Get Mystery Box with random crypto!

ፀጋ በላቸው ከእገታ ነጻ መውጣቷ ተነገረ። ወ/ሪት ጸጋ ከታገተችበት ነጻ ወጥታ በፖሊስ ወደ ሀዋ | Ethio Fm 107.8

ፀጋ በላቸው ከእገታ ነጻ መውጣቷ ተነገረ።

ወ/ሪት ጸጋ ከታገተችበት ነጻ ወጥታ በፖሊስ ወደ ሀዋሳ መግባቱዋን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

ይሁንና ተጠርጣሪው ግለሰብ እስካሁን በቁጥጥር ስር እንዳልዋለም ታውቋል።

ከሰሞኑ እጅግ መነጋገሪያ የነበረችውና ለ10 ቀናት ያህል በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ታግታ የቆየችው ፀጋ በላቸው፤ ከአጋቿ ቁጥጥር ነጻ በመውጣት ወደ ሐዋሳ ተመልሳለች ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ በአሁኑ ሰዓት የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ እና የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሸን መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ ።

በሔኖክ ወ/ ገብርኤል

ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos