Get Mystery Box with random crypto!

ትራምፕ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። የትራምኘ የፍርድ ሂደት የሚካሄድበት በሚያሚ የሚገኘው ፍርድ | Ethio Fm 107.8

ትራምፕ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።

የትራምኘ የፍርድ ሂደት የሚካሄድበት በሚያሚ የሚገኘው ፍርድ ቤት አካባቢም ጥንቃቄ የተሞላበት መረጋጋት ሰፍኗል።

በሚያሚ በሚገኘው ፍርድ ቤት አቅራቢያ የትራምኘን የፍርድ ሂደት ለመከታተልም በርካታ ሰዎች፤ጋዜጠኞች እና የህግ አካላት ተገኝተዋል።

በአካባቢው ከሚያንዣብቡ ሂሊኮፕተሮች ውጪ ያለው ሁኔታ እጅግ ፀጥታ የሰፈነበት መሆኑ ተነግሯል።

በተጨማሪም የፖሊስ መኪኖች በህንፃው ዙሪያ ባሉ ጎዳናዎች ተሰልፈዋል።

እ.ኤ.አ. በ 2024 እንደገና ለኋይት ሀውስ ለመወዳደር ጥረት በማድረግ ላይ ያሉት ትራምፕ፣ በ2021 ከፕሬዚዳንትነታቸው ከለቀቁ በኋላ ሚስጥራዊ ሰነዶችን አላግባብ በመያዝ በ37 መዝገቦች ክስ የተመሰረተባቸው የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነዋል።

የቀረበባቸው ክስ ውድቅ ያደረጉት የቀደሞ የአሜሪካው ፕሬዝደንት የፍርድ ሂደታቸውን ለመከታተል በሚያሚ ተገኝተዋል።

የሚያሚ ከንቲባ ፤ ከተማዋ ለትራምፕ የፍርድ ቤት ውሎ በዝግጅት ላይ ነች ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ይህንንም ሁኔታ ለመጠባበቅ ፖሊስ እንደተሰማራ ከንቲባው ገልጸዋል፡፡(አልጀዚራ እና ቢቢሲ)

በየውልሰው ገዝሙ

ሰኔ 06 ቀን 2015 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos