Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Fm 107.8

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofm107dot8
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.12K
የሰርጥ መግለጫ

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-06-08 10:49:50
አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ በሁለቱ ሃገራት ግንኙነትና በቀጠናዉ ሰላም ዙሪጣ መክረዋል፡፡

የአሜሪካዉ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከሳኡዲዉ ልኡል ጋር ተገናኝተዉ መነጋገራቸዉ ተገልጿል፡፡

ዉጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በእስራኤል፣ የመን፣ ሱዳን ጉዳይ እና በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ግልጽ እና የተሳካ ንግግር ከልኡል ሞሀመድ ቢን ሳልማን ጋር ማድረጋቸዉን የአሜሪካ መንግስት ነዉ የገለጸዉ፡፡

ከተወያዩባቸዉ ጉዳዮች መካከል ሳዑዲ እና እስራኤል ያላቸዉን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ መልካም መመለስ አንዱ ቢሆንም ሳዑዲ ግን ለዚህ ቅድመ ሁኔታን አስቀምጣለች፡፡

የፍልስጤም ዘላቂ ደህንነት እና የሳዑዲ የኒኩሌር ፕሮግራም ማዘጋጀት ቅድመ ሁኔታዎቹ ሆነዉ ተቀምጠዋል፡፡
የአሜሪካዉ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጉብኝት ሳዑዲ አረቢያ የአረብ-ቻይና ኢንቨስትመንት ኮንፍረንስ ሊካሄድ ሁለት ቀናት ሲቀሩት የተደረገ መሆኑን አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.7K viewsedited  07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 10:17:32
የሽግግር ፍትህና የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ላይ ትኩረት ያደረጉ ጽሁፎች የሚቀርቡበት 3ተኛው የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ሳምንት ተጀምሯል፡፡

"የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ንቁ ተሳትፎ ዘላቂ ለሆነ ሰላም፣ ሰብዓዊ መብትና መልካም አስተዳደር" በሚል መሪ ሀሳብ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚካሄደው የሲቪል ማህበራት ድርጅት ሳምንት ኤግዚቢሽን እና ባዛር ትናንት በጊዮን ሆቴል የመክፈቻ ስነ-ስረዓቱ ተካሂዷል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከየሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በጋራ ባዘጋጀው በዚህ ሁነት፤ የመወያያ ፅሁፎች ቀርበው የፖናል ውይይቶች እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች የሰላም እና ድህረ ግጭት የሰላም ግንባታ፣ የሽግግር ፍትህ፣ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ስነ-ፆታ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ፅሁፎች እንደሚቀርቡ ተመላክቷል።

በእሌኒ ግዛቸው

ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.6K views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 14:11:58 ግብጽ ኢትዮጵያ በህዳሴው ግደቡ ዙሪያ አሳሪዉን ስምምነት እንድትቀበል ጠየቀች፡፡

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ አሳሪዉን ስምምነት እንድትቀበል አሳስበዋል፡፡

አልሲሲ ከሞሪታኒያዉ አቻቸዉ ጋር ባደረጉት ዉይይት ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ መፍትሄ ለማምጣት ልትስማማ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በዉይይታቸዉም የግብጽን የዉሃ ደህንነት ማስጠበቅ ለአረቡ ዓለም ጸጥታ እና ደህንነት ዋስትና መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ መግባባት ላይ እንዲደረስም ፕሬዝዳንቱ ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት በማሳየት የታችኛዉን ተፋሰስ አገራት ጥቅም እንዲጠበቅም አልሲሲ ጠይቀዋል፡፡

የአሁኑ የግብጽ ማሳሰቢያ ኢትዮጵያ አሳሪዉን ስምምነት እንድትፈርም እንዲሁም በግድቡ ሙሌትና አስተዳደር ላይ የጋራ መግባባት እንዲኖር መሆኑን ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

በቅርቡ ግብጽ በአረብ ሊግ ጉባዔ ላይ በግድቡ ጉዳይ ላይ የአረብ አገራት እጃቸዉን እንዲያስገቡ መጠየቋ ይታወሳል፡፡

ግብጽ የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሶስቱ አገራት አልፎ የአረብ የደህንነት ስጋት ነዉ በሚልም ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ ትከሳለች፡፡

ከሳምንት በፊት የኢትዮጵያ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በግድቡ ዙሪያ የአረብ ሊግ ያወጣዉን መግለጫ ዉድቅ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በግድቡ ዙሪያ ሲያካሂዱት የነበረዉን ድርድር ካይሮ ፣ አዲስ አበባ አሳሪዉን ስምምነት ካልፈረመች አሻፈረኝ በማለቷ ዉይይቱ መቋረጡም ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ግን በግድቡ ዙሪያ ያሉትን አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ ይገልጻል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አራተኛዉ ዙር የዉሃ ሙሌት በቀጣይ የክረምት ወቅት እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.5K viewsedited  11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 13:15:55 በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር ድርጊት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል---ኢሰመኮ
////

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች እየጨመረ የመጣውን የአስገድዶ መሰወር (Enforced Disappearance) እና ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታ ሳይታወቅ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ጉዳይ ሲከታተል መቆየቱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አሳውቋል።

በተለይም ይህ አሳሳቢ ሁኔታ በተከሰተባቸው የአዲስ አበባ ከተማ፣ የኦሮሚያ ክልል እና የአማራ ክልል ኮሚሽኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን መንግሥታዊ ኃላፊዎች በማነጋገር፣ በልዩ ልዩ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ቦታዎች በመዘዋወር እና ከቤተሰቦችና ከሌሎች የመረጃ ምንጮች መረጃዎችን ሲያሰባስብ እንደቆዬ አመልክቷል።

ኢትዮጵያ ገና ያላጸደቀችው ቢሆንም ሁሉንም ሰዎች ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ በተደረገው ዓለም አቀፍ ስምምነት (International Convention for the Protection of All Persons from Enforced Disappearance) መሠረት አስገድዶ መሰወር ማለት “በመንግሥት ወኪሎች ወይም ከመንግሥት ፈቃድ ወይም ድጋፍ በተሰጣቸው ሰዎች ወይም ቡድኖች ወይም በመንግሥት ስምምነት አንድን ሰው በማሰር፣ አፍኖ በመውሰድ፣ ወይም በሌላ በማናቸውም መንገድ ነጻነቱን በማጥፋትና፤ በቁጥጥር ስር መዋሉን በመካድ፣ በመደበቅ፣ የአለበትን ቦታ ባለማሳወቅ ወይም ደብዛውን በማጥፋት ፈጽሞ ከሕግ ጥበቃ ውጪ እንዲሆን ማድረግ’’ ነው።

በሌላ በኩል አንድን ሰው የሚገኝበት ቦታና ሁኔታ ሳይታወቅ በእስር መያዝ ማለት በተለይ በከባድ ወንጀል ተጠርጥሯል የተባለን ሰው ለወንጀል ምርመራ በሚል ምክንያት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ እንዳይገናኝ አድርጎ በእስር የማቆየትን ተግባር የሚገልጽ ፅንሰ ሐሳብ ሲሆን፤ እነዚህ ሁለቱም ድርጊቶች ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ናቸው።

በተለይ በአስከፊነቱ የሚታወቀው የአስገድዶ መሰወር ተግባርን የሚያቋቁሙት ዋነኛ አላባዎች ሦስት ዋና ጉዳዮች ናቸው ያለው ኮሚሽኑ፣በማናቸውም ዓይነት መንገድ ቢሆን አንድን ሰው ከፈቃዱ ውጪ ነጻነቱን መንፈግ/ማጥፋት፣ መንግሥት በጉዳዩ ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ፈቃድ ወይም ድጋፍ ወይም ስምምነት በመስጠት ተሳታፊ መሆን እና
አስገድዶ የተሰወረውን ሰው ያለበትን ቦታ እና ሁኔታ መካድ፣ አለመቀበል ወይም ለማሳወቅ ፈቃደኛ አለመሆን መሆናቸውን አብራርቷል፡፡

ኢሰመኮ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ከደረሱት አቤቱታዎችና ጥቆማዎች በመነሳት ሲያደርግ በነበረው ክትትል መሠረት በርካታ የአስገድዶ መሰወርን ድርጊት የሚያቋቁሙ ድርጊቶች መከሰታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

አብዛኛውን ጊዜ የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው፣ ከሥራ ቦታ ወይም ከመንገድ ላይ የሲቪልና የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታና ደኅንነት ሠራተኞች ያለ ፍርድ ቤት የመያዣ ትእዛዝ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ወዳልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ እንዲሰወሩ የተደረጉ ሲሆን፤ ከፊሎቹ ከተወሰኑ ቀናት፣ ሳምንታት ወይም ወራት መሰወር በኃላ የተገኙ መሆናቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ ሌሎች ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ በግዳጅ እንደተሰወሩ የቀጠሉ ናቸው።

ከእነዚህ ተጎጂዎች መካከል የተወሰኑት ሲያዙ በወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ መሆኑ ተነግሯቸው ወደ መደበኛ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ የተሰወሩ ሲሆን ከፊሎቹ ደግሞ ምንም ሳይነገራቸው በጸጥታ ኃይሎች ተወስደው የተሰወሩ ናቸው ብሏል፡፡

ለምሳሌ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በማስገደድ ተሰውረው ከነበሩ ሰዎች ውስጥ ከተለያየ የጊዜ መጠን መሰወር በኃላ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው የተገኙ ሲኖሩ፣ አስገድደው በተሰወሩበት ወቅት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ውስጥ ገላን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ የቀድሞው ልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ ተይዘው እንደቆዩ ለመረዳት ተችሏል። በአስገድዶ መሰወሩ ወቅት ተፈጽሟል ስለተባለ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ ወይም የማሰቃየት ተግባር ኮሚሽኑ ምርመራውን የቀጠለ ሲሆን የምርመራ ሥራው እንደተጠናቀቀ ትክክለኛውን መረጃ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “ይህ አስከፊ የሆነ የአስገድዶ መሰወር ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም መንግሥት አስፈላጊውን ጊዜያዊ እና ዘለቄታዊ እርምጃዎች ሁሉ እንዲወስድ፣ የተሰወሩ ሰዎች ሁሉ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ፣ በተሰወሩበት ጊዜ ሁሉ የተፈጸሙ ድርጊቶች ላይ የተሟላ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም ችግሩ የደረሰበትን አሳሳቢ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ሀገር አቀፍ ገለልተኛ አጣሪ የሥራ ቡድን በማዋቀር የድርጊቱ ሰለባ የሆኑ ሰዎችን ማፈላለግ እና ፍትሕን ማረጋገጥ ይገባል” በማለት አሳስበዋል።

ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.5K viewsedited  10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 13:03:03
የዋጋ ትልልፍ ኦዲት ምንነት!

የዋጋ ትልልፍ ኦዲት ማለት ምን ማለት ነው?
የዋጋ ትልልፍ ህግ የፀደቀው በታህስስ 2008 ዓ.ም ነው፡፡

የዋጋ ትልልፍ ማለት?

በገቢ ግብር ወይም በአስተዳዳር አዋጅ እንደተገለፀው፤ ሁለትና ከዛ በላይ ግንኙነት ያላቸው፤ ዓለም አቀፍ እና ሀገር በቀል እህት ኩባንያዎች እርስ በርስ የሚጠቀሙት የግብይት ዋጋ ግብር ከፋዮችን ይመለከታል፡፡

የዋጋ ትልልፍ ኦዲት ምንነት፡-

የዋጋት ትልልፍ ኦዲት ግንኙነት ያላቸው ድርጅቶች፤ የሚገበያዩበት የገበያ ዋጋ መርህን የተከተለ መሆን ይኖርበታል ሳይሆን ሲቀር ደግሞ ተገቢውን ማስተካከያ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
ግንኙነት ባላቸው ድርጅቶች መካከል የሚደረግ የግብይት ዋጋ፤ በሙሉ ጤናማ አይደለም ተብሎም አይወሰድም፡፡
ግብይቱ ሲፈፀምም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በሚገበያዩበት ልክ፤ መገበያየት ይኖርባቸዋል፡፡

ለመሆኑ ይህ የዋጋ ትልልፍ ኦዲት፤ ከታክስ ኦዲት የሚለየው ነገር ምን ይሆን?


የዋጋ ትልልፍ ኦዲት ከታክስ ኦዲት የተለየ ሁኔታ አለው የሚለይበት ምክንያትም ግንኙነት ባላቸው ድርጅቶች መካካል የሚደረግን ግብይት ኦዲት ማደረጉ የተለየ ያደርገዋል፡፡

እርስ በርስ ሲገበያዩ ከሌሎች ጋር በሚገበያዩበት በጤናማ መንገድ ተገበያይተዋል ወይ የሚለውን ኦዲት የማድረግ ስራ የሚሰራበት ነው፡፡

በቀጣይ በአስገዳጅ ሁኔታ የዋጋ ትልልፍ ህግን ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፤ በተለይም የዋጋ ትልልፍ ኢዲትን ሪፖርት በማያደርጉ ላይ፤ አስከ መቶ ሺ ብር የሚደርስ ቅጣት ይጣላል ተብሏል፡፡


በአቤል ደጀኔ
ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም
2.4K views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 10:58:19 የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
2.7K views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 21:02:43 የእምነት ቤቶች ክብር፣ ሰላምና ደህንነት ሊጠበቅ ይገባል.... የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ


የመግለጫ ሙሉ ቃል የሚከተለው ነው፦


በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ በአንዋር መስጅድ የጁምአ ሰላት ከተሰገደ በኋላ በሸገር ከተማ አስተዳደር ስለፈረሱ መስጅዶች ተቃውሞ ለማሰማት የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ በተፈጠረው ግጭትና በተወሰደው የኃይል እርምጃ በሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።


በተመሳሳይ ባለፈው ሳምንትም ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር እና በኑር (በኒን) መስጅዶች ከጁምአ ሰላት በኋላ በተፈጠረው ተቃውሞና በጸጥታ ኃይሉ የተወሰደው ያልተመጣጠነ እርምጃ ምክንያት ሁለት ሰዎች የሞቱ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞችም ከባድና ቀላል አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል።


ስለሞቱት ወገኖቻችን ጉባኤው የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለሟቾች ቤተሰቦች ወዳጅ ዘመዶች ሁሉ መጽናናትን ይመኛል፤ በተጨማሪም በዕለቱ የአካልና የሥነ ልቦና ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ ፈጣን ፈውስን እንዲያገኙ ጉባኤያችን ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንም በምዕራብ ጎጃምና በአርሲ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ሁለት አጥቢያዎች ላይ ደረሰ ስለተባለው ጉዳት እየተጣራ እንደሚገኝ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በይፋዊ የፊስ ቡክ ገጹ ያወጣው መረጃ ይጠቁማል።


መስጅዶች እና አብያተ ክርስቲያናት የአማኞች የሃይማኖታዊ፣ የመንፈሳዊ እና የሞራላዊ ዕሴቶች የሚገነባባቸው ዋነኛ ማዕከላት ከመሆናቸውም በላይ የምዕመናን ልዩ ምልክቶች እንደሆኑ የሚታወቅ ሲሆን አማኞችም ከእምነት ተቋማትና ከቤተ እምነቶቻቸው ጋር ያላቸው መንፈሳዊና ስሜታዊ ትስስርም ጠንካራ ነው።

ከዚህ አንጻር በአዲሱ በሸገር ከተማ አስተዳደር በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ መስጅዶችና የእምነት ቤቶች ሕጋዊነት ጋር በተያያዘ በመፍረሳቸው ሙስሊሙን ህብረተሰብ አስቆጥቷል።


ከዚህ አንፃር ከመነሻው ጀምሮ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም ባለፈው ሳምንት የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም ከመንግስት ጋር እየተነጋገር እንደሆነ መግለጫ በመስጠት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት ሕዝበ ሙስሊሙ ዱአ እያደረገ በትዕግስት እንዲጠባበቅ ማሳሰቡ ይታወሳል።

ይሁን እንጅ መሪ ተቋሙ ያስተላለፈው ማሳሰቢያ እንደተጠበቀ ሆኖ በዛሬው እለት ማለትም ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከጁምዓ ሰላት በኋላ ሁከትና አለመረጋጋት የተከሰተ ሲሆን የጸጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ ጉዳት መድረሱ በእጅጉ ያሳዝናል።

ስለሆነም የሕዝበ ሙስሊሙ ብቸኛ መሪ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከመንግስት አካላት ጋር የጀመረው ውይይት እስኪጠናቀቅ ሕዝበ ሙስሊሙ በትዕግስት እንዲጠብቅ፣ በተመሳሳይ መንግስትም በተለይም የጸጥታ ኃይሉ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ተግባሩን በከፍተኛ ጥንቃቄና ሆደ ሰፊነት እንዲያከናውን ጉባኤያችን በአጽንኦት እያሳስበ ሁሉም ወገን የመስጅዶችንና የቤተ እምነቶችን ክብር፣ ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ የእምነት ቤቶች የተቋቋመበትን ዓላማና ተልዕኮ ለመፈጸም የሚቻልባቸው ቅዱስ ስፍራነታቸው የማክበርና የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ
3.7K views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 12:29:48
ሕብረት ባንክ በይቆጥቡ ፣ይቀበሉ፣ይመንዝሩና ይሸለሙ መርሃግብሩ አሸናፊ ደንበኞችን ሸለመ።

ባንኩ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ከፍ ለማድረግ ለሶስተኛ ጊዜ ባካሄደው በይቆጥቡ፣በይቀበሉ፣ይመንዝሩና ይሸለሙ መርሃግብሩ የዕጣ አሸናፊ የሆኑትን ደንበኞቹን በዛሬው ዕለት ሸለሟል።

የሕብረት ባንክ ከፍተኛ ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ፅጌሬዳ ተስፋዬ ፣ ባንኩ የደንበኞችን የቁጠባ ባህል እያሳደገ ይገኛል፣ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝትም ከፍ እንዲል እያደረገ ነው ብለዋል።

በቀጣይም የባንክ ኢንዱስትሪው የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ደንበኞቹን እያበረታታ ይቀጥላል ነው ያሉት።

በባንኩ የሶስተኛ ዙር ሽልማት አሸናፊ የሆኑ ዕድለኞች ሽልማታቸውን ተረክበዋል።

ሽልማቶቹ ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል ፣ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ፣የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ ፍሪጆች፣ ቴሌቪዥን፣ ወመናዊ ስልኮችና የውሃ መሳቢያ ጄኔሬተር ናቸው።

በአባቱ መረቀ

ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም


ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
3.9K views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 07:28:29 ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ክልል ስለነበሩ ከ6ሺህ በላይ ኢንዱስትሪዎች አሁን ላይ መረጃ እንደሌለዉ የክልሉ ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ

በትግራይ ክልል የነበሩ 6ሺህ 4መቶ 39 ኢንዱስትሪዎች መካከል አሁን ላይ ሁሉም በአጠቃላይ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንደማይዉቅ የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቋል፡፡

የቢሮዉ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ገ/ጻድቅ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት፤ በ 2012 ዓ.ም በክልሉ 61 ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች፣ 8 መቶ 72 መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች እና 5ሺህ 506 አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ነበሩ፡፡

አሁን ላይ እነዚህ ኢንዱስትሪዎች በአጠቃላይ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ምንም የምናዉቀዉ ነገር የለም ብለዋል፡፡

ለዚህም አቶ ዳዊት ጥናት አለመደረጉን እንደምክንያት አንስተዋል፡፡

ቢሮዉ በጉዳዩ ላይ ጥናት ባለማካሄዱ መቀሌ ላይ ካሉ የተወሰኑ ኢንዱስትሪዎች በስተቀር፤ ሌሎቹ የት ደረጃ ላይ እንዳሉ አስካሁን ያወቅነዉ ነገር የለም ነዉ ያሉት፡፡

በአጠቃላይ ግን ሙሉ ለሙሉ ከወደሙ እና ከተዘጉ ኢንዱስትሪዎችባሻገር የተወሰነ ጉዳት ደርሶባቸዉ ወደ ስራ መመለስ የሚችሉ ኢንዱስትሪዎች መኖራቸዉን ተናግረዋል፡፡

ይሁንና ለእነዚህ ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ ተደርጎ ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ አሁን ያለዉ የመንግስት አሰራር አመቺ አይደለም ብለዋል፡፡

የፌደራሉ መንግስት ኢንዱስትሪዎቹ የሚያስፈልጋቸዉን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ቢያሳይም ድጋፎቹ ግን ለኢንዱስትሪዎቹ በተግባር የደረሱ አይደሉም ነዉ ያሉት፡፡


በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም


ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
3.6K viewsedited  04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 07:22:57
የሱዳን ተኩስ አቁም ስምምነት መጣሱ እንዳሳሰባት አሜሪካ ገለጸች።


የአሜሪካ መንግስት የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች የተኩስ አቁሙን መጣሳቸዉ እንዳሳሰበዉ በመግለፅ የሰብዓዊ ርዳታ ተደራሽነት ለማመቻቸት ያላቸዉ ቁርጠኝነት ጥርጣሬ ዉስጥ መግባቱን አስታውቋል።


የአሜሪካ መንግስት የዉጭ ጉዳይ ቢሮ እንዳስታወቀው ከሆነ " እንደ አንድ የድርድሩ አስተባባሪ እየተጣሱ ያሉት የተኩስ አቁም ስምምነቶች የሱዳንን ህዝብ ወክለዉ የወሰዱትን ግዴታ ተረክበዉ እርምጃ ለመዉሰድ ዝግጁ መሆናቸውን ጥያቄ ዉስጥ የሚከት ነዉ ሲል ወቅሷል"።

በዋና ከተማዋ ካርቱም በትላንትናዉ ዕለት ግጭቱ ተባብሷ መቀጠሉን የአይን ዕማኞች ገልጸዋል።


በተለይም በዋና ከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ካርቱም፣ባህሪ እና ኦምዱርማን ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉ ተገልፃል።

እነዚህ አካባቢዎች በናይል ወንዝ ዙሪያ የሚገኙና በአፍሪካ በርካታ የህዝብ ቁጥር ካለባቸዉ ከተሞች መካከል ናቸው።


በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
3.1K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ