Get Mystery Box with random crypto!

መንገዶችን በሚያበላሹ ተሸከርካሪዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል! የመንገድ ህግን ተከትለው በማያሽከረክ | Ethio Fm 107.8

መንገዶችን በሚያበላሹ ተሸከርካሪዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል!

የመንገድ ህግን ተከትለው በማያሽከረክሩ የጭነት ተሸከርካሪዎች ላይ አርምጃ እየተወሰደ ነው ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመነት ኤጀንሲ በከተማዋ መንገዶችን የሚያበላሹ የጭነት ተሸከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ለጣብያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በትራፊክ ፍሰት እና ደህንነት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች ላይ ኤጀንሲው ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ጥብቅ ቁጥጥር መጀመሩን አስታውቋል፡፡

በከተማዋ እየተገነቡ ከሚገኙ የተለያዩ የግንባታ ቦታዎች ተረፈ ምርቶችን እና አፈር እየጫኑ የሚንቀሳቀሱ የጭነት ተሽከርካሪዎች መንገዶችን ከማበላሸታቸው እና ከማቆሸሻቸው ባሻገር ለእግረኞች እና ለተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ስጋት እየሆኑ ስለሚገኙ ጥብቅ ቁጥጥር መጀመሩ ተገልፃል፡፡

በትራፊ ጭነት ላይ ተገቢውን ምልክት ሳያደርግ ወይም ተሽከርካሪው ላይ የተጫነውን ጭነት በሚገባ ሳያስር ወይም ሳይሸፍን ያሽከረከረ እንዲሁም በመንገድ ላይ ያፈሰሰውን ወይም የጣለውን ፈሳሽ ወይም ጠጣር ነገሮችን ያላነሳ ወይም ያለጸዳ አሽከርካሪ ቅጣት የሚጣልበት መሆኑን በግልጽ የተቀመጠ በመሆኑ እነዚህን ደንቦች ተላልፎ የሚገኝ የጭነት ተሸከርካሪዎች ላይ በህጉ መሰረት የቅጣት ውሳኔ እየተሰጠባቸው እንደሚገኝ ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡


በአቤል ደጀኔ
ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos