Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት እና የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በጋራ ለመስ | Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት እና የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ሰነድ ዛሬ ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ተቋማት በጥናት እና ስልጠና ዘርፍ በጋራ የሚሰሩ ይሆናል፡፡

የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ የሆኑት ወ/ሮ ህይወት አለማየሁ፣ በሲቪል ማህበረሰቦች ላይ ያለዉን የአመራር ክህሎት ክፍተት ለመሙላት ተቋማቸዉ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የስምምነት ሰነዱ ዋነኛ አላማዉ ጥናትና ምርምር፣የአመራር ክህሎት ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት መስጠት ላይ ያተኮረ መሆኑ ታውቋል።

ልህቀት አካዳሚው ከመንግስት ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሆነ የገለፁት ምክትል ሀላፊዋ፣ በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት ከሲቪል ማህበረሱ ጋርም ጥናትና ምርምሮችን የመስራት እና የአመራር ክህሎትን የመፈጠር ስራን በህግ የተቀመጠለት በመሆኑ እነዚህን የመሳሰሉ ስራዎች እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ሄኖክ መለሰ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከልህቀት አካዳሚው ጋር በአመራር ዘርፉ ብቁ የሆኑ የሲቪል ማህበረሰብ አመራሮችን ለመፍጠር የታሰበ መግባቢያ ሰነድ መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በዛሬው እለትም ሲቪል ማህበረሰቦች ያለባቸዉን የአመራር ሽግግር ችግር መፈተሽ የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮች ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል።

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos