Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Fm 107.8

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofm107dot8
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.12K
የሰርጥ መግለጫ

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-06-10 23:37:36
የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ፍፃሜ

በአታቱርክ ስታዲየም

ማንቸስተር ሲቲ 1 - 0 ኢንተር ሚላን፣ ጨዋታው እንደቀጠለ ነው።
1.3K views20:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 10:38:41
2.5K views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 18:29:08 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ያገለለ ነው ተባለ፡፡

የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ያገለለ የምክክር ሂደት ውጤታማ  የመሆን እድሉ ዝቅተኛ ነው  ተባለ፡፡

የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት   ሃገራዊ የምክክር ኮምሽኑ  በሚያካሂደቸው ውይይቶች ላይ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን እያሳተፈ ያለመሆኑ እንደሚያሳስበው ገልፃል፡፡

የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያው  በብሄራዊ የምክክር ኮምሽኑ የተሰጠው ቦታ  አነስተኛ በመሆኑም  የኮምሽኑ  ሂደት እንደገና ሊጤን ይገባዋል ሲል  ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ምክክር ያደረገ ቢሆንም የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን እንደ ተቋም ከመጋበዝ ይልቅ ሌሎች ሲወያዩ የዜና ሽፋን እንዲሰጡ ብቻ የሚጋበዙ መሆኑ  ትልቅ ጉድለት ነው ብሎ እንደሚያምንም ገልፃል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሳታፊዎች ልየታን በሚያካሂድበት ወቅት የምክክር ሂደቱ ዋናኛ ባለድርሻ አካላት የሚባሉት የፖለቲካ ፖርቲዎች ምክር ቤትን፤ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤን እንዲሁም ሌሎች በርካታ የሲቪክ  ማህበራትን ከግምት አስገብቶ ተሳታፊ ሲያደርግ የጋዜጠኞች የሙያ ማህበራትንም ሆነ  የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትን የሚወክለውን ምክር ቤቱን መዘንጋቱ  የአካታችነትን  መሰረታዊ መርሆን ይቃረናል  ብሏል ምክር ቤቱ፡፡

በመሆኑም የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ያገለለ የምክክር ሂደት ውጤታማ የመሆን እድሉ አነስተኛ በመሆኑ ሂደቱ እንደገና ሊጤን ይገባዋል ሲል አሳስቧል፡፡ ፡፡
ሀገራዊ  ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ከዘጋቢነት ሚናቸው ባለፈ በሙያ ማህበራቱና በምክር ቤቱ  የተወከሉ ሙያተኞች ሀሳብ በአግባቡ እንዲንፀባረቅ እንዲደረግ  ሂደቱም የመገናኛ ብዙሃን ባለሙዎችን የሀሳብ መዋጮ ከግምት እንዲያስገባም ጠይቋል፡፡

የውል ሰው ገዝሙ
ሰኔ 02 ቀን 2015 ዓ.ም
3.2K views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 16:36:54
በሸገር ከተማ እየተደረገ የሚገኘዉ የዕምነት ተቋማት ፈረሳ በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎቸ የጋራ ምክር ቤት ጠይቋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ አዉጥቷል።

የጋራ ምክር ቤቱ ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ማድረጉን አስታዉቋል።

በተለይም በሸገር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘዉ የቤት እና የዕምነት ተቋማት ፈረሳ፣የፀጥታ አካላት በአንዋር መስኪድ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የተጠቀመዉ ሀይልን ያላገናዘበ እርምጃ፣በእስረኞች ላይ እየደረሰዉ ያለዉ እንግልት፣የዜጎች አፈና እና የሰዎች መሰወር እንዲሁም ህዝቡ ባልመረጣቸዉ አካላት የመመራት ሂደትና ሌሎችም በርካታ ችግሮች ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቷል።

ይህንን ሀገሪቱ የገባችበትን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን እልባት ይሰጥ ዘንድ መንግስት መፍትሄ እንዲሰጥ መጠየቁን ዶ/ር መብራቱ አለሙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ገልፀዋል ።

በዚህም ዙሪያ ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ አዉጥቷል።
በመግለጫዉም የዜጎች ደህንነትን ፣ የሀገር ሰላም እንዲጠበቅ፣በትግራይ ክልል የመጣዉ አንፃራዊ ሰላም በሌሎች ክልሎችም በተለይም በአማራ እና ኦሮምያ ክልል እንዲሰፍን ማድረግ፣በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለዉ የቤት እና ዕምነት ተቋማት ፈረሳ በአስቸኳይ እንዲቆም እና የፀጥታ አካላት ያልተመጣጠነ ሀይል የዜጎች ህይወት መጥፋቱ በእጅጉ እንዳሳዘነዉና አጥፊዎች ለህግ እንዲቀርቡ ባወጣዉ መግለጫ አሳዉቋል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገዢዉ ብልፅግና ፓርቲን ጨምሮ 61 አባላት አሉት።

አቤል ደጀኔ
ሰኔ 02 ቀን 2015 ዓ.ም
3.1K views13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 16:46:53
ኢትዮጵያ በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት እንደምታደንቅ አሜሪካ አሳወቀች፡፡

የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኩንን በሳውዲ ሪያድ እየተካሄደ ባለው አይ ኤስ አይ ኤስ የሽብር ቡድንን ለመዋጋት በተቋቋመው ዓለም አቀፍ ጥምረት የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ ከተገኙት የአሜሪካው አቻቸው አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በወይይታቸውም በህዳር ወር ከተደረሰው ስምምነት ጋር ተያይዞ በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የተመዘገበውን እድገት አሜሪካ እንደምታደንቅ አብራርተዋል፡፡

በትግራይ ክልል ከሰብአዊ ዕርዳታ ጋር በተያያዘ አጋጠመ የተባለውን ዝርፊያም የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ምርመራ ለማካሄድ እና ተጠያቂነትን ለማስፈን በጋራ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት በደስታ እንቀበለዋለን ብለዋል አንቶኒ ብሊንከን፡፡

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን እና አንቶኒ ብሊንከን ምዕራብ ትግራይን ጨምሮ የሰብአዊ መብት አያያዝን በተመለከተም ተወያይተዋል።

ግልጽ እና ሁሉን አቀፍ የሽግግር የፍትህ ሂደትን ማራመድ፤ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን መፍታትንም ያካተተ ውይይት ማደረጋቸውን የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ተናግረዋል።

በያይኔአበባ ሻምበል

ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም
ፎቶ---ፋይል

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
3.3K views13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 16:16:31
የጉዞ መስመሩ የተቀየረዉ የህንድ ጄት አዉሮፕላን በሩሲያ የአየር ክልል እንዲያርፍ ተገደደ፡፡

የአሜሪካ ስሪት የሆነዉ የህንድ ጄት አዉሮፕላን ባጋጠመዉ የሞተር ችግር ነው በሩሲያ የአየር ክልል እንዲያርፍ የተገደደው፡፡

ይህ ክስተት የአሜሪካን ሰንደቅ ዓላማ የያዘች አዉሮፕላን ተመሳሳይ የሞተር ችግር ካጋጠማት አንድ ቀን በኋላ የተፈጠረ በመሆኑ በሩሲያ አየር ክልል አከባቢ ዉጥረት መፈጠሩ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ባሳለፍነው ማክሰኞ የተጠናቀቀዉ አለም ዓቀፉ የኢንዱስትሪ ስብሰባ፣ ወደ ዓለም ዓቀፍ መዳረሻዎች ለሚደረጉ አብዛኞቹ ጉዞዎች በሩሲያ የአየር ክልል ማለፍን እንደ ወሳኝ መሸጋገሪያ አድርጎ ወስዷል፡፡

ይህን ተከትሎ ከዩክሬን ጋር ጦርነት ዉስጥ ባለችዉ ሩሲያ ላይ ከምዕራባዊያን የተጣለባትን ማዕቀብ ምክንያት በማድረግ፣ ሩሲያ የተወሰኑ አገራትን መለያ የያዙ አዉሮፕላኖች በአየር ክልሏ እንዳያልፉ መወሰኗን ተከትሎ፣ በዚህ የአየር ክልል ማለፍ ግድ የሆነባቸዉ የተለያዩ አገራት በዉሳኔዉ ደስተኛ አለመሆናቸዉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.8K views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 16:01:26
በትግራይ ክልል 552 ትምህርት ቤቶች አሁንም ድረስ አገልግሎት መስጠት አለመጀመራቸው ተገለፀ፡፡

በክልሉ ከሚያዚያ 23 2015 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምር መደረጉ የተገለፀ ቢሆንም አሁንም በርካታ ትምህርት ቤቶች ወደ አገልግሎት መመለስ አልቻሉም ተብሏል፡፡

የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ኪሮስ ግዕሽ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት በክልሉ ከነበረው 1774 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 552 የሚሆኑት አሁንም ድረስ አገልግሎት መስጠት አለመጀመራቸውን ነግረውናል፡፡

ሀላፊው ለዚህ እንደምክንያት ያነሱት በማዕከላዊ ዞን ትግራይ 12 ትምህርት ቤቶች፣በሰሜን ምዕራብ ትግራይ 15 ትምህርት ቤቶች በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ያሉ በመሆናቸው ትምህርት ማስጀመር እንዳልተቻለ አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ክልል ስር የነበሩ አካባቢዎች የሚገኙ የነበሩ በርካታ ትምህርት ቤቶችን ወደ አገልግሎት ማስመለስ አለመቻሉን ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ኪሮስ ከነዚህ ምክንያቶች በተጨማሪ በርካታ ተፈናቃይ ወገኖች በተለያ የትግራይ አካባቢ ያሉ ትምህርት ቤቶች በመጠለላቸው ትምህርት ቤቶቹ አገልግሎት መስጠት አለመቻላቸውን አንስተዋል፡፡

በመሆኑም በነዚህ 552 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ አለመቻሉን ለጣብያች ገልፀዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.5K views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 15:39:02 “በደመወዝ ጥያቄ ሽፋን፣ ሁከት እና ብጥብጥ አስነስታችኋል” በሚል ለእስር የተዳረጉት 40 ሰራተኞች እያንዳንዳቸዉ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተለቀቁ፡፡

በደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን ምስራቅ ባድዋቾ ወረዳ ለወራት ያልተከፈላቸውን ደመወዝ ይከፈለን በሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ታስረው የነበሩት ሰራተኞች ከእስር መፈታታቸውን ኤትዩ ኤፍ ኤም አረጋግጧል፡፡
ከ40 በላይ ቀናት በእስር መቆየታቸውን የተናገሩት እና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት ግለሰቦቹ አሁን በዋስትና ተፈተው ከቤተሰብ መቀላቀላቸውን ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡

ከሚመለከተው አካል ጋር ንግግር እያደረጉ መሆኑን የሚናገሩት ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት ያናገርናቸው ግለሰብ “በህግ ቁጥጥር ስር ስውል በተፈጸመብኝ ድብደባ ህክምና ማግኘት ባለመቻሌ በአንድ አይኔ ላይ ከፍተኛ የጤና ችግር ድርሷል” ብለዋል፡፡
ከተፈጸመባቸው የመብት ጥሰት በተጨማሪ፣ ሕክምና መከልከላቸውንም ተናግረዋል፡፡

ከእስር የተፈቱት ችግሩ ተፈቶ እንደሆነ የጠየቅናቸው ግለሰቦቹ " አይ በፍጹም፤ ዐቃቤ ሕግ በማስረጃ የተደገፈ ክስ ማቅረብ ባለመቻሉ ነፃ ናችሁ በሚል ነው እያንዳንዳችን በ50ሺህ ብር ዋስ የተፈታነው ” ብለዋል፡፡

በእስር ላይ ከነበሩት መካከል ሌላኛው ስሜ አይጠቀስ ያሉን ግለሰብ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቁይታ እንደነገሩን፤ በውድቅት ሌሊት በር ሰብረው በገቡ የጸጥታ ሀይሎች እሳቸው እና ሌሉች አምስት የቤተሰቡ አባላትን ስብእናን በሚነካ መልኩ መወሰዳቸውን ገልጸው ከባድ የተባለ ድብደባም ተፈጽሞብናል ነው ያሉት፡፡
“በደመወዝ ጥያቄ ሽፋን ሁከት እና ብጥብጥ አስነስታችኋል ፤ለመገናኛ ብዙሀን እና በማህበራዊ ሚዲያም ዞናችን ስም አጥፍታችኃል በሚልም ክስ ቀርቦብን ነበር ኋላ ግን በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተለቀናል” ብለውናል፡፡

“አሁንም ድረስ የሾኔ ሆስፒታል ደሞዝ ለሰራተኞቹ መክፈል ባለመቻሉ ስራ እንዳቆመ ተናግረው ሌሎች ወረዳዎች ላይም ችግሩ ተባብሶ ቀጠለ እንጂ መፍትሔ አልተሰጠንም” ብለውናል ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት ግለሰቦች፡፡

የሃዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም ሜጫ ስለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡን ተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ስልክ ሊያነሱልን አልቻሉም፡፡

ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም ከአንድ የውጪ የዜና ወኪል ጋር በነበራቸው ቁይታ፤ ታስረው የነበሩ ሠራተኞች የዋስትና መብታቸው ተፈቅዶ መለቀቃቸውን ገልጸው፣ “ጉዳዩ ግን ገና አልተቋጨም ” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

በያይኔአበባ ሻምበል

ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.3K viewsedited  12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 15:24:23
ሕብረት ለበጎ የበጎ አድራጎት ድርጅት በ4 ቢሊየን ብር በለገጣፎ ሪፈራል ሆስፒታል ሊገነባ ነው፡፡

ሕብረት ለበጎ የበጎ አድራጎት ድርጅት በለገጣፎ የ4 ሄክታር ወይንም የ40 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ተረክቦ በዛሬው ዕለት ሰኔ 01/2015 ዓ/ም የግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር አካሂዷል።

የሚገነባው ሪፈራል ሆስፒታል 4 ቢሊየን ብር እንደሚተይቅ ኢትዮ ኤፍ ኤም ከሕብረት ለበጎ የፕሮጀክት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ደጀኔ ሰምቷል።
የግንባታ ወጭውም ከህብረተሰቡ የሚሰበሰብ ስለመሆኑም ሰምተናል፡፡

ሆስፒታሉ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ለአካባቢው እና ከአጎራባች ክልሎች ለሚመጡ አገልግሎት ፈላጊዎች አገልግሉት ይሰጠል ሲሉ አቶ ሐብታሙ ተናግረዋል፡፡

ግንባታውን ለማጠናቀቅም 3 ዓመት ሊፈጅ እንደሚችል የፕሮጀክት ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ሕብረት ለበጎ ከሁለት ዓመት በፊት በለገጣፎ ከተማ አስተዳደር ቃል የተገባለትን 6 ሄክታር ወይንም 6ዐ ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ በሙሉ እንዳላገኘም ተናግሯል፡፡

2ሺህ ካሬ ሜትሩን ለአካባቢው ተጨማሪ የልማት ሥራዎች እንዲውል በመደረጉ የ 4 ሄክታር ወይንም የ40 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ተረክቦ በዛሬው ዕለት የግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር አካሂዷል።

በግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ላይም የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ አርቲስቶችና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡

ሪፈራል ሆስፒታሉን ለመገንባት በሚደረገው ጥረትም መላው ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተቻላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ

ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም
2.3K views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 15:11:23
በጨረታ ወቅት የሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮችን የሚከላከል የዲጅታል ሲስተም ወደ ስራ ሊገባ ነው፡፡

ኦክሽን ኢትዮጵያ አክስዮን ማህበር ዘመናዊ የጨረታ ስርዓትን ለማሳለጥ የሚያስችል እና ብልሹ አሰራርን ያስቀራል የተባለለትን የዲጂታል አሰራርን ይፋ አድርጓል።

"እኮሽን ኢትዮጵያ" የመንግስትም ሆኑ የግል ተቋማት በቀላሉ መጠቀም የሚችሉት ሲስተም እንደሆነ የአክሲዮን ማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ አንኩ ተናግረዋል።
ተጫራቾች በእጅ በሚይዟቸው ስልኮቻቸው ካሉበት ሆነው መጫረት እንዲችሉ የሚረዳ ነው ያሉም ሲሆን፣አሰልቺ የሆነ የጨረታ ሂደትን እንደሚያስቀር ገልጸዋል።

በጨረታ ሂደቱ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት እንዳይፈጠሩ የተዘረጋው ሲስተም በራሱ ይከለክላል ብለዋል።
የጨረታውን አሸናፊ በፍትሃዊነት እና በቀላሉ መለየት የሚችለው ሲስተሙ፣ የኢንተርኔት አቅማቸው ደካማ በሆኑባቸው አከባቢዎች የሚገኙ አካላትም መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

ተጫራቾች የሚከወኑ ጨረታዎችን የጨረታ አይነቶችን እና ዝርዝሮች መመልከት የሚችሉበት ሲስተሙ፣ ከባንኮች ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ለጨረታው አስፈላጊ የሆኑ ክፍያዎች በቀላሉ እንዲፈፀሙ እንዲሁም ከጨረታውም በኃላ ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል ተብሏል።

በሚቀጥለው ወር ተግባራዊ ይሆናል የተባለው ቴክኖሎጂ፣ የኢንሹራንስ ድርጅቶች፣የመንግስት ተቋማት፣የውጭ ተቋማት እና የተለያዩ የቢዝነስ ድርጅቶች ከሙስና በፀዳ መልኩ መሳተፍ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.4K views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ