Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች ቁጥር ወደ 3ሚሊዮን ሊጠጋ እንደሚችል ተገለፀ፡፡ በትግራይ ክ | Ethio Fm 107.8

በትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች ቁጥር ወደ 3ሚሊዮን ሊጠጋ እንደሚችል ተገለፀ፡፡


በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ በመቀሌ እና አቢዓዲ የሚገኙ ተፈናቃዮች 2.8 ሚሊዮን የሚጠጉ ሲሆን አሁንም በተለያዩ አከባቢዎች መፈናቀል በመኖሩ ምክንያት የተፈናቃዮች ቁጥር ወደ 3 ሚሊዮን ከፍ ሊል እንደሚችል ለኢትዮ ኤፍ የደረሱት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡


በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በርካታ ዜጎች ከትውልድ ቀያቸው ተፈናቅለው በመቀሌና አቢዓዲ እንዲሁም በተለያዩ ትምህርት ቤቶችና የተፈናቃዮች መጠለያ ጣብያዎች እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡

የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የአስተዳደር ወንጀል መከላከል ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ኡመር መሀመድ ለጣብያችን እንደገለፁት፣ ለተፈናቃይ ወገኖች እየተደረገ ያለው ድጋፍ አነስተኛ ነው፡፡

የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በፕሪቶሪያው በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሠረት ክልሉ ያለበት ሁኔታ በተመለከተ የመስክ ምልክታ ማድረጉን ገልጾ በምልከታውም በተለይም ተፈናቃዮች ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ መረዳቱን ገልጿል፡፡

አቶ ኡመር እንዳሉት በክልሉ ከ1.6 ሚሊዮን እስከ ሁለት ሚሊዮን ለሚደርሱ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ፣ቁሣዊ እንዲሁም ምግብ ነክ አቅርቦቶች በአስቸኳይ ማቅረብን ይጠይቃል፡፡

ከትግራይ በተጨማሪም በአማራ እና አፋር ክልሎችም ተፈናቃዮችን መልሶ በማቋቋም ዙሪያ ፈተና እንደገጠማቸው በተደጋጋሚ ሲገልጹ ይደመጣሉ።


በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos