Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ያገለለ ነው ተባለ፡፡ የመገናኛ | Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ያገለለ ነው ተባለ፡፡

የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ያገለለ የምክክር ሂደት ውጤታማ  የመሆን እድሉ ዝቅተኛ ነው  ተባለ፡፡

የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት   ሃገራዊ የምክክር ኮምሽኑ  በሚያካሂደቸው ውይይቶች ላይ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን እያሳተፈ ያለመሆኑ እንደሚያሳስበው ገልፃል፡፡

የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያው  በብሄራዊ የምክክር ኮምሽኑ የተሰጠው ቦታ  አነስተኛ በመሆኑም  የኮምሽኑ  ሂደት እንደገና ሊጤን ይገባዋል ሲል  ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ምክክር ያደረገ ቢሆንም የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን እንደ ተቋም ከመጋበዝ ይልቅ ሌሎች ሲወያዩ የዜና ሽፋን እንዲሰጡ ብቻ የሚጋበዙ መሆኑ  ትልቅ ጉድለት ነው ብሎ እንደሚያምንም ገልፃል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሳታፊዎች ልየታን በሚያካሂድበት ወቅት የምክክር ሂደቱ ዋናኛ ባለድርሻ አካላት የሚባሉት የፖለቲካ ፖርቲዎች ምክር ቤትን፤ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤን እንዲሁም ሌሎች በርካታ የሲቪክ  ማህበራትን ከግምት አስገብቶ ተሳታፊ ሲያደርግ የጋዜጠኞች የሙያ ማህበራትንም ሆነ  የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትን የሚወክለውን ምክር ቤቱን መዘንጋቱ  የአካታችነትን  መሰረታዊ መርሆን ይቃረናል  ብሏል ምክር ቤቱ፡፡

በመሆኑም የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ያገለለ የምክክር ሂደት ውጤታማ የመሆን እድሉ አነስተኛ በመሆኑ ሂደቱ እንደገና ሊጤን ይገባዋል ሲል አሳስቧል፡፡ ፡፡
ሀገራዊ  ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ከዘጋቢነት ሚናቸው ባለፈ በሙያ ማህበራቱና በምክር ቤቱ  የተወከሉ ሙያተኞች ሀሳብ በአግባቡ እንዲንፀባረቅ እንዲደረግ  ሂደቱም የመገናኛ ብዙሃን ባለሙዎችን የሀሳብ መዋጮ ከግምት እንዲያስገባም ጠይቋል፡፡

የውል ሰው ገዝሙ
ሰኔ 02 ቀን 2015 ዓ.ም