Get Mystery Box with random crypto!

ኒያላ ሞተርስ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶችንና የጭነት ተሽከርካሪዎችን ሊያስመጣ መሆኑን አስታወቀ | Ethio Fm 107.8

ኒያላ ሞተርስ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶችንና የጭነት ተሽከርካሪዎችን ሊያስመጣ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የተመረተበትን 50ኛ አመት እያከበረ የሚገኘው ኒያላ ሞተርስ፣ በቅርቡ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶችንና የጭነት ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚያስገባ አስታውቋል።

የኒያላ ሞተርስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ቦጋለ፣ ኩባንያው ባለፉት 50 ዓመታት በአውቶሞቲቭ ዘርፍ ለሀገሪቱ ትልቅ ስራን እንደሰራ አስታውሰው፣ በቀጣይም አዳዲስ ምርቶችን ለገበያ ማቅረቡን ይቀጥላል ብልዋል።

በቅርቡም በኤልክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶችንና የጭነት ተሽከርካሪዎችን ከኒሳንና ሌሎች ኩባንያዎች ጋር በመሆን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ፍቃድ ማግኘታቸውን አቶ መስፍን ገልፀዋል።

የኒያላ ሞተርስ አዲስ አበባ ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ ባለፈ በመቀሌ፣ በባህርዳር ፣ በሃዋስ፣በድሬዳዋና በጂማ ከተሞች ቅርንጫፎች እንዳሉት አስታውቋል።

በቅርቡም በገላን ከተማ ትልቅ የማስፋፊያ ስራዎችን እንደሚሰራ ይፋ አድርጓል።
ከአፍሪካ አህጉር ቀዳሚው የኒሳን ኩባንያ አጋር እንደሆነም ነው የተነገረው።

ኒያላ ሞተርስ ከ50 አመት በፊት ሶማሌ ተራ አካባቢ የዳትሰን አውቶሞቢሎችን በማቅረብ ሥራ እንደጀመረ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በአባቱ መረቀ
ግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos