Get Mystery Box with random crypto!

በደቡብ አፍሪካ በአማካኝ በየሰአቱ ሶስት ሰዎች የወንጀል ሰለባ ይሆናሉ፡፡ አፍሪካ ኒስው ይዞት | Ethio Fm 107.8

በደቡብ አፍሪካ በአማካኝ በየሰአቱ ሶስት ሰዎች የወንጀል ሰለባ ይሆናሉ፡፡


አፍሪካ ኒስው ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት በተያዘው የፈረንጆቹ 2023 በአፍሪካዊቷ ሃገር ደቡብ አፍሪካ በአማካኝ በየሰአቱ ሶስት ሰዎች በወንጀለኞች ህይወታቸው እንደሚያጡ ነው ያተተው፡፡


በዚህም ሃገሪቷ ልክ እንደ አሜሪካ የዘፈቀድ ግድያ የሚደረግባት ሃገር እየሆነች ትገኛለች ብሏል፡፡

በ2023 ግማሽ ወራት ብቻ ከ6ሺህ 200 በላይ ዜጎች በጠራራ ጸሃይ በወንጀለኞች ህይወታቸው ማለፉ ነው የተነገረው፡፡


ደቡብ አፍሪካዊያን በፈለጉት አካባቢ ለመንቃቀስም ሆነ ንብረት ይዞ ለመጓዝ ወንጀለኞቹ አያፈናፍኑም ብሏል፡፡

ድንገት ኤቲኤም ልጠቀም ቢባልም መሳርያ ደቅነው እንደሚያስፈራሩ እና ከዚህም አለፍ ሲል ግድያ እንደሚፈጽሙ ነው የተረጋገጠው፡፡


እነዚህ የግድያ ወንጀል የሚፈጽሙት አክራሪ ደቡብ አፍሪካዊ ነን የሚሉ ማፍያዎች መሆናቸውን ነው ይሕው የዜና ወኪል ያስነበበው፡፡
በተያያዘ ዜና በሃገሪቱ ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች ቁጥራቸው እየተበራከተ መምጣቱንም ተሰምቷል፡፡


በሶስት ወራት ብቻ 10ሺህ 500 ሴቶች ጾታዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው አፍሪካ ኒውስ ያወጣው መረጃ ይጠቁማል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos