Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በበዓላት ቀን ጭምር ስራ መስራት ግዴታ ሊሆን ነዉ፡፡ በአዲስ | Ethio Fm 107.8

በመዲናዋ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በበዓላት ቀን ጭምር ስራ መስራት ግዴታ ሊሆን ነዉ፡፡


በአዲስ አበባ ዉስጥ በተመረጡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በበዓላት ቀናት መስራት ግዴታ ሊሆን ነው ተብሏል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ የአገልግሎት መስጫ ጊዜን በተመለከተ አዲስ አበባ ላይ የተለየ ትኩረት ይፈልጋል የሚል እምነት አለን ብለዋል፡፡

በመዲናዋ የ 24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም መፈጠር አለበት ነዉ ያሉት፡፡

በመዲናዋ የቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓላት ቀን አገልግሎት በአሰራር ተዘርግቶ መተግበር አለበት ብለዋል፡፡

እንደ ከተማ አስተዳደር ከመደበኛዉ 8 ሰዓት ተጨማሪ መስራት ያለባቸዉ መስሪያ ቤቶች የትኞቹ ናቸዉ? የሚለዉ ላይ ጥናት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ ባለዉ የትራንስፖርት መጨናነቅ እና በተለያዩ ጉዳዮች ሰራተኛዉ ቢሮ ገብቶ የሚሰራበት ሰዓት ዉስን በመሆኑ ሰዉ ማግኘት ያለበትን ተገቢዉን አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ የ 24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት መጀመር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡


በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos