Get Mystery Box with random crypto!

አባቶች የህይወት ልምዳቸው የሚያካፍሉበት 'አባቶች ይመርቁ' መርሃግብር እየተደረገ ይገኛል። ኤሴቅ | Ethio Fm 107.8

አባቶች የህይወት ልምዳቸው የሚያካፍሉበት 'አባቶች ይመርቁ' መርሃግብር እየተደረገ ይገኛል።

ኤሴቅ ዲኮር እና ኤቨንት ኦርጋናይዘር ከጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ነው መርሃል ግብሩን ያዘጋጁት።


በዚህ መርሀግብር የሃገር ሽማግሌዎች በየተሰማሩበት ዘርፍ ለሃገር ለከፈሉት እና እየከፈሉትም ላለው ዋጋ አዲሱ ትውልድ የተለዬ ነገር መስጠት ባይችልም ምስጋና የሚያቀርብበት፣አባቶችም ከህይወት ልምዳቸው ጨልፈው ተሞክሯቸውን የሚያካፍሉበትና ምርቃት የሚያቀርቡበት ነው።


የጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፍጻሚ ተስፋዬ ኦሜጋ ይህ ፕሮግራም ለኢትዮጵያ ትልቅ አንድነት የሚፈጥር ነው ብለዋል።


የአባት የህይወት ልምድ መሰረት ያስይዛል፣አባቶችና እናቶች የብዙ ሃገር በቀል እዉቀት ባለቤቶች ናቸው፣እናም ቀረብ ብለን ምክራቸውን ልንሰማ፣ተሞክሯቸውን ልንቀስም ይገባናል” ብለዋል፡፡


ኤሴቅ ዲኮር እና ኤቨንት ኦርጋናይዘር ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ደረጄ ፕሮግራሙ የሃገራችንን ባህላዊ እሴቶች ጠብቆ ለማቆየት፣ትዉልዱ ለአባቶችና እናቶች ያለበትን እዳ መክፈል ባይችል እንኳን የሚያመሰግንበትን መድረክ እንደሆነ ገልጸዋል።


እንደዚሁም በሃገራችን እየተከሰቱ ያሉ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀዉሶች አገር በቀል መፍትሄ የመስጠት ልምድን ለማስቀጠል እና ታላላቆቻችንን ለማክበር ከእነርሱ ማግኘት የሚገባንን እዉቀትና ምርቃት ለማግኘት ዓላማ ተደርጎ መዘጋጀቱን ሰምተናል፡፡


በሀገሪቱ በማህበራዊ ጉዳዮች ንቁ ተሳትፎ ያላቸው፣በሰብአዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩና በመዝናኛ ዘርፉም የተሰማሩ ሽማግሌዎች በመርሀግብሩ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም