Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Fm 107.8

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofm107dot8
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.12K
የሰርጥ መግለጫ

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-07-03 09:19:21
የመቀሌው አይደር ሆስፒታል ሰራተኞቹ በውዝፍ የቤት ኪራይ መቸገራቸውን አስታወቀ፡፡


በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ያገለግሉ የነበሩ የጤና ባለሙያዎች ለበርካታ ወራት ደሞዝ ስላልተከፈላቸው አሁን ላይ ውዝፍ የቤት ኪራይ ዕዳቸውን መክፈል አልቻሉም ተብሏል።

ሆስፒታሉ ታህሳስ 2015 የ ደሞዝ ክፍያ እስኪጀመር ድረስ ሰራተኞቹ ያለ ደሞዝ በመቆየታቸው ለተደራራቢ ችግር እንደተጋለጡ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

የጤና ባለሙያዎቹ መኖሪያ ቤታቸው ኪራይ በመወዘፉ ምክንያት ለችግር እንደተጋለጡ በተደጋጋሚ ቅሬታ ማቅረባቸውን ኢቲዮ ኤፍ ኤም ከአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አብረሃ ገብረመድን ሰምቷል።

ሆስፒታሉ የሰራተኞቹን ችግር ለመፍታት ለፌደራል መንግስቱ ጥያቄያ ቢያቀርብም መፍትሄ እንዳልተሰጠው ዶ/ር አብረሃ ተናግረዋል ።

የሰሜኑ ጦርነት ከተነሳበት አንስቶ ሆስፒታሉ አንድ ቀን ስራ አቁሞ እንደማያውቅ ያነሱት ዶክተር አብረሃ "የጤና ባለሙያዎቹ ያገለገሉበትን መጠየቅ መብታቸው በመሆኑ የሚመለከተው ትኩረት ሰቶት መመለስ ይገባዋል" ነው ያሉት።
የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎቹ በከፍተኛ ውዝፍ የቤት ኪራይ ችግር ውስጥ መሆናቸውንም አንስተዋል።

ሆስፒታሉ አጠቃላይ የህክምና ኮሌጁን ጨምሮ 3 ሺህ 5 መቶ የሚጠጉ ሰራተኞች እንዳሉት ሰምተናል።
በአመት እስከ 3 መቶ ሺህ ለሚጠጉ ተመላላሽ ታካሚዎች እና 16 ሺህ ለሚጠጉ ተኝቶ ህክምና ተከታታዮች አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየም ዶ/ር አብረሃ ለኢቲዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በረድኤት ገበየሁ

ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም
3.0K views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 09:13:45
በ156 አመራሮች ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተባለ፡፡

ከ156 በላይ አመራሮች፣የስራ ቡድኖችና ባለሙያዎች፣ ከፎርጂድ መታወቂያ፣የልደት እና ያላገባ ሰርተፍኬት ጋር በተያያዘ፣ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃዎች እንደተወሰደባቸዉ ከአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አመራሮቹ በተለያዩ እርከን ላይ የወረዳ፣የክፍለ ከተማ እና ማዕከል ላይ ሲሰሩ የነበሩ አካላት መሆናቸዉም ተነግሯል፡፡
ለህገወጥ የሰወች ዝዉዉር ዋነኛ ከሆኑት መከካል ፎርጂድ ዶክመንቶቸ በመሆናቸዉ እነዚህን በጋራ መከላከል ይገባል ተብሏል።

በአቤል ደጀኔ

ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.7K views06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 09:10:39
ባለሥልጣናት በስማቸው የተመዘገበ የግል ድርጅትና የአክሲዮን ድርሻ እንዲያቋርጡ ወይም እንዲያስተላልፉ ሊገደዱ ነው፡፡


የመንግሥት ባለሥልጣናት በግል ጥቅማቸውና በኃላፊነታቸው መካከል ለጥቅም ግጭት የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን መከላከልና ማስወገድ እንዲችሉ፣ በስማቸውና በቅርብ ቤተሰብ ባለቤትነት የተመዘገቡ የንግድ ኩባንያዎችን ወይም የአክሲዮን ድርሻዎችን፣ እንዲያቋርጡ አልያም እንዲያስተላፉ ሊገደዱ ነው፡፡

ይህንን ግዴታ በመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ለመጣል ያቀደው፣ በፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ መሆኑን የሪፖርተር ዘገባ ያመለክታል፡፡
ረቂቅ ደንቡ፣ ‹‹ማንኛውም የመንግሥት ባለሥልጣን በረቂቅ ደንቡ የተጠቀሱ ለጥቅም ግጭት የሚያጋልጡ ሁኔታዎችና መንስዔዎች መኖራቸውን ሲረዳ፣ የጥቅም ግጭቱን ማስወገድ አለበት›› የሚል ድንጋጌ ይዟል፡፡

በዚህም መሠረት ማንኛውም የመንግሥት ባለሥልጣን የጥቅም ግጭት የሚፈጥሩ፣ ወይም ግጭት ሊፈጥሩ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ ድርጊቶችን፣ አስቀድሞ ማወቅና ግጭቱን የማስወገድ ግዴታ ይኖርበታል፡፡

የጥቅም ግጭቱን ለማስወገድ ይገባቸዋል ተብለው ከተዘረዘሩት ተግባራት መካከልም፣ ‹‹ማንኛውም ባለሥልጣን ለጥቅም ግጭቱ መነሻ የሆነውን የግል ኢንተርፕራይዝ፣ ካምፓኒ ወይም የግል ድርጅት ድርሻውን ማስተላለፍ አልያም ማቋረጥ አለበት›› የሚለው ድንጋጌ ይገኝበታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.3K views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 09:05:18
ቻይና የኢትዮጵያ የባህል አልባሳት እንዲጠፉ ምክንያት እየሆነች ነው---- የፈትል እመቤት!


የኢትዮጵያዊን መገለጫ የሆኑት የባህል አልባሳት በቻይና የባህል ወረራ ተፈጽሞባቸዋል በዚህም ምክንያት ዘርፉ አደጋ ተደቅኖበታል ተብሏል።

የሃገራችንን ባህላዊ ጥለት መስለው በማሽን የሚታተሙት ጨርቆች ግማሾቹ ከቻይና ተመርተው እንደሚመጡ፤ ኢትዮጵያ ውስጥም የሚመረቱ እንዳሉ የፈትል እመቤት የተሰኘው ድርጅት አስታውቋል።

የኢትዮጵያን ቱባ የባህል አልባሳት ከወረራ ለመከላከል በማሰብ የፈትል እመቤት ከዮድ አብስኒያ የባህል ድርጅት ጋር ስምምነት አድርገዋል።

የፈትል እመቤት ድርጅት መስራች ወ/ሮ ጸዱ ተስፋዬ በሽመና ባለሙያዎች ጥበብ አምረው የሚሰሩት ባሕላዊ የኢትዮጽያ አልባሰት በቻይናዊያን ታትመው ከሚመጡት ጋር ተወዳድሮ ገበያ ውስጥ መዝለቅ ከባድ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።

የቻይናዎቹ አቡጀዲ ጨርቅ ላይ እነሱ ያተሙት ጥለት መሰል ጨርቅ ይለጠፍበታል።
ለመሥራት በጣም ቀላል ነው። ለዚያ ነው በርካሽ ዋጋ የሚሸጠው ብለዋል።
በሸማኔ የሚሠሩ ባህላዊ ልብሶች ብዙ ውጣ ውረድ አልፈው ነው እዚህ የሚደርሱት።


ከጥጥ ማምረት ጀምሮ፤ መፍተል እንዲሁም ከሳባ ወይም ከመነን ጨርቅ ጋር አስማምቶ መሸመን ትልቅ ጥበብ ነው፤ አድካሚም ነው እናም የሚመለከተው አካል ባህላችንን ማስጠበቅ አለበት ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ቻይና ውስጥ ተሠርተው የሚመጡ ጨርቆች ገበያውን መቀላቀል ከጀመሩ በኋላ አምራቾች እና ነጋዴዎች ባዶ እጃቸው መቅረታቸው ተነግሯል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም
2.1K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 08:59:05
በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚሰሩ ልማቶች ከወዲሁ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ ነው ተባለ፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ከወዲሁ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በመገባደድ ላይ በሚገኘው የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ጥናት ማድረግ ተጀምሯል።

ግድቡ ሲጠናቀቅ ኃይል ከመስጠቱ ባለፈ የቱሪስት መዳረሻ ስለሚሆን፣ ባለሃብቶችን በልማት ስራ ላይ ለማሰማራት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስተባባሪነት ማስተር ፕለን እየዘጋጀለት መሆኑን ነግረውናል።

የህዳሴ ግድብ ውሃው በተኛበት ቦታ ላይ ደሴቶች መኖራቸው ይታወቃል፤ እነዚህም ለቱሪስት መስህብነት እንደሚሆኑ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ለባህር ትራንስፖርት ምቹ ስለሚሆን የቱሪዝም ዘረፉን ያነቃቃል ነው የተባለው።

ሌላው በአካባቢው ከፍተኛ የአሳ ርባታ ለማከናወን የሚያስችል ሁኔታ በመኖሩ፣ ግድቡ እንደተጠናቀቀ በእነዚህ ዘርፎች ላይ የሚሰሩ ስራዎች በጥናት ላይ የተመሠረቱ ለማደሰረግ ጥናቱ ተጀምሯል ነው ያሉት ሚኒስትሩ።

ግድቡን ከዳር ለማድረስ አሁንም ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
አራተኛውን የግድቡን የውሃ ሙሌት ለማከናወን ዝግጅት መጀመሩንም ሰምተናል።

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.4K views05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 11:10:06
በካቡል ሰርግ ያለሙዚቃ እንዲደረግ ታሊባን ወሰነ፡፡

በካቡል ምንም አይነት የሰርግ ዝግጅት ሲደረግ ሙዚቃ መክፈት መከልከሉን የታሊባን ባለሰልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የሰርግ ዝግጅቶችን የሚያካሂዱ ሆቴሎችም ይህንን ህግ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸዋል፡፡

ሰርግ ወይንስ ቀብር ሲል አልጀዚራ እንዳስነበበውዘ ታሊባን በአፍጋኒስታኗ ካቡል ምንም አይነት ሙዚቃ በሰርግ ድግሶች ላይ አይኖርም ብሏል፡፡

በፈረንጆቹ 2022 ታሊባን በሰርጎች እና ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ሙዚቃ እንዳይከፈት ምክረ ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን፣ ግዴታ ያደረገው በዚህ ሳምንት ነው፡፡

ታሊባን ለዜጎቹ የማይመቹ ህጎችን በማውጣት አፋኝ ስርዓትን ይከተላል ሲሉ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ቡድኑን ይተቻሉ፡፡

በቅርቡ በሴቶች የሚተዳደርን ሬዲዮ ጣቢያ እንዲቋረጥ ያደረገው ታሊባን፣ ጣቢያው ወቅቱን ያልጠበቀ ሙዚቃ ሲያስተላልፍ እንደነበር በምክንያትነት ጠቅሷል፡፡

ታሊባን በድግሶች ላይ ሙዚቃ እንዳይከፈት የከለከለው ከእስልምና አስተምሮ ጋር አይሄድም በሚል መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል፡፡


በየውልሰው ገዝሙ

ሰኔ 06 ቀን 2015 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
733 views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 10:20:04
ትራምፕ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።

የትራምኘ የፍርድ ሂደት የሚካሄድበት በሚያሚ የሚገኘው ፍርድ ቤት አካባቢም ጥንቃቄ የተሞላበት መረጋጋት ሰፍኗል።

በሚያሚ በሚገኘው ፍርድ ቤት አቅራቢያ የትራምኘን የፍርድ ሂደት ለመከታተልም በርካታ ሰዎች፤ጋዜጠኞች እና የህግ አካላት ተገኝተዋል።

በአካባቢው ከሚያንዣብቡ ሂሊኮፕተሮች ውጪ ያለው ሁኔታ እጅግ ፀጥታ የሰፈነበት መሆኑ ተነግሯል።

በተጨማሪም የፖሊስ መኪኖች በህንፃው ዙሪያ ባሉ ጎዳናዎች ተሰልፈዋል።

እ.ኤ.አ. በ 2024 እንደገና ለኋይት ሀውስ ለመወዳደር ጥረት በማድረግ ላይ ያሉት ትራምፕ፣ በ2021 ከፕሬዚዳንትነታቸው ከለቀቁ በኋላ ሚስጥራዊ ሰነዶችን አላግባብ በመያዝ በ37 መዝገቦች ክስ የተመሰረተባቸው የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነዋል።

የቀረበባቸው ክስ ውድቅ ያደረጉት የቀደሞ የአሜሪካው ፕሬዝደንት የፍርድ ሂደታቸውን ለመከታተል በሚያሚ ተገኝተዋል።

የሚያሚ ከንቲባ ፤ ከተማዋ ለትራምፕ የፍርድ ቤት ውሎ በዝግጅት ላይ ነች ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ይህንንም ሁኔታ ለመጠባበቅ ፖሊስ እንደተሰማራ ከንቲባው ገልጸዋል፡፡(አልጀዚራ እና ቢቢሲ)

በየውልሰው ገዝሙ

ሰኔ 06 ቀን 2015 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
971 viewsedited  07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 10:07:26
ህጻናትን በተመለከተ በማህበራዊ ድረ-ገጽ አማካኝነት የሚደርሱ የተለያዩ ወንጀሎችን መቆጣጠር ከባድ እንደሆነበት የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ገለጸ፡፡

በማህበራዊ ድረ-ገጽ እና በተያያዥ የዲጂታል መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ህጻናት ላይ የሚደርሰዉን ወንጀል ለመቆጣጠርም፣ለማስፈጸምም ሆነ ለመቅጣት እጅግ አስቸግሮናል ሲሉ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሃላፊ ዳኛ ተክለሃይማኖት ዳኜ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

በህጻናት ላይ እየደረሰ የሚገኘዉ ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ እና መልኩን እየቀየረ መምጣቱን የሚገልጹት ዳኛ ተ/ሃይማኖት፣ በተለይ ለማግኘትም አስቸጋሪ የሆነዉ በማህበራዊ ድረ-ገጽ የሚደረገዉ ወንጀል መሆኑን አንስተዋል፡፡

የተጠቃሚዉ ትክክለኛ ማንነት አለመታወቅ እንዲሁም ደግሞ ትክክለኛ ማንነት ቢታወቅም እንኳን እያንዳንዱን ካለበት ፈልጎ ለፍርድ ማቅረብ ላይ ክፍተቶች አሉ ነው ያሉት።

በወንጀል ህጉ ከ7 መቶ በላይ የወንጀል አይነቶች አሉ ያሉት ዳኛው፣ ወደ ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ ከሚመጡ ክሶች መካከል አስገድዶ መድፈር ዋነኛው መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በማህበራዊ ድረ-ገፆች አማካኝነት በህፃናት ላይ የሚደርሱ ወንጀሎችም በዛው ልክ አደገኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 06 ቀን 2015 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
999 views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 13:55:55
የቀድሞዉ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር አሜሪካ እንድታሰር ዶልታብኛለች አሉ፡፡

የቀድሞዉ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህን ከሩሲያ ጋር በነበረኝ ግንኙነት ምክንያት አሜሪካ እንዳሳሰረቻቸው ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈዉ ወር በሙስና ጉዳይ ተጠርጥረዉ ለእስር ተዳርገው ነበር፡፡ ከእስራት ባሻገር ከስልጣን ለመዉረዳቸዉም አሜሪካ ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖ ተጠቅማለች ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከኒዉስ ዊክ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ በጥር 2022 ሩሲያ ዩክሬን ላይ ጦርነት ባወጀችበት በዛኑ ዕለት ሞስኮ ገብተዉ እንደነበር ያነሱት ኢምራን ካህን፣ በሰዓቱ የሄዱበትን የንግድ ስምምነት ላለማጣት ሲሉ የሩሲያን ተግባር መኮነን እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን አሜሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኩል የሩሲያን ተግባር እንድናወግዝ የጠየቀችን ቢሆንም፣ ከሩሲያ ጋር በገባነዉ የንግድ ስምምነት መሰረት በዝቅተኛ ዋጋ ነዳጅ እና ስንዴ ወደ አገራችን ለማስገባት በመስማማታችን ያንን ማድረግ አልቻልንም ነበር ነዉ ያሉት፡፡

“አሜሪካ እንዳለችዉ ሩሲያን ብናወግዝ በዜጎቻችን ላይ ሊኖረዉ የሚችለዉን ተጽዕኖ በማሰብ ያንን ማድረግ አልቻልንም፣በዚህም አሜሪካ በሴራ ከስልጣን እንድወርድ እና እንድታሰር አድርጋለች” ሲሉ መናገራቸዉን አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 05 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.7K views10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 13:38:50 በግሉ የጤና ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች ለሕብረተሰቡ በፋይናንስ ተደራሽ እንዲሆኑ የአሠራር፣ የፖሊሲ እና የሕግ ማሻሻያ ያስፈልጋል….ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የግሉ የጤና ዘርፍ ከሕብረተሰቡ የመክፈል ዐቅም ጋር የተመጣጠነ እና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት አቅርቦት ላይ ያተኮረ ባለ 39 ገጽ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ¬¬¬ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

የጤና መብት ተገኝነት፣ ተደራሽነት፣ ተቀባይነት እና ጥራት ላይ ያተኮሩ አራት ዋና ዋና ይዘቶች ያሉት ሲሆን ክትትሉ በተደራሽነት (accessibility) ሥር ከተጠቃለሉት ንዑስ ይዘቶች መካከል በገንዘብ ተደራሽነት ላይ ትኩረት በማድረግ መከናወኑ በሪፖርቱ ተብራርቷል።

ሪፖርቱን ለማዘጋጀት በአጠቃላይ ከ218 የባለድርሻ አካላት (80 የግል የጤና ተቋማት ኀላፊዎች፣ 8 መንግሥታዊ ያልሆኑ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ተጠሪዎች፣ 20 የመንግሥት ተቋማት ኀላፊዎች፣ 80 የግል የጤና ተቋማት ተጠቃሚዎች/ተገልጋዮች እና 30 የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች) ከሃዋሳ፣ ከባሕር ዳር፣ ከአዲስ አበባ እና ከጅማ ከተሞች መረጃዎች ተሰብስበዋል።

የግሉ የጤና ዘርፍ አገልግሎት ከመንግሥት የጤና ዘርፍ አገልግሎት አንጻር ሲታይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሕብረተሰቡ የመክፈል ዐቅም በላይ እየሆነ መምጣቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ለዚህም ዋነኛ ምክንያቶች የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦት እጥረት እና ዋጋ መናር፣ የግዴታ ግዥ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት እና ቁጥጥር አናሳ መሆን፣ ከሙያ ሥነ ምግባር ውጪ የሆኑ ተግባራት እና በመንግሥት ተቋማት የተሟላ እና አመርቂ አገልግሎት አለመኖር መሆናቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

ኢሰመኮ የጤና መብት በተሻለ ሁኔታ እንዲተገበር እና ቀደም ሲል የተዘረዘሩትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ይረዳሉ በማለት የለያቸውን የአሠራር፣ የፖሊሲ እና የሕግ ማሻሻያ ምክረ ሐሳቦችን በሪፖርቱ አቅርቧል።

ከእነዚህምመካከል በሕዝብ የጤና ተቋማት ላይ የአገልግሎት እና የአቅርቦት ማሻሻያ እና ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ሕብረተሰቡ አማራጭ እንዲያገኝ ማድረግ፣ መሠረታዊ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የጤና መድኅን አገልግሎት ማስፋፋት እና የግል የጤና ተቋማትም የሚሳተፉበትን አሠራር መዘርጋት፣ የመንግሥት እና የግል የጤና ተቋማት ሽርክናዎችን (public-private partnerships) ማጠናከር የሚሉት በምክረ ሐሳብነት በሪፖርቱ ተካተዋል።


የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአብዛኛው በመንግሥት ሲቀርብ በነበረው የጤና አገልግሎት ላይ የግሉ ዘርፍ በሰፊው መሰማራቱ ሊበረታታ እንደሚገባው ገልጸው፣ ተቋማቱ ካላቸው የፋይናንስ ተደራሽነት አንጻር ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ አስረድተዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም የግል የጤና ተቋማት ለሕብረተሰቡ በገንዘብ ተደራሽ እንዲሆኑ ለማስቻል እና የጤና መብትን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም የባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ግዴታ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 05 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.4K viewsedited  10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ