Get Mystery Box with random crypto!

ህጻናትን በተመለከተ በማህበራዊ ድረ-ገጽ አማካኝነት የሚደርሱ የተለያዩ ወንጀሎችን መቆጣጠር ከባድ | Ethio Fm 107.8

ህጻናትን በተመለከተ በማህበራዊ ድረ-ገጽ አማካኝነት የሚደርሱ የተለያዩ ወንጀሎችን መቆጣጠር ከባድ እንደሆነበት የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ገለጸ፡፡

በማህበራዊ ድረ-ገጽ እና በተያያዥ የዲጂታል መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ህጻናት ላይ የሚደርሰዉን ወንጀል ለመቆጣጠርም፣ለማስፈጸምም ሆነ ለመቅጣት እጅግ አስቸግሮናል ሲሉ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሃላፊ ዳኛ ተክለሃይማኖት ዳኜ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

በህጻናት ላይ እየደረሰ የሚገኘዉ ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ እና መልኩን እየቀየረ መምጣቱን የሚገልጹት ዳኛ ተ/ሃይማኖት፣ በተለይ ለማግኘትም አስቸጋሪ የሆነዉ በማህበራዊ ድረ-ገጽ የሚደረገዉ ወንጀል መሆኑን አንስተዋል፡፡

የተጠቃሚዉ ትክክለኛ ማንነት አለመታወቅ እንዲሁም ደግሞ ትክክለኛ ማንነት ቢታወቅም እንኳን እያንዳንዱን ካለበት ፈልጎ ለፍርድ ማቅረብ ላይ ክፍተቶች አሉ ነው ያሉት።

በወንጀል ህጉ ከ7 መቶ በላይ የወንጀል አይነቶች አሉ ያሉት ዳኛው፣ ወደ ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ ከሚመጡ ክሶች መካከል አስገድዶ መድፈር ዋነኛው መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በማህበራዊ ድረ-ገፆች አማካኝነት በህፃናት ላይ የሚደርሱ ወንጀሎችም በዛው ልክ አደገኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 06 ቀን 2015 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos