Get Mystery Box with random crypto!

በሸገር ከተማ እየተደረገ የሚገኘዉ የዕምነት ተቋማት ፈረሳ በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ የፖለቲካ | Ethio Fm 107.8

በሸገር ከተማ እየተደረገ የሚገኘዉ የዕምነት ተቋማት ፈረሳ በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎቸ የጋራ ምክር ቤት ጠይቋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ አዉጥቷል።

የጋራ ምክር ቤቱ ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ማድረጉን አስታዉቋል።

በተለይም በሸገር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘዉ የቤት እና የዕምነት ተቋማት ፈረሳ፣የፀጥታ አካላት በአንዋር መስኪድ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የተጠቀመዉ ሀይልን ያላገናዘበ እርምጃ፣በእስረኞች ላይ እየደረሰዉ ያለዉ እንግልት፣የዜጎች አፈና እና የሰዎች መሰወር እንዲሁም ህዝቡ ባልመረጣቸዉ አካላት የመመራት ሂደትና ሌሎችም በርካታ ችግሮች ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቷል።

ይህንን ሀገሪቱ የገባችበትን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን እልባት ይሰጥ ዘንድ መንግስት መፍትሄ እንዲሰጥ መጠየቁን ዶ/ር መብራቱ አለሙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ገልፀዋል ።

በዚህም ዙሪያ ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ አዉጥቷል።
በመግለጫዉም የዜጎች ደህንነትን ፣ የሀገር ሰላም እንዲጠበቅ፣በትግራይ ክልል የመጣዉ አንፃራዊ ሰላም በሌሎች ክልሎችም በተለይም በአማራ እና ኦሮምያ ክልል እንዲሰፍን ማድረግ፣በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለዉ የቤት እና ዕምነት ተቋማት ፈረሳ በአስቸኳይ እንዲቆም እና የፀጥታ አካላት ያልተመጣጠነ ሀይል የዜጎች ህይወት መጥፋቱ በእጅጉ እንዳሳዘነዉና አጥፊዎች ለህግ እንዲቀርቡ ባወጣዉ መግለጫ አሳዉቋል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገዢዉ ብልፅግና ፓርቲን ጨምሮ 61 አባላት አሉት።

አቤል ደጀኔ
ሰኔ 02 ቀን 2015 ዓ.ም