Get Mystery Box with random crypto!

የመቀሌው አይደር ሆስፒታል ሰራተኞቹ በውዝፍ የቤት ኪራይ መቸገራቸውን አስታወቀ፡፡ በሰሜኑ ጦር | Ethio Fm 107.8

የመቀሌው አይደር ሆስፒታል ሰራተኞቹ በውዝፍ የቤት ኪራይ መቸገራቸውን አስታወቀ፡፡


በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ያገለግሉ የነበሩ የጤና ባለሙያዎች ለበርካታ ወራት ደሞዝ ስላልተከፈላቸው አሁን ላይ ውዝፍ የቤት ኪራይ ዕዳቸውን መክፈል አልቻሉም ተብሏል።

ሆስፒታሉ ታህሳስ 2015 የ ደሞዝ ክፍያ እስኪጀመር ድረስ ሰራተኞቹ ያለ ደሞዝ በመቆየታቸው ለተደራራቢ ችግር እንደተጋለጡ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

የጤና ባለሙያዎቹ መኖሪያ ቤታቸው ኪራይ በመወዘፉ ምክንያት ለችግር እንደተጋለጡ በተደጋጋሚ ቅሬታ ማቅረባቸውን ኢቲዮ ኤፍ ኤም ከአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አብረሃ ገብረመድን ሰምቷል።

ሆስፒታሉ የሰራተኞቹን ችግር ለመፍታት ለፌደራል መንግስቱ ጥያቄያ ቢያቀርብም መፍትሄ እንዳልተሰጠው ዶ/ር አብረሃ ተናግረዋል ።

የሰሜኑ ጦርነት ከተነሳበት አንስቶ ሆስፒታሉ አንድ ቀን ስራ አቁሞ እንደማያውቅ ያነሱት ዶክተር አብረሃ "የጤና ባለሙያዎቹ ያገለገሉበትን መጠየቅ መብታቸው በመሆኑ የሚመለከተው ትኩረት ሰቶት መመለስ ይገባዋል" ነው ያሉት።
የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎቹ በከፍተኛ ውዝፍ የቤት ኪራይ ችግር ውስጥ መሆናቸውንም አንስተዋል።

ሆስፒታሉ አጠቃላይ የህክምና ኮሌጁን ጨምሮ 3 ሺህ 5 መቶ የሚጠጉ ሰራተኞች እንዳሉት ሰምተናል።
በአመት እስከ 3 መቶ ሺህ ለሚጠጉ ተመላላሽ ታካሚዎች እና 16 ሺህ ለሚጠጉ ተኝቶ ህክምና ተከታታዮች አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየም ዶ/ር አብረሃ ለኢቲዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በረድኤት ገበየሁ

ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም