እንዳደረጉም አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡
የክላስተር ቦምቦች ፍንጥርጣሪ ደግሞ ለቀጣዩ የዩክሬን ትለዉልድ አደጋ እደሚሆንም ድርጅቱ አስጠንቅቋል፡፡

አሜሪካ እነዚህ የጦር መሳሪያ ፍንጥርጣሪና ተቀጣጣዮችን ለመልቀም የሚደረገዉን ጥረት ለመደገፍ 95 ሚሊን ዶላር ድጋፍ ማድረጓም ተሰምቷል፡፡
እናም ዩክሬናዉያን በጦርነቱ ወቅት ብቻም ሳይሆን ከጦርነቱ በኋላም የከፋ ችግር እያንዣበባቸዉ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም
2.5K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 17:56:06
ደምበል ኮሌጅ ተማሪዎቹን አስመረቀ።

ኮሌጁ በቀን እና በማታ መርሃ ግብር  ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል።

ደምበል ኮሌጅ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣በአውቶሞቲቨ በአካውንቲንግ ፣በነርሲንግ በፋርማሲ እና በሌሎችም መርሃ ግብር ነው ተማሪዎቹን ያስመረቀው።

በጠቅላላው 350 ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል።

የኮሌጁ የቦርድ ሰብሳቢ እና የኮሌጁ ባለቤት የሆኑት አቶ ተሾመ በቀለ እንደተናገሩት የልፋታችሁ ውጤት ለማየት ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ኮሌጁ በቀጣይ አዳዲስ የትምህርት አይነቶችን ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል።



የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን ደመላሽ ከበደ አመታትን በድካም አሳልፋችሁ ለዛሬ ቀን ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ደምበል ኮሌጅ 2015 አመት የዲግሪ መርሃ ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል።

ደምበል ኮሌጅ የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ በየጊዜው ኮሌጁን እያስገመገመ እንደሚገኝ የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን ተናግረዋል።

ለቀጣይ የትምህርት ዘመን ምዝገባ እንደጀመረ አስታውቋል።


በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም
3.2K views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 15:49:14
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዩክሬን እንዲጎበኙ ከፕሬዝዳንቱ ግብዣ ቀረበላቸው፡፡

ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ዩክሬንን እንዲጎበኙ ግብዣ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንኪ ጋር በስልክ ከተወያዩ በኃላ ነው ዩክሬን እንዲጎበኙ ጥሪ የተደረገላቸው ተብሏል፡፡

ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው ዩክሬን፣ለኢትዮጵያ 300 ሺህ ቶን ስንዴ ማቅረቧ የተሰማ ሲሆን፣ከሰሞኑ በጥቁር ባህር በኩል ለዓለም ሃገራት ስንዴ ለማቅረብ የነበረው ስምምነት ሩስያ ከሰሞኑ ከስምምነቱ መውጣቷ ይታወሳል፡፡

ኬቭን እንዲጎበኙ የተጋበዙት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ግብዣውን ስለመቀበላቸው እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው ዩክሬን በጦርነት ውስጥም ሆና ለኢትዮጵያ 300 ሺህ ቶን ስንዴ አቅርባለች ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ዩክሬን ተጨማሪ 90 ሺህ ቶን ስንዴ ለኢትዮጵያ እንደምታቀርብ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube

https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
4.1K viewsedited  12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 11:46:29
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቢኒያም በለጠ የክብር ዶክትሬት ሰጠ

የመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ሕሙማን ማዕከል መሥራች ቢኒያም በለጠ ለባረከተው በጎ ስራ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የክብር ዶክተሬት ዛሬ ተሰጥቶታል።

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በማታና በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 8 ሺህ 642 የቅድመ ምረቃና ድሕረ ምረቃ ተማሪዎችን በሚሊኒየም አዳራሽ እያስመረቀ ነው።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ሌሎችም ተገኝተዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 13ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube

https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
4.7K views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 11:44:15
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ባስመረቀበት ወቅት ነው ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት የሰጠው፡፡

ጂጂን ማክበር ጥበብን ማክበር ነው ያሉት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር)÷ጂጂን ማክበር የኢትዮጵያን ታሪክና ጀግኖችን እንዲሁም ፍቅርንና አንድነትን ማክበር ነውም ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 13ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube

https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
3.7K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 11:22:46
የወለኔ ህዝብ ተደጋጋሚ የማንነት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን የወለኔ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ፈይሰል አብዱላዚዝ ተናገሩ፡፡

ለ30 ዓመታት የቆየው የወለኔ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን የወለኔ ህዝብ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ፈይሰል አብዱላዚዝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ፓርቲያቸው ‘የወለኔ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ’ በሀገሪቱ ፖለቲካ ሰፊ ተሳትፎ ያደረገ እንዲሁም በሁሉም የሀገሪቱ ምርጫዎች ላይ የተሳተፈ ቢሆንም የህዝባቸው የማንነት ጥያቄ ግን ምላሽ ሊያገኝ አለመቻሉን አስታውቀዋል፡፡

በጉራጌ ዞን ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኘው ወለኔ የራሷ ቋንቋ፣ባህል እና ማንነት ያላት ናት የሚሉት ሊቀመንበሩ የሚቀርቡ የማንነት ጥያቄያች ሰሚ ሊያገኙ አለመቻላቸው እንቆቅልሽ ሆኖብኛል ብለዋል፡፡

በደቡብ ክልል ካሉ ስድስት የማንነት ጥያቄዎች አንዱ የሆነው የወለኔ ህዝብ የማንነት ጥያቄን በተመለከተ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ይዞት ውሳኔ እየተጠባበቁ እንደሆነም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

አቶ ፈይሰል ፓርቲያቸው እየታገለ የሚገኘው የወለኔ ህዝብ የራሱ የሆነ አስተዳደር እንዲኖረው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጉዳዩን አጥንቶ በቅርቡ ውሳኔ ከሚሰጥባቸው የማንነት ጥያቄዎች አንዱ እንደሚሆንም ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ሐምሌ 13ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube

https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.7K viewsedited  08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 11:11:56 በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የመሳሪያ ብልሽት አጋጥሟል በሚል የኩላሊት ህመምተኞች የዕጥበት አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸዉን ተናገሩ፡፡

ስምንት እና ከዚያ ዓመት በላይ በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የኩላሊት ዕጥበት ሲያደርጉ ነበሩ ፣ ወደ 43 የሚጠጉ የኩላሊት ህመምተኞች ቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ማጠብ ስላልቻለ ከአለፉት 15 ቀናት ጀምሮ በሚኒሊክ ሆስፒታል ተባባሪነት የዕጥበት አገልግሎት ሲያገኙ እንደነበር ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በሚኒሊክ ሆስፒታል ለ 15 ቀናት ያህል የዕጥበት አገልግሎት ስናገኝ ብንቆይም ባሳለፍነው ቅዳሜ ለመታጠብ ስንሄድ ማክሰኞ እንዳትመጡ በሚል ከሚኒሊክ ሆስፒታል ወጥተናል ፣ ወደ ጳዉሎስ ሆስፒታል ብንሄድም፤ ሆስፒታሉ ምንም ማድረግ ስለማልችል በግላችሁ ታጠቡ የሚል ምላሽ ሰጥቶናል” ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ቅሬታቸዉን አቅርበዋል፡፡

ይህንን ጉዳይ ለማጣራት ወደ የኩላሊት ህመምተኞች በጎ አድራጎት ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ጋር ደዉለን ያለዉን ነገር ስንጠይቅ ከዘዉዲቱ ሆስፒታል ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል አስፈላጊዉ የማጠቢያ አሲድ እንዲላክ መነጋገራቸዉን እና አሲዱ ለሚኒሊክ ሆስፒታል መድረሱን ማረጋገጣቸዉን ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ሆኖም በድጋሚ ቅሬታ አቅራቢዎቸን ስናነጋግር ምንም ዓይነት የተሰጣቸዉ መፍትሄ እንደሌለ እና አሁን ባለው ሁኔታ ዛሬም ፣ነገም ሆነ ከነገ በስትያ የኩላሊት ዕጥበት ማግኘት የሚችል ታካሚ አለመኖሩን ነግረዉናል፡፡

ከኩላሊት ህመምተኞች በጎ አድራጎት ማህበርም የተሰጣቸዉ ምላሽ ተገቢ ያልሆነ መሆኑንም ነዉ ጨምረዉ የነገሩን፡፡

የሚኒሊክ ሆስፒታል የማጠቢያ ማሽን የአገር ዉስጥ አሲድን ስለማይቀበል የቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ማሽን ቢሆንም አገልግሎት ሊሰጠን የሚችለዉ ፣ የሆስፒታሉ ማሽን በመበላሸቱ ምንም ለማድረግ አልተቻለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በትናንትናው እለት ጤና ሚኒስቴር ሄደዉ እንደነበር የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ሁሉም ስብሰባ ላይ በመሆናቸዉ ተመልሰዉ መምጣታቸዉን ገልጸዋል፡፡

ጤና ሚኒስቴር አሲዱ ተገዝቶ ጉምሩክ ላይ መሆኑን ነግሮናል ያሉን ሲሆን ቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታልም ችግሩን ለማስተካከል እየሰራ መሆኑን እንዳሳወቃቸዉ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የኩላሊት ህመምተኞች በጎ አድራጎት ማህበር በበኩሉ በትናንትናው ዕለት አገልግሎቱ በሚኒሊክ ሆስፒታል መጀመሩንና ለታካሚዎች እየተደወለ የዕጥበት አገልግሎት ሲሰጣቸዉ እንደነበር ማረጋገጡን የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሞን አሰፋ ነግረዉናል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 13ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube

https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.5K viewsedited  08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 10:50:48
"ችግር ፈቺ"፣ የሃሳብ ግብዓት ያስገኛል የተባለ ውይይት ለማካሄድ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን በቅርቡ ከኢዜማ የለቀቁ አመራሮች እና አባላት አሳወቁ፡፡

ያልዳበረው የውስጠ -ፓርቲ የፖለቲካ ባህልና አሠራር ለተቃዋሚ ፖርቲዎች የትግል ጉዞ መዳከም ምክንያት ነው ብለዋል ስለውይይቱ ዝግጅት በተመከተ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላኩት መግለጫ፡፡

እነዚህን መሠረታዊ ከሀገራዊ ህልውና፣ ሰላምና እድገት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን ችግሮች ለመቅረፍ እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ፖለቲካ ድርጅታዊ ኃይል (ፓርቲ)፣ የፖለቲካ ባህላችንን በአፅንኦት መመልከት ፣ ጥሩውን ለመጠበቅና ለማሳደግ ኃላፊነት መውሰድ፣ መጥፎውን በመንቀስና ለችግሮቹ ሳይንሳዊ መፍትሔ በማፍለቅ የወደፊቱን መተለይም አማራጭ የሌለው ተቀዳሚ ተግባር ነው ብለዋል በመግለጫቸው።

ወቅቱ የሀገር ሰላምና ህልውናን ለማቅናት የሕዝቧን አብሮት (አንድነት) ለማስጥበቅ፤ ነባር ፖለቲካዊ ባህል በመገምገም፤ አዲስ ፖለቲካዊ ባህል ለመትከል በጋራ የምንቆምበት ወሳኝ ጊዜ ነው ሲሉም አንስተዋል።

በመሆኑም «በቅርቡ ከኢዜማ ድርጅታዊ መዋቅር የለቀቅን አመራሮች እና አባላት ፣ ከሌሎች ሀገር ወዳድ አካላት፣ ስብስብና ፣ግለሰቦች ጋር በመሆን፣ በመተባበር ለአዲስ ፖለቲካዊ ባህል ግንባታ ጠቀሜታ ባላቸው፣ ለቀጣዩ ፖለቲካዊ የትግል ጉዞ በሚያግዙ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ግምገማ፣ ውይይትና ምክክር መጀመራችንን ለማሳወቅ እንወዳለን» ብለዋል።

"ችግር ፈቺ"፣ የሃሳብ ግብዓት ያስገኛል ያሉትን ይህንን ውይይት እንዲሁም ለወቅቱ የሚመጥን፤ ተገቢውን ሰላማዊ የትግል አማራጭ ለመወሰን የሚያስችል አቅም ያጎናፅፋል የሚል እምነት እንዳላቸውም አንስተዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 13ቀን 2015 ዓ.ም
2.6K views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ