Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Fm 107.8

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofm107dot8
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.12K
የሰርጥ መግለጫ

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-05-19 16:04:20
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት በቡድን ሰባት አባል ሃገራት ጉባዔ ላይ እንደሚሳተፉ ተነገረ፡፡

ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ በጃፓኗ ሄሮሺማ ከተማ ዛሬ በሚጀምረዉ የቡድን ሰባት ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ላይ በአካል እንደሚገኙ ታዉቋል፡፡

ቀደም ሲል ዘሌንስኪ አሁን ካለዉ የፀጥታ ሁኔታ አንፃር ወደ ጃፓን እንደማይጓዙ የተነገረ ቢሆንም፣ ሩሲያ ላይ ጫና ለማሳደር በአካል እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡

የቡድን ሰባት አባል ሀገራት መሪዎች በሩሲያ ላይ ጠንከር ያለ ማእቀብ ለመጣል በጃፓኗ ሄሮሺማ ተሰባስበዋል፡፡

ሀገራቱ ከሩሲያ በተጨማሪ ቻይና ላይም መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ይጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዘገበዉ አልጄዚራ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ
ግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
1.8K views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 15:52:47
የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 ከየካቲት 5/2012 ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን፤ ይህ አዋጅ የታክሱን መሰረት በማስፋት እና የታክሱን አስተዳደር ስርዓት በመቀየር ከፍተኛ ጠቀሜታን ማስገኘቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 19/2015 ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባኤው በአዋጁ ላይ የቀረቡ ማሻሻያዎችን ታሳቢ በማድረግ የአዋጁ ማሻሻያ መድረጉንም ሚኒስቴሩ አስታውሷል።

የአዋጁ ማሻሻያ ታሳቢ ያደረገው ተደራራቢ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ምርቶች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ላይ የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፈል ለማድረግ፣ የኤክሳይዝ ታክስ ተጥሎባቸው የነበሩት አንዳንድ ምርቶች ላይ ታክሱን ለማንሳት መሆናቸው ተገልጿል።

በመሆኑም ገቢዎች ሚኒስቴር የአዋጁ ማሻሻያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል እንዲደረግ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት፤ የንግዱ ማህበረሰብ ሁሉ እንዲያውቁት መመሪያ ተሰጥቷል ተብሏል።

 የተደረገው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ማሻሻያ ከሥር ተያይዟል፤
1.8K views12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 11:21:30 የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
2.4K views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 11:30:17
ምርጫ ቦርድ የህወሓትን የስረዛ ውሳኔ እንዲነሳ የቀረበውን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ላይ ያስተላለፈውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሥረዛ ፓርቲው ይነሣልኝ ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ውድቅ አደረገ።

ቦርዱን በውሳኔው የህወሓትን ስረዛ ለማንሳት የሚያስችል የሕግ ድጋፍ አለመኖሩን በመጥቀስ በሕጉ መሠረት እንደአዲስ አመልክቶ በሕግ አግባብ መስተናገድ እንደሚችል ገልጷል።

የቦርዱ ደብዳቤ ከታች ተያይዟል።

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
1.0K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 11:04:13
በእለተ ቅዳሜ በምሳ ሰዓት ጨዋታ በድጋሚ በተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኒውካስትል ዩናይትድ ከሜዳ ውጪ ሊድስ ዩናይትድ ጋር ከቀኑ 8:00 ጀምሮ የሚያደርጉትን ብርቱ ፍልሚያ ድሪብል ስፖርት የኢትዮጵያዊያን በሆነው 107.8 ላይ ለአድማጮች ይዞ ይቀርባል።|

ሊድስ ዩናይትድ ከ ኒውካስትል ዩናይትድ
ኤላንድ ሮድ
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
ከቀኑ 8:00 ጀምሮ

<<ድሪብል ስፖርት>>

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
1.1K viewsedited  08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 18:28:00
በአማራ ክልል በባህርዳር እና በሌሎችም ትልልቅ ከተሞች ታግዶ የነበረው የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት ተለቋል።

በአማራ ክልል ከልዩ ኃይል እንደገና መደራጀት ጋር ተያይዞ በተከሰተው አለመግባባት በትልልቅ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ እንደቆየ ሲገለጽ ነበር።

ካሳለፍነው ረቡዕ ግንቦት 2/2015 ምሽት ጀምሮ ግን አገልግሎቱ መለቀቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከነዋሪዎቹ አረጋግጧል።

የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩት ጎንደር፣ ባህርዳር እና ወልዲያ ከዕረቡ ምሽት ጀምሮ መስራት እንደጀመረ ታውቋል፡፡

የሞባይል ዳታ አገልግሎት በአማራ ክልል በጎንደር፣ በባህርዳር እና በወልዲያ ከተማ ከተዘጋ ከኹለት ሳምንታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን፣ የተዘጋበት ዋና ምክንያት በክልሉ ከሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ኃይልና ከክልሉ ልዩ ኃይል ጋር በተገናኘ በተፈጠረው ውጥረት እንደነበር ተነግሯል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
2.8K viewsedited  15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 17:55:00
የሩሲያ ሄሊኮፕተር በክሪሚያ በልምምድ ላይ ሳለ ተከስክሶ አብራሪዎች ሞቱ።

ኤም-28 የተሰኘው ሄሊኮፕተር ዣንኮይ በተባለው የክሪሚያ አካባቢ ልምምድ በማድረግ ላይ እንደነበር የሩሲያ የመከላከያ ሚንስቴር አስታውቋል።

እስካሁን ባለው መረጃ ለአደጋው መከሰት የሄሊኮፕተሩ ውስጣዊ ክፍል ላይ የሰከሰተ ብልሽት መሆኑን ሚንስቴሩ ገልጿሏ።

በአደጋውም በልምምድ ላይ የነበሩ ሁለት አብራሪዎች ሕይወት ማለፋን አር ቲ ዘግቧል።

በሙሉቀን አሰፋ

ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
2.7K views14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 17:35:18 ከግል ጉዳዩ ጋር በተያያዘ የወረዳ ስራ አስፈፃሚውን የገደለ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገለጸ፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ የእለት ከእለት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ እንዳሉ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ/ም ማለትም ዛሬ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ በፖሊስ አባል ተገድለዋል፡፡

ግድያውን የፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል የግል ጉዳዩ እንዲፈፀምለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት ያመለክታል፡፡

ወረዳው ጉዳዩን ተመልክቶ ምላሽ እንደሚሰጠው የተገለፀለት ቢሆንም ጥያቄዬ እንዳይፈፀም የከለከልከው አንተነህ በሚል ምክንያት የወረዳውን ዋና ስራ አስፈፃሚ ቢሯቸው ውስጥ በስራ ላይ እንዳሉ በታጠቀው ሽጉጥ መግደሉ ታውቋል ብሏል ፖሊስ፡፡

ወንጀሉን የፈፀመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የፖሊስ አባሉ በፈፀመው ድርጊት ማዘኑን በመግለፅ ለሟች ቤተሰቦች ፣ ጓደኞችና የስራ ባልደረቦች መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
2.5K viewsedited  14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 14:55:39
በአዲስ አበባ ከተማ 6ኛ ዙር የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራ ትላንት ተጀምሯል።

በ6ኛ ዙር በተመረጡ በሰባት ክፍለ ከተሞች ከግንቦት 03/09/2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ ተከታታይ አምስት ወራት 50 ሺህ የመሬት ይዞታዎችን የማረጋገጥ ስራ ይካሄዳል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታውቋል።

ኤጀንሲው ምዝገባው ፦

በኮልፌ ቀራኒዮ፣
በቂርቆስ፣
በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣
በቦሌ፣
በአዲስ ከተማ፣
በልደታና በአራዳ ክፍለ ከተሞች ባሉ 50 ቀጠናዎችና 211 ሰፈሮች እንደሚከናወን ገልጿል።

ይህ የይዞታ ማረጋገጥ እወጃ ከተላለፈ ከ15 ቀናት በኃላ የይዞታ ይረጋገጥልኝ ጥያቄዎች በክፍለ ከተማ ቅ/ጽ/ቤቶች ቀርበው ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይቻላል ተብሏል።

ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ በተመረጡ ቀጠናዎችና ሰፈሮች ስራው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ባለቱ አምስት ወራት ውስጥ የመረጃ ልዩነት እንዳይፈጠር ሲባል ምንም ዓይነት የስመ- ንብረት ዝውውር አገልግሎት እንደማይሰጥ ኤጀንሲው ማስታወቅን ከአ/አ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
2.7K views11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 14:46:20
በመዲናዋ ባሉ የነዳጅ ማደያዎች ላይ መጨናነቅ መፈጠሩ ተገለፀ፡፡

በመዲናዋ ባሉ የነዳጅ ማደያዎች ላይ ከሰሞኑ መጨናነቅ መስተዋሉን የነዳጅ ማደያዎች ማህበር አስታውቋል።

የነዳጅ ማደያዎች ማህበር ቦርድ አባል የሆኑት አቶ ደሳለኝ አበባየሁ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ከግንቦት 1/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ በመላው ሀገሪቱ መጀመሩን ተከትሎ ወደ አዲስ አባባ ዙሪያ ሄደው ይቀዱ የነበሩ ተሸከርካሪዎች ወደ ከተማዋ ተመልሰው እየቀዱ በመሆኑ መጨናነቅ መፈጠሩን ገልፀዋል፡፡

ከሰሞኑ ተረጋገግቶ የነበረው ሰልፍ የተመልሰው በዚህ ምክንያት ነው የሚሉት የቦርድ አባሉ፣ ቀስ በቀስ ግን ወደ ነበረበት ይመለሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

የኤልክትሮኒክስ የነዳጅ ግብይቱ ተግባራዊ ሲደረግ በርካታ መጨናነቆች ተፈጥረው እንደነበር ያስታወሱት አቶ ደሳለኝ፣ አሁንም ቴክኖሎጂው ችግር ፈቺ እና ኑሮን ለማቅለል የመጣ መሆኑን ህብረተሰቡ ሊረዳን ይገባል ብለዋል፡፡

ነዳጅ በኤልክትሮኒክስ ግብይት በመላው ሀገሪቱ ከግንቦት አንድ ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡

በክልሎች አከባቢ ያለው የህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀርፈው የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬተር ወይዘሮ ሰሀርላ አብዱላሂ አስታውቀዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም
2.2K views11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ