Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Fm 107.8

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofm107dot8
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.12K
የሰርጥ መግለጫ

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-06-02 07:15:29
የከተማዋ ህዝበ ሙስሊም የዛሬውን ጁመዐ በሰላም እንዲያሳልፍ ጥሪ ቀርቧል።


በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የመስጅድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ ማህበረሰቡ ያቀረበውን ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄዎች ማለትም የመስጅድ ፈረሳው ሙሉ በሙሉ እንዲቆም ፣የፈረሱትም መስጅዶች ወደ ቀድሞው ቦታቸው እንዲመለስ መሪ ድርጅቱ መጅሊስ ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት በተለያዩ ደረጃዎች ከሚገኙ የመንግስት አካላት ጋር እያደረገ ይገኛል ተብሏል ።

በመሆኑም መንግስትም የፍትህን መጓደል የጥያቄውን አሳሳቢነት፣በሸገር ሲቲ አስተዳደር በውይይት ላይ ያልተመሰረተን አካሄድን ከግንዛቤ በማስገባት ለተከሰተው የመብት ጥሰት ፍትህ የማስፈን ሚናውን በአፋጣኝ እንደሚወጣ ተስፋ እናደርጋለን ብሏል መግለጫው ።

በመሆኑም ኮሚቴው የደረሰበትን እስኪያሳውቀን ድረስ ውጤቱን በትእግስትና በዱአ እንዲጠባበቅ ለህዝበ ሙስሊሙ ጥሪ ቀርቧል።


የዛሬውን የጁመአ ሰላት የከተማዋ ሙስሊሞች በሁሉም መስጅዶች በሰላም ሰግዶ ወደ ቤቱ በሰላም እንዲመለስ መልእክት ተላልፏል።


በከተማዋ የሚገኙ ኢማሞች በሰላምና በትእግስት ዙሪያ የጁመአ ኹጥባ እንዲያደርጉም አሳስቧል።


ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.8K views04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 19:22:59 ትኩረት @ መታወቂያ


ያለ መታወቂያ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 2ሺህ ያህል ሰዎች መያዛቸው ተነገረ።

በአዲስ አበባ ከተማ ያለ መታወቂያ እና ያለ ምንም ማስረጃ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን የማጣራት ስራ እየተደረገ ነው ተብሏል።

የከተማዋ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ባለፋት ዘጠኝ ወራት በከተማዋ ያለ ምንም አይነት ማስረጃ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች መያዙን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታሁን አበራ በከተማዋ ያለ መታወቂያ የሚንቀሳቀሱ ዜጎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል ብለዋል።


በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
3.4K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 18:56:47
# ተጨማሪ መረጃዎች @ጸጋ


በሲዳማ ብሔራዊ ክልል የፀጥታ ግብረ ሀይል በተደረገ የተቀናጀና በቴክኖሎጂ የታገዘ ጠንካራራ ክትትል ወሪ/ት ፀጋ በላቸውን ከተጠርጣሪ ወንጀለኛ ማስመለጥ መቻሉ ተነግሯል፡፡


የፀጥታ ግብረ ሀይሉ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ የኃላመብራት ወ/ማሪያምን በቁጥጥር ስር ለማዋል ባደረገው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ከትላንት 23/09/2015ዓ.ም ጀምሮ በምስራቅ ጉጂ ዞን ቦሬ ወረዳ ጀምሮ ተጠርጣሪ ወንጀለኛውን በመከታተልና መፈናፈኛ በማሳጣት በዛሬው እለት በሻፋሞ ወረዳ ሹሮ ቀበሌ ወሪ/ት ፀጋ በላቸውን ከግለሰቡ ማስጣል ተችሏል፡፡


ግለሰቡ ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ወደጫካ የገባ ቢሆንም የፀጥታ ግብረ ሀይሉ ያልተቋረጠ ክትትል በማድረግ ተጠርጣር ወንጀለኛን በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡


ለዚህ ስምሪት መሳካት ከፍተኛ አስተወጽኦ ላበረከቱ ለብሔራዊ መረጃ ደህንነት፣ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል፣ ለሻፋሞ ወረዳ አስተዳደርና የህብረተሰብ ክፍል የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮና የፀጥታ ግብረ ሀይል ልባዊ ምስጋና ያቀርባል፡፡

ተጠርጣሪ ወንጀለኛውንም በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ ለማቅረብ በጫካው ውስጥ አሰሳ እየተካሄደ ሲሆን የሚገኙ ውጤቶችን ለመላው የሀገራችንና የክልላችን ህዝቦች የምናሳውቅ ይሆናል ብሏል ፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
3.1K views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 18:43:57
በደቡብ አፍሪካ በአማካኝ በየሰአቱ ሶስት ሰዎች የወንጀል ሰለባ ይሆናሉ፡፡


አፍሪካ ኒስው ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት በተያዘው የፈረንጆቹ 2023 በአፍሪካዊቷ ሃገር ደቡብ አፍሪካ በአማካኝ በየሰአቱ ሶስት ሰዎች በወንጀለኞች ህይወታቸው እንደሚያጡ ነው ያተተው፡፡


በዚህም ሃገሪቷ ልክ እንደ አሜሪካ የዘፈቀድ ግድያ የሚደረግባት ሃገር እየሆነች ትገኛለች ብሏል፡፡

በ2023 ግማሽ ወራት ብቻ ከ6ሺህ 200 በላይ ዜጎች በጠራራ ጸሃይ በወንጀለኞች ህይወታቸው ማለፉ ነው የተነገረው፡፡


ደቡብ አፍሪካዊያን በፈለጉት አካባቢ ለመንቃቀስም ሆነ ንብረት ይዞ ለመጓዝ ወንጀለኞቹ አያፈናፍኑም ብሏል፡፡

ድንገት ኤቲኤም ልጠቀም ቢባልም መሳርያ ደቅነው እንደሚያስፈራሩ እና ከዚህም አለፍ ሲል ግድያ እንደሚፈጽሙ ነው የተረጋገጠው፡፡


እነዚህ የግድያ ወንጀል የሚፈጽሙት አክራሪ ደቡብ አፍሪካዊ ነን የሚሉ ማፍያዎች መሆናቸውን ነው ይሕው የዜና ወኪል ያስነበበው፡፡
በተያያዘ ዜና በሃገሪቱ ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች ቁጥራቸው እየተበራከተ መምጣቱንም ተሰምቷል፡፡


በሶስት ወራት ብቻ 10ሺህ 500 ሴቶች ጾታዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው አፍሪካ ኒውስ ያወጣው መረጃ ይጠቁማል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.8K views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 18:35:44 በመዲናዋ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በበዓላት ቀን ጭምር ስራ መስራት ግዴታ ሊሆን ነዉ፡፡


በአዲስ አበባ ዉስጥ በተመረጡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በበዓላት ቀናት መስራት ግዴታ ሊሆን ነው ተብሏል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ የአገልግሎት መስጫ ጊዜን በተመለከተ አዲስ አበባ ላይ የተለየ ትኩረት ይፈልጋል የሚል እምነት አለን ብለዋል፡፡

በመዲናዋ የ 24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም መፈጠር አለበት ነዉ ያሉት፡፡

በመዲናዋ የቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓላት ቀን አገልግሎት በአሰራር ተዘርግቶ መተግበር አለበት ብለዋል፡፡

እንደ ከተማ አስተዳደር ከመደበኛዉ 8 ሰዓት ተጨማሪ መስራት ያለባቸዉ መስሪያ ቤቶች የትኞቹ ናቸዉ? የሚለዉ ላይ ጥናት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ ባለዉ የትራንስፖርት መጨናነቅ እና በተለያዩ ጉዳዮች ሰራተኛዉ ቢሮ ገብቶ የሚሰራበት ሰዓት ዉስን በመሆኑ ሰዉ ማግኘት ያለበትን ተገቢዉን አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ የ 24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት መጀመር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡


በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.5K views15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 18:22:12 በትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች ቁጥር ወደ 3ሚሊዮን ሊጠጋ እንደሚችል ተገለፀ፡፡


በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ በመቀሌ እና አቢዓዲ የሚገኙ ተፈናቃዮች 2.8 ሚሊዮን የሚጠጉ ሲሆን አሁንም በተለያዩ አከባቢዎች መፈናቀል በመኖሩ ምክንያት የተፈናቃዮች ቁጥር ወደ 3 ሚሊዮን ከፍ ሊል እንደሚችል ለኢትዮ ኤፍ የደረሱት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡


በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በርካታ ዜጎች ከትውልድ ቀያቸው ተፈናቅለው በመቀሌና አቢዓዲ እንዲሁም በተለያዩ ትምህርት ቤቶችና የተፈናቃዮች መጠለያ ጣብያዎች እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡

የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የአስተዳደር ወንጀል መከላከል ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ኡመር መሀመድ ለጣብያችን እንደገለፁት፣ ለተፈናቃይ ወገኖች እየተደረገ ያለው ድጋፍ አነስተኛ ነው፡፡

የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በፕሪቶሪያው በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሠረት ክልሉ ያለበት ሁኔታ በተመለከተ የመስክ ምልክታ ማድረጉን ገልጾ በምልከታውም በተለይም ተፈናቃዮች ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ መረዳቱን ገልጿል፡፡

አቶ ኡመር እንዳሉት በክልሉ ከ1.6 ሚሊዮን እስከ ሁለት ሚሊዮን ለሚደርሱ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ፣ቁሣዊ እንዲሁም ምግብ ነክ አቅርቦቶች በአስቸኳይ ማቅረብን ይጠይቃል፡፡

ከትግራይ በተጨማሪም በአማራ እና አፋር ክልሎችም ተፈናቃዮችን መልሶ በማቋቋም ዙሪያ ፈተና እንደገጠማቸው በተደጋጋሚ ሲገልጹ ይደመጣሉ።


በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.4K views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 17:53:44
ፀጋ በላቸው ከእገታ ነጻ መውጣቷ ተነገረ።

ወ/ሪት ጸጋ ከታገተችበት ነጻ ወጥታ በፖሊስ ወደ ሀዋሳ መግባቱዋን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

ይሁንና ተጠርጣሪው ግለሰብ እስካሁን በቁጥጥር ስር እንዳልዋለም ታውቋል።

ከሰሞኑ እጅግ መነጋገሪያ የነበረችውና ለ10 ቀናት ያህል በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ታግታ የቆየችው ፀጋ በላቸው፤ ከአጋቿ ቁጥጥር ነጻ በመውጣት ወደ ሐዋሳ ተመልሳለች ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ በአሁኑ ሰዓት የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ እና የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሸን መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ ።

በሔኖክ ወ/ ገብርኤል

ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.6K views14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:34:27
ማንቸስተር ሲቲ የ2022/2023 የውድድር ዓመት ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ፡፡
1.3K views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 16:36:53
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት እና የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ሰነድ ዛሬ ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ተቋማት በጥናት እና ስልጠና ዘርፍ በጋራ የሚሰሩ ይሆናል፡፡

የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ የሆኑት ወ/ሮ ህይወት አለማየሁ፣ በሲቪል ማህበረሰቦች ላይ ያለዉን የአመራር ክህሎት ክፍተት ለመሙላት ተቋማቸዉ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የስምምነት ሰነዱ ዋነኛ አላማዉ ጥናትና ምርምር፣የአመራር ክህሎት ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት መስጠት ላይ ያተኮረ መሆኑ ታውቋል።

ልህቀት አካዳሚው ከመንግስት ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሆነ የገለፁት ምክትል ሀላፊዋ፣ በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት ከሲቪል ማህበረሱ ጋርም ጥናትና ምርምሮችን የመስራት እና የአመራር ክህሎትን የመፈጠር ስራን በህግ የተቀመጠለት በመሆኑ እነዚህን የመሳሰሉ ስራዎች እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ሄኖክ መለሰ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከልህቀት አካዳሚው ጋር በአመራር ዘርፉ ብቁ የሆኑ የሲቪል ማህበረሰብ አመራሮችን ለመፍጠር የታሰበ መግባቢያ ሰነድ መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በዛሬው እለትም ሲቪል ማህበረሰቦች ያለባቸዉን የአመራር ሽግግር ችግር መፈተሽ የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮች ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል።

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.7K views13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 16:23:29
ኒያላ ሞተርስ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶችንና የጭነት ተሽከርካሪዎችን ሊያስመጣ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የተመረተበትን 50ኛ አመት እያከበረ የሚገኘው ኒያላ ሞተርስ፣ በቅርቡ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶችንና የጭነት ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚያስገባ አስታውቋል።

የኒያላ ሞተርስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ቦጋለ፣ ኩባንያው ባለፉት 50 ዓመታት በአውቶሞቲቭ ዘርፍ ለሀገሪቱ ትልቅ ስራን እንደሰራ አስታውሰው፣ በቀጣይም አዳዲስ ምርቶችን ለገበያ ማቅረቡን ይቀጥላል ብልዋል።

በቅርቡም በኤልክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶችንና የጭነት ተሽከርካሪዎችን ከኒሳንና ሌሎች ኩባንያዎች ጋር በመሆን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ፍቃድ ማግኘታቸውን አቶ መስፍን ገልፀዋል።

የኒያላ ሞተርስ አዲስ አበባ ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ ባለፈ በመቀሌ፣ በባህርዳር ፣ በሃዋስ፣በድሬዳዋና በጂማ ከተሞች ቅርንጫፎች እንዳሉት አስታውቋል።

በቅርቡም በገላን ከተማ ትልቅ የማስፋፊያ ስራዎችን እንደሚሰራ ይፋ አድርጓል።
ከአፍሪካ አህጉር ቀዳሚው የኒሳን ኩባንያ አጋር እንደሆነም ነው የተነገረው።

ኒያላ ሞተርስ ከ50 አመት በፊት ሶማሌ ተራ አካባቢ የዳትሰን አውቶሞቢሎችን በማቅረብ ሥራ እንደጀመረ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በአባቱ መረቀ
ግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.2K views13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ