Get Mystery Box with random crypto!

የቱርክ-አፍሪካ የንግድ መድረክ በኢስታንቡል ይካሄዳል፡፡  ኢትዮጵያም ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ መ | Ethio Fm 107.8

የቱርክ-አፍሪካ የንግድ መድረክ በኢስታንቡል ይካሄዳል፡፡

 ኢትዮጵያም ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ መድረክ ላይ ተሳታፊ ትሆናለች፡፡

ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያሳትፈው 10ኛው የቱርክ-አፍሪካ የንግድ መድረክ በቱርክ ዋና ከተማ ኢስታንቡል ይደረጋል።

በቱርክ-አፍሪካ ቢዝነስ አሶሴሽን "TABA"አማካኝነት የሚደረገው ይህ የንግድ መድረክ የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራትን እንደሚያሳትፍ ተገልጿል።

ሃገራችንም በዚህ ወቅት ተሳታፊ መሆኗ ደግሞ "የኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ውጤታማነቱን ለማሳደግ እንደሚረዳ፣ በኢንድስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር እና የሚንስትሩ አማካሪ አቶ አስፋው አበበ ገልጸዋል።

እንደ ሃገር ከቱርክ ጋር የተሳካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙቶችን ለማድረግ ይህ የንግድ መድረክ አስተዋጽኦው የጎላ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

ከ10 በፊት መካሄድ የጀመረው ይህ የንግድ መድረክ፣ ዋና አላማው በአፍሪካ እና በቱርክ መካከል ያለውን የባህል መስተጋብርን ማሳደግ መሆኑም ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም በንግድ መድረኩ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ የአፍሪካ ሃገራት ለሚያመርቷቸው ምርቶች ተደራሽነት ትልቅ በር ከፋች እየሆነ ስለመምጣቱም ተወስቷል።

ግብርናን፣የፈርኒቸር ምርቶችን ጨምሮ ከአስር በላይ የንግድ ዘርፎችን አካቶ የሚሰራው "የቱርክ -አፍሪካ ቢዝነስ አሶሴሽን" 55 በመቶ የሚሆኑ የአፍሪካ ሃገራትን እያሳተፈ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው።

ኢትዮጵያ በዚህ ዓለም-አቀፍ የንግድ መድረክ የምትሳተፈው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በተለይ የግብርና ምርቶቿን ለአለም አቀፍ ገበያዎች ለማሳወቅ ትልቅ በር እንደሚከፍትላት የተገለፀ ሲሆን ከ400 በላይ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎችና ባላብቶች እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል።

በመሳይ ገ/መድህን

ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም