Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Fm 107.8

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofm107dot8
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.12K
የሰርጥ መግለጫ

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-05-12 14:32:44
ቴክኖ ሞባይል አዲስ የስፓርክ 10 ሲሪየስ ስልክ በኢትዮጵያ ይፋ አደረገ፡፡

ቴክኖ ሞባይል ስፓርክ 10 የተሰኝ አዲስ የሞባይል ስልክ ምርት በይፋ አስመርቋል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ70 በላይ ዓለምአቀፍ ገበያዎች ላይ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተቀባይነትን ያተፈራው ቴክኖ ሞባይል፣ ለሁለት ቀናት በሚቆየው ዝግጅት የስፓርክ 10፣ ስፓርክ 10ሲ እና ስፓርክ 10 ፕሮ ሞዴሎች ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል።

ስልኮቹ የተጠቃሚውን ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ዘመናዊ የፊት ለፊት ካሜራን፣ ወቅታዊ ዲዛይን እና ፈጣንና ፕሮሰሰር በመጠቀም ለተገልጋዮች መቅረቡን ገልጿል።
ስፓርክ 10 ሲሪየስ ስልክ ሞዴል ስልኮች ድንቅ ምስሎችን እንዲያነሱ ታስቦ የተሰሩ ናቸው ተብሏል።

ትራንስሚሽን ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር (ቴክኖ ሞባይል) ጎሮ አካባቢ በሚገኘው አይሲቲ ፓርክ ያስገነባው ዘመናዊ ፋብሪካ፣ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ዓይነት የስልክ ምርቶችን በመገጣጠም ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ገበያዎች ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል።

ይህንን ዘመናዊ ፋብሪካ በመጠቀም ስልኮችን ለገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬን ያስቀረ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ የወጪ ንግድ ገቢ ማሰገኝት መቻሉም ተነግሯል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር መቻሉን አስታውቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርአኤል

ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም
2.1K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 11:18:38

2.3K views08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 11:12:22 የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
2.3K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 08:45:50
አንጋፋዋ ድምጻዊት ሂሩት በቀለ አረፈች፡፡

ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን እንካችሁ ያለችው ድምጻዊት ሂሩት በቀለ፣ በአደረባት ህመም በሃገር ውስጥና በውጭ በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው እለት ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ህልፈተ-ሕይወቷ ተሰምቷል፡፡

ከ1950 መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን ያስደመጠችን ሂሩት በቀለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘማሪነት/አገልጋይነት ስራዎችን ስትስራ እንደነበር ይታወሳል፡፡
የቀድሞ ድምጻዊት ከዛም ዘማሪት ሂሩት በቀለ በተወለደች በ83 ዓመቷ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው፡፡

ሂሩት በቀለ የ7 ልጆች እናት፣የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች፡
(ታዲያስ አዲስ)
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ለቤተሰቦቿ፤ለወዳች ዘመዶቿና አድናቂዎቿ መጽናናትን ይመኛል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም
2.7K views05:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 18:21:32
ድሪብል ስፖርት በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ተመልሷል
ለእግር ኳስ ተመልካቾቹ እያደረሰ የሚገኘው ድሪብል ስፖርት ዛሬ ምሽት በዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ 4፡00 ሰዓት ላይ የጣሊያኑ ጁቬንቱስ ከ ስፔኑ ክለብ ሲቪያ እንዲሁም የጣሊያኑ ሮማ ከ ጀርመኑ ባየር ሌቨርኩዝን ጋር በተመሳሳይ ሰዓት የሚያደርትን ይህንን ተጠባቂ ጨዋታ ከ ምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት የኢትዮጵያዊያን በሆነው ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ላይ ወደ እናንተ ይደርሳል፡፡
3.1K views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 11:54:11 በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በኮሌራ በሽታ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡

በደቡብ ክልል በአማሮ ልዩ ወረዳ በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ ምክንያት የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የልዩ ወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል ።

በጽ/ቤቱ የበሽታ መከላከል እና ጤና ማጎልበት ዋና የስራ ሂደት መሪ አቶ አክሊሉ ካሌብ እንደተናገሩት ከወረዳው አጎራባች ቦታዎች በመጡ ሁለት በበሽታው በተጠቁ ግለሰቦች ምክንያት በሽታው ሊዛመት ችሏል ።

በተለይ በወረዳው በርካታ ሰዎች በሚንቀሳቀሱባቸው ይሮ፤ቂሲ ማሼ እና ቤዚ ማሼ ቀበሌዎች በሽታው በፍጥነት እየስፋፋ ነው ብለዋል።

አሁንም በአጎራባች ዞኖችና እና በልዩ ወረዳው መካከል ያለው ማህበራዊ መስተጋብ የጠነከረ መሆኑ በሽታውን ለመከላከል ፈታኝ እንደሚያደርግባቸው ገልፀዋል ።

በተጨማሪም በልዩ ወረዳው የሚስተዋለው የመድኃኒት እጥረት የወረርሽኙን አስጊነት ከባድ እንደሚያደርገው አንስተዋል ።

አሁን ላይ የወረርሽኙን የመዛመት ፍጥነት ለመለየት አስቸጋሪ እንደሆነባቸው የተናገሩት አቶ አክሊሉ ወረዳው በተቻለ አቅም የግንዛቤ ስራዎችን ለመስራት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎችን ማሰማራቱን ገልጸዋል ።

ጉዳዩንም ለደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ማሳወቃቸውን የገለፁት ባለሞያው በዛሬው እለት ከክልሉ የተላኩ የሉካን ቡድኖች ይገባሉ ብለው እንደሚጠብቁ ነግረውናል ።

እስካሁን ድረስ በተረጋገጠው መረጃ መሰረት በርካታ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ የአራት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ገልጸው ቁጥሩ ከዚህ በእጅጉ ሊበልጥ ይችላል ብለዋል ።

መሳይ ገ/መድህን
ግንቦት 03 ቀን 2015

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
1.5K viewsedited  08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 11:35:53 ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ቀን ልታከብር ነው፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረው የአለም አካባቢ ጥበቃ ቀን በተያዘው ወር ግንቦት 28 ቀን ይከበራል፡፡
ኢትጵያም ይህንኑ ቀን በተለያዩ ሁነቶች ለማክበር መዘጋጀቷን አስታውቃለች፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ቀን በየአመቱ ግንቦት 28 ቀን የሚከበር ሲሆን ዘንድሮም ለመጀመርያ ጊዜ በአፍሪካ ኮትዲቫር ይከበራል፡፡

በኢትዮጵያ የአለም የአካባቢ ጥበቃ ቀን ለ30ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን ለፕላስቲክ ብክለት መፍትሄ በሚል መሪ ቃል ይከበራል
ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የአለም የአካባቢ ጥበቃ ቀን ግንቦት 28 ቀን ለማክበር ዝግጅት እያደረገች እንደምትገኝ ተገልጾ

በአዲስ አበባ ደረጃ ከግንቦት 25 እስከ ግንቦት 27ቀን ደረስ ጦር ሃይሎች በሚገኝው የጎልፍ ክለብ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር የአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ድዳ ድሪባ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከካሪቡ ኢቨንት ሃላፊነቱ ከተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር የአካባቢ ጥበቃ ቀን እንደሚከበር ነው የተገለጸው፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረው የአለም አካባቢ ጥበቃ ቀን በተያዘው ወር ግንቦት 28 ቀን ይከበራል፡፡
ኢትጵያም ይህንኑ ቀን በተለያዩ ሁነቶች ለማክበር መዘጋጀቷን አስታውቃለች፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ቀን በየአመቱ ግንቦት 28 ቀን የሚከበር ሲሆን ዘንድሮም ለመጀመርያ ጊዜ በአፍሪካ ኮትዲቫር ይከበራል፡፡
በኢትዮጵያ የአለም የአካባቢ ጥበቃ ቀን ለ30ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን ለፕላስቲክ ብክለት መፍትሄ በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡

ሄኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 03 ቀን 2015

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
1.5K viewsedited  08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 11:29:52
የትራፊክ ህግን በመተላለፍ ከ 90 በላይ አሽከርካሪዎች ተቀጡ።

በትራፊክ መብራት ላይ ልመና እና ግብይትን ለመከላከል የወጣውን ህግ የተላለፉ ከ90 በላይ አሽከርካሪዎች ተቀጥተዋል።

በአዲስ አበባ በሚያዝያ ወር ብቻ በተመረጡ 20 አካባቢዎች ላይ በተደረገ ቁጥጥር በልመና ለተሰማሩ ዜጎች ገንዘብ ሲሰጡ እና ግብይት የፈፀሙ 92 አሽከርካሪዎች በመንገድ ትራፊክ ደንብ መሠረት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ብርሃኑ ኩማ ለኢትዩ ኤፍ ኤም ገልፀዋል።

ኤጀንሲው ቁጥጥር ካደረገባቸው ዋና ዋና የከተማዎ የትራፊክ መብራቶች መካከልም ፣ በሾላ ገበያ ፖሊስ መምርያ፣ ልኳንዳ 18 ማዞሪያ፣ ሰሜን ሆቴል፣ኢሚግሬሽን መብራት፣ እስጢፋኖስ መብራት ፣ ለቡ መብራት፣ ጀሞ መብራት፣ አየር ጤና መብራት፣ ሜክስኮ፣ ጦር ሀይሎች መብራት፣ ቄራ እና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው።

በትራፊክ መብራቶች፣ አደባባዮች እና አካባቢዎች ላይ የሚከናወኑ የልማና እና የግብይት ክልከላዎች የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከል፣ የትራፊክ ፍሰትን ለማሳለጥ እንዲሁም ህገወጥ የመብራት ላይ ንጥቅያና ሌብነትን ለመከላከል ጭምር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ኤጀንሲው ገልፆል።

እሌኒ ግዛቸው
ግንቦት 03 ቀን 2015
1.5K viewsedited  08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 12:19:03 Ethio Fm 107.8 pinned a photo
09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 12:11:40
2.6K views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ