Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Fm 107.8

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofm107dot8
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.12K
የሰርጥ መግለጫ

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-20 10:45:00
በዛሬው እለት 20 ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው፡፡

20 ዩኒቨርስቲዎች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት በማስመረቅ ላይ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች መካከል አዲስ አበባ፣ ወለጋ፣ ደብረብርሃን፣ አርባምንጭ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ እና ሰመራ፣ ወልቂጤ እንዲሁም ኢንጅባራ ዩኒቨርስቲዎች ይገኙበታል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ መርሐ ግብር ያስተማራቸውን 8 ሺህ 642 ተማሪዎች በማስመረቅ ላይ ነው።

ከተመራቂዎቹ መካከል 5 ሺህ 121 በመጀመሪያ ዲግሪ ፣ 3 ሺህ 221 በሁለተኛ ዲግሪ እና 300 ተማሪዎች ደግሞ በሶስተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች መሆናቸው ተገልጿል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ላለፉት 73 ዓመታት በማስተማር እና በምርምር ስራ ላይ የቆዬ አንጋፋ የትምህርት ተቋም መሆኑ ይታወቃል።

ኢንጅባራ ዩኒቨርስቲ በምረቃ ስነስርአቱ ላይ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ መስጠቱንም አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም ለተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 13ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube

https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
3.2K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-18 12:32:08
አባቶች የህይወት ልምዳቸው የሚያካፍሉበት 'አባቶች ይመርቁ' መርሃግብር እየተደረገ ይገኛል።

ኤሴቅ ዲኮር እና ኤቨንት ኦርጋናይዘር ከጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ነው መርሃል ግብሩን ያዘጋጁት።


በዚህ መርሀግብር የሃገር ሽማግሌዎች በየተሰማሩበት ዘርፍ ለሃገር ለከፈሉት እና እየከፈሉትም ላለው ዋጋ አዲሱ ትውልድ የተለዬ ነገር መስጠት ባይችልም ምስጋና የሚያቀርብበት፣አባቶችም ከህይወት ልምዳቸው ጨልፈው ተሞክሯቸውን የሚያካፍሉበትና ምርቃት የሚያቀርቡበት ነው።


የጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፍጻሚ ተስፋዬ ኦሜጋ ይህ ፕሮግራም ለኢትዮጵያ ትልቅ አንድነት የሚፈጥር ነው ብለዋል።


የአባት የህይወት ልምድ መሰረት ያስይዛል፣አባቶችና እናቶች የብዙ ሃገር በቀል እዉቀት ባለቤቶች ናቸው፣እናም ቀረብ ብለን ምክራቸውን ልንሰማ፣ተሞክሯቸውን ልንቀስም ይገባናል” ብለዋል፡፡


ኤሴቅ ዲኮር እና ኤቨንት ኦርጋናይዘር ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ደረጄ ፕሮግራሙ የሃገራችንን ባህላዊ እሴቶች ጠብቆ ለማቆየት፣ትዉልዱ ለአባቶችና እናቶች ያለበትን እዳ መክፈል ባይችል እንኳን የሚያመሰግንበትን መድረክ እንደሆነ ገልጸዋል።


እንደዚሁም በሃገራችን እየተከሰቱ ያሉ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀዉሶች አገር በቀል መፍትሄ የመስጠት ልምድን ለማስቀጠል እና ታላላቆቻችንን ለማክበር ከእነርሱ ማግኘት የሚገባንን እዉቀትና ምርቃት ለማግኘት ዓላማ ተደርጎ መዘጋጀቱን ሰምተናል፡፡


በሀገሪቱ በማህበራዊ ጉዳዮች ንቁ ተሳትፎ ያላቸው፣በሰብአዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩና በመዝናኛ ዘርፉም የተሰማሩ ሽማግሌዎች በመርሀግብሩ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም
4.2K views09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 13:52:37
ሜሰን ማውንት ማንቸስተር ዩናይትድን ተቀላቀለ።

ማንቸስተር ዩናይትድ ሜሰን ማውንትን በይፋ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።

የላንክሻየሩ ክለብ ሜሰን ማውንትን በአምስት ዓመት ኮንትራት ነው ለዩናይትድ ያስፈረመው፡፡

ለአማካዩ ዝውውር 60 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ መደረጉን ጠቅሶ ቢ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

ሜሰን ማውንት በቼልሲ ቆይታው 195 ጊዜ ተሰልፎ 33 ጎሎችን ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዎያን

ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
581 views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 15:34:57
የቱርክ-አፍሪካ የንግድ መድረክ በኢስታንቡል ይካሄዳል፡፡

 ኢትዮጵያም ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ መድረክ ላይ ተሳታፊ ትሆናለች፡፡

ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያሳትፈው 10ኛው የቱርክ-አፍሪካ የንግድ መድረክ በቱርክ ዋና ከተማ ኢስታንቡል ይደረጋል።

በቱርክ-አፍሪካ ቢዝነስ አሶሴሽን "TABA"አማካኝነት የሚደረገው ይህ የንግድ መድረክ የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራትን እንደሚያሳትፍ ተገልጿል።

ሃገራችንም በዚህ ወቅት ተሳታፊ መሆኗ ደግሞ "የኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ውጤታማነቱን ለማሳደግ እንደሚረዳ፣ በኢንድስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር እና የሚንስትሩ አማካሪ አቶ አስፋው አበበ ገልጸዋል።

እንደ ሃገር ከቱርክ ጋር የተሳካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙቶችን ለማድረግ ይህ የንግድ መድረክ አስተዋጽኦው የጎላ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

ከ10 በፊት መካሄድ የጀመረው ይህ የንግድ መድረክ፣ ዋና አላማው በአፍሪካ እና በቱርክ መካከል ያለውን የባህል መስተጋብርን ማሳደግ መሆኑም ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም በንግድ መድረኩ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ የአፍሪካ ሃገራት ለሚያመርቷቸው ምርቶች ተደራሽነት ትልቅ በር ከፋች እየሆነ ስለመምጣቱም ተወስቷል።

ግብርናን፣የፈርኒቸር ምርቶችን ጨምሮ ከአስር በላይ የንግድ ዘርፎችን አካቶ የሚሰራው "የቱርክ -አፍሪካ ቢዝነስ አሶሴሽን" 55 በመቶ የሚሆኑ የአፍሪካ ሃገራትን እያሳተፈ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው።

ኢትዮጵያ በዚህ ዓለም-አቀፍ የንግድ መድረክ የምትሳተፈው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በተለይ የግብርና ምርቶቿን ለአለም አቀፍ ገበያዎች ለማሳወቅ ትልቅ በር እንደሚከፍትላት የተገለፀ ሲሆን ከ400 በላይ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎችና ባላብቶች እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል።

በመሳይ ገ/መድህን

ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም
2.3K views12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 13:56:50 የኢትዮጵያ መንግስት የዴር ሱልጣን ገዳም ይዞታን ማስጠበቅ እንዳለበት እስራኤል አስታወቀች፡፡

በግብፅ ኮፕቲክና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መካከል አለመግባባት የሚፈጥረው የዴር ሱልጣን ገዳም ይዞታ፣ የኢትዮጵያ ሆኖ እንዲዘልቅ እንደሚፈልግም የእስራኤል መንግስት ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለሊ አድማሱ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ባደረጉት ቆይታ፤የኢትዮጵያ መንግስት እየሩሳሌም የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ያን ንብረት የሆነውን የዴር ሱልጣን ገዳም ይዞታ ማስጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡

የእስራኤል መንግስት የዴር ሱልጣን ገዳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ይዞታ ነዉ ብሎ እንደሚያምንም አምባሳደሩ ነገረዉናል፡፡
ነገር ግን ጉዳዩ የፖለቲካ ጥቅም ግጭት ያለበት በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት እንዳለበት አምባሳደሩ አስታዉቀዋል፡፡

በቅድስቲቱ ሀገር በኢየሩሳሌም ክርስቶስ የተሰቀለበት፤ የተቀበረበት፤ እንዲሁም በተነሳበት ስፍራ በጎልጎታ ተራራ ላይ ይገኛል የዴር ሱልጣን ገዳም፡፡
ከ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በገዳምነት ይጠቀሙበትና ይኖሩበት እንደነበር የሚነገርለት በሀገረ እስራኤል በኢየሩሳሌም የሚገኘው የዴር ሡልጣን ገዳም፣ በተለያየ ጊዜ የባለቤትነት ጥያቄ ይነሳበታል፡፡
በተለይ የግብፅ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን የባለቤትነት ጥያቄ ስታነሳ ቆይታለች፡፡ በተደጋጋሚም ገዳሙ ዉዝግብና ግጭቶችን ያስተናግዳል፡፡


ይዞታዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንደሆነ ቢነገርም፣ ግብጻዉያኑም የይገባኛል ጥያቄ በማንሳት ለዘመናት ዉጥረትን የሚያስተናግድ የእምነት ቦታ ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ ንግሥት ሳባ ኢየሩሳሌም በሄደችበት ጊዜ እስዋን የተከተሉ ሰዎች ያረፉበት ነበር በሚባለዉ በዚሁ በቅዱሱ ስፍራ ጎልጎታ የሚገኘዉ በዴር ሱልጣን ገዳም፣ ስያሜዉ በጥንት ዘመን በአረቦች የተሰየመና የንጉሥ ገዳም የሚል ትርጉም እንዳለዉ ስለገዳሙ የሚያዉቁ ይናገራሉ።

ለመሆኑ ግብፆች በምን አግባብ ገዳሙ የእኛ ነዉ ሊሉ ቻሉ? ስንል በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለሊ አድማሱን ጠይቀናል፡፡
አምባሳደሩ ሲመልሱ “ቀደም ባለዉ ጊዜ የኢትዮጵ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ያን አባቶች በገዳሙ ዉስጥ እንዲጠለሉ አንድ የግብጽ መነኩሴ በማስጠጋታቸዉ ግብጾቹ የእኛነዉ የሚል እሳቤ እንዳደረባቸዉ” ነግረዉናል፡፡

በዴር-ሱልጣን ገዳም የግሪክ ኦርቶዶክሶ ቤተክርስትያን፤ የሮማን ካቶሊካዉያን ቤተክርስትያን፤ የሶርያ ኦርቶዶክሶ ቤተክርስትያን፤ የአርመን ኦርቶዶክሶ ቤተክርስትያን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እና የግብጽ ኮፕት ቤተክርስትያን ይገኙበታል።

በአባቱ መረቀ

ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.4K viewsedited  10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 12:02:54
ትናንት የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች መሰረዛቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ረሜዲያል ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ትናንት ሰኔ 26/2015 ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በፈተና ሂደት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር የሚከተሉትን ውሳኔዎች ያሳለፈ መሆኑን እንገልጻለን ብሏል።

1) ሰኔ 26/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ

2)ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ

3)በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት የሚሰጥ መሆኑን አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም
2.5K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 10:43:22 በጉራጌ ዞን በታጠቁ ኃይሎች አምስት ሰዎች ተገደሉ።

በአካባቢውም ውጥረት ነግሷል ተብሏል።

በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ እሁድ ሰኔ 25/2015 ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በተሰነዘረ ጥቃት ሦስት ተማሪዎች እንዲሁም እናትና ልጅ መገደላቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በዕለቱ ተማሪዎቹ የተገደሉት ምሽት ሦስት ሰዓት ገደማ የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ለመፈተን እያነበቡ በነበረበት በመኖሪያ ቤታቸው ነው ተብሏል፡፡

እንደ አዲስ ማለዳ ዘገባ፣ ታጣቂዎቹ ሦስቱን ተማሪዎች ከገደሉ በኋላ፤ የአካባቢው ማህበረሰብ በጩኸት ሲከተላቸው በቼ ቀበሌ ውስጥ የምትኖር አንዲት እናትን ከእነልጇ ገድለው ከአካባቢው መሰወራቸውን ነው ነዋሪዎች የገለጹት።

በዚህም በዞኑ የሚገኙት መስቃንና ማርቆ ብሄረሰቦች መካከል የቆየ አለመግባባት ከመኖሩ ጋር ተያይዞ "ተማሪዎቹ በማርቆ ብሄረሰብ ተወላጆች የተገደሉ ናቸው" በሚል በኹለቱ ብሄረሰቦች መካከል ውጥረት መንገሱ ተነግሯል።

በአሁኑ ወቅት በምስራቅ መስቃን ወረዳ ሥር የሚገኙ ዘጠኝ ቀበሌዎች፤ በመስቃንና በማረቆ ብሄረሰቦች መካከል በይገባኛል ጥያቄ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ተመላክቷል።

ይህን ተከትሎም እሁድ ሰኔ 25/2015 ምሽት በተገደሉት ሦስት ተማሪዎች ምክንያት፤ በኹለቱ ብሔረሰቦች መካከል ውጥረት ነግሷል ነው የተባለው።

ተማሪዎቹ ከተገደሉበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ትናንት ሰኔ 26/2015 ከቀኑ አምስት ሰዓት ድረስም በአካባቢው ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማም ነው የተጠቀሰው።

የተፈጠረውን ችግር ለማረጋጋት ወደ ቦታው ከፍተኛ የመንግሥት የጸጥታ አካላት እየገቡ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ይሄ ዘገባ እስከትጠናቀረበት ሰዓት ድርስ በአካባቢው ያለው ውጥረ እንደቀጠለ መሆኑ ተመላክቷል።

የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ “እኛም ጉዳዩን ሰምተን ለማረጋጋት ወደ አካባቢው እየሄድን ነው፡፡” ሲሉ ገልጸው፤ ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም
2.6K viewsedited  07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 04:33:34
ስቲቨን ዤራርድ የሳኡዲ አረቢያው ክለብ አል- ኢቲፋቅ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ! (አቤል ጀቤሳ)

ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.8K views01:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 14:51:07
መንገዶችን በሚያበላሹ ተሸከርካሪዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል!

የመንገድ ህግን ተከትለው በማያሽከረክሩ የጭነት ተሸከርካሪዎች ላይ አርምጃ እየተወሰደ ነው ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመነት ኤጀንሲ በከተማዋ መንገዶችን የሚያበላሹ የጭነት ተሸከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ለጣብያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በትራፊክ ፍሰት እና ደህንነት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች ላይ ኤጀንሲው ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ጥብቅ ቁጥጥር መጀመሩን አስታውቋል፡፡

በከተማዋ እየተገነቡ ከሚገኙ የተለያዩ የግንባታ ቦታዎች ተረፈ ምርቶችን እና አፈር እየጫኑ የሚንቀሳቀሱ የጭነት ተሽከርካሪዎች መንገዶችን ከማበላሸታቸው እና ከማቆሸሻቸው ባሻገር ለእግረኞች እና ለተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ስጋት እየሆኑ ስለሚገኙ ጥብቅ ቁጥጥር መጀመሩ ተገልፃል፡፡

በትራፊ ጭነት ላይ ተገቢውን ምልክት ሳያደርግ ወይም ተሽከርካሪው ላይ የተጫነውን ጭነት በሚገባ ሳያስር ወይም ሳይሸፍን ያሽከረከረ እንዲሁም በመንገድ ላይ ያፈሰሰውን ወይም የጣለውን ፈሳሽ ወይም ጠጣር ነገሮችን ያላነሳ ወይም ያለጸዳ አሽከርካሪ ቅጣት የሚጣልበት መሆኑን በግልጽ የተቀመጠ በመሆኑ እነዚህን ደንቦች ተላልፎ የሚገኝ የጭነት ተሸከርካሪዎች ላይ በህጉ መሰረት የቅጣት ውሳኔ እየተሰጠባቸው እንደሚገኝ ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡


በአቤል ደጀኔ
ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
3.2K views11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 14:07:23 በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ ኹለት የአካባቢው ሚሊሻዎች መገደላቸው ተገለጸ።


በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን በዲማ ወረዳ ለግዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ፤ ኹለት የአካባቢው ሚሊሻዎች ሕይወት ሲያልፍ አንድ ሚሊሻ መቁሰሉን የዲማ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡


የጽ/ቤቱ ሃላፊ ኡኬሎ ኡጁሉ እንደገለጹት ከሆነ፤ በትናንትናው ዕለት ከጥዋቱ 2 :00 ላይ ለግዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በካችና ቀበሌ አካባቢ ገብተው በከፈቱት ተኩስ፤ በሰዓቱ ጸጥታ በማስከበር ላይ የነበሩ ኹለት ታጣቂዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ አንድ ሚሊሻ ቆስሎ በሕክምና ላይ ይገኛል፡፡


ኡኬሎ አያይዘውም፤ ቅዳሜ ሰኔ 24/2015 ከቀኑ 3:00 አካባቢ ከካችና ቀበሌ ወደ ናምካዶ ቀበሌ በመጓዝ ላይ የነበረው አንድ ሞተረኛ በጥይት ተመትቶ ጉዳት እንደደረሰበት ገልጸዋል።


ሃላፊው አክለውም፤ በወረዳው ላይ የተሻለ ሰላም ቢኖርም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በመንገድ ላይ ዝርፊያ የተሠማሩ ሽፍቶች በተደጋጋሚ ጥቃት እየፈፀሙ መሆኑን ገልጸው፤ የወረዳው መንግሥት ጥቃቱን ለማስቆም ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት የአቅሙን ያህል እየሠራ መሆኑን መናገራቸውን የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገልጿል፡፡


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.9K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ